በሸገር ከተማ የ17 ዓመቱን ታዳጊ በማገት 2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የጠየቁ ሁለት ግለሰቦች በ24 ዓመት እስራት ተቀጡ
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር በመልካኖኖ ክፍለከተማ መልካገፈርሳ ወረዳ ዉስጥ ነዉ። መሀመድ አሚን እና አቡበከር ረሺድ የተባሉ ግለሰቦች ድርጊቱን መፈፀማቸዉን የመልካኖኖ ክፍለከተማ ፖሊስ የምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ብርሃኔ ሁንዴሳ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ሁለቱ ግለሰቦችች ከፍተኛ ገንዘብ ለማግኘት የሚያስችላቸዉን ዕቅድ በማዉጣት ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም አቶ ፍቅሩ ከተባሉ ግለሰብ ላይ ቤት ይከራያሉ። ቀን ቀን የሚያጠኑበትን ቤት መከራየት እንደሚፈልጉ በመንገር የሁለት ወር ክፍያ 40 ሺህ ብር በመክፈል ቤቱን መከራየታቸዉ ተገልጿል። በተከራዩበት ቤት ዉስጥ በመሆን ማንን አግተን ከፍተኛ ብር አግኝተን እንለወጣለን በማለት ያቅዳሉ።በዚህም የተነሳ አንደኛ ተከሳሽ የአጎቱ ልጅ የሆነዉን ሰሚር ሬደዋንን ቢያግቱት ቤተሰቦቹ ሀብታም በመሆናቸዉ ከፍተኛ ብር እንደሚያገኙ ሀሳብ ያቀርባል። ሰሚርን አግተዉ ቤተሰቦቹ ጋር በመደወል 2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ካልስገቡ ልጃቸዉን በህይወት እንደማያገኙት ይነግራቸዋል ።
ቤተሰቦች 2 ሚሊዮን ዶላር እንደሌላቸዉ እና 1ሚሊዮን ብር እንደሚያስገቡላቸዉ የነገራቸው ሲሆን በዚህ አለመስማማታቸዉ ግን ተገልጿል። ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ማታ 1:30 ላይ ቤተሰቦችህ አይፈልጉህም ብሩንም ለማስገባት ፍቃደኛ አይደሉም በማለት የ17 ዓመቱን ታዳጊ አንገቱን በማነቅ እንደገደሉት ተገልጿል ። ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ አስክሬኑን በሸራ ጠቅልለዉ ከቤታቸዉ ጀርባ ወደ ሚገኝ ገደል ይጥላሉ። ከስራ በመመለስ ላይ የነበረ የፌደራል ፖሊስ ምን እንደያዙ ሲጠይቃቸዉ ቆሻሻ ነው በማለት አስክሬኑን እዛዉ በመጣል ከአከባቢው መሠወራቸዉ ተገልጿል ።
ወንጀሉ ከተፈፀመ በኋላ የተጣለ አስክሬን ሪፖርት ለፖሊስ ይደርሰዋል፡፡ሟቹ ማን እንደሆነ መዝገብ የሚያጣራ ፣ማስረጃ የሚሰበሰብ እና ወንጀለኞቹ እንዴት ይያዛሉ ፣እነማን ናቸዉ የሚለዉን የሚያጣራ ሁለት ቡድን ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱ ተገልጿል ። አንጀኛ ተከሳሽን በአዲስአበባ በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን ሁለተኛ ተከሳሽ ከብዙ ዉጣዉረድ በኋላ በጉራጌ ዞን ተይዟል። የምርመራ መዝገቡ በበቂ መረጃ ተደግፎ አቃቤ ህግ ክስ ይመሰርታል፡፡ ክሱን የተመለከተዉ ፍርድ ቤት ሁለቱን ተከሳሾች ጥፋተኛ በማለት በ24 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ዉሳኔ ማስተላለፋን ኢንስፔክተር ብርሃኔ ሁንዴሳ ጨምረዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል