ጢሞቴዎስ ማን ነው?
◉ ጢሞቴዎስን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚናገኘው በሐዋ 16፡1-5 ነው፤ ያደገው ደግሞ ልስጥራን በምትባል ከተማ ነው፡፡
◉ አባቱ የግሪክ ሰው፣ እናቱ አይሁዳዊት ነበረች። በእናቱ ኤውንቄና በአያቱ ሎይድ በኩል የብሉይ ኪዳንን ተምሯል (2ኛ ጢሞ 1፡ 5፤ 2ኛ ጢሞ 3፥14-15)፡፡
◉ ጢሞቴዎስ የጳውሎስ አጋዥ ነበር፡፡ ለ15 ዓመታት ከጳውሎስ ጋር አብሮ ሲያገለግል ነበር፡፡
◉ ጢሞቴዎስ ወጣት ቢሆንም እንኳ ጠንካራ የቤተ ክርስቲያን መሪ ሊሆን እንደሚችል ጳውሎስ ስለተረዳ ይዞት ለመዞር ፈለገ፡፡ ሆኖም ጢሞቴዎስ በእናቱ ምክንያት አይሁዳዊ ቢሆንም፤ ካልተገረዝ በቀር በአይሁዶች ዘንድ ተቀባይነት ስለማይኖረው ገረዘው፡፡
◉ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያጽናና በመጀመሪያ ወደ ተሰሎንቄ ተላከ (1ኛ ተሰ 3፥2)። ከዚያም ወደ መቄዶንያና ወደ ቆሮንቶስ ተላከ (1ኛ ተሰ 3፥4-7)። ከዚያም የተሰበሰበውን የእርዳታ ገንዘብ ይዞ ከጳውሎስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ (ሐዋ 20፡4)፡፡
◉ ጳውሎስ የፊልጵስዩስንና የቄላስያስን መልዕክቶች ሲጽፍ ጢሞቴዎስ አብሮት ነበረ (ፊል 1፥1፤ ቄላ 1፥1)፡፡
◉ ጳውሎስ ሁለቱን መልዕክቶችን ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ እርሱ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያገለግል ነበረ (1ኛ ጢሞ 1፡3)፡፡
◉ ጢሞቴዎስ ባልታወቀ ጊዜ ታስሮም ነበር (ዕብ 13፡23)
◉ ጢሞቴዎስ የጳውሎስ ታማኝ ረዳት በመሆን እስከ መጨረሻው ጸንቶ የክርስቶስን ወንጌል በታማኝነት አብሮት አገለገለ፡፡
@zemeru
በማስተዋል ዘምሩ Telegram Channel JOIN US for more Updates!