ለ20 አመት ያለ ደሞዝ ህብረተሰቡን ያገለገሉት እውቅና ተሰጣቸው።
በክርስትያን ሆስፒታል ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን ሲያገለግሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጣቸው
በክርስትያን ሆስፒታል ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን በነፃ ሲያገለግሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዕውቅና የተሰጣችው ሲሆን እነዚህም፡-
1ኛ ዶክተር ዱዌን አንደርሰን እና ባለቤታቸው ጃኪ አንደርሰን ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በፍፁም በቅንነትና በታማኝነት እና በልዩ ፍቅር ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ታካሚዎችን በማገልገላቸው፣
2ኛ- ዶክተር ማርክ ክርንስ እና ባለቤታቸው አሊሰን ካርንስ ወደ ወላይታ ሶዶ በመምጣት ላለፉት 16 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በታላቅ ትህትና በሆስፒታሉ በማገልገል፣ ሀኪሞችን በማስተማር እና በማሰልጠን ላደረጉት አስተዋጽኦ።
3ኛ ሚስተር ኬን አስሙዝና ባለቤታቸው ማርጋሪት አስሙዝ ላለፉት 20 ዓመታት የሴንት ሉክስ ቦርድ አባል በመሆንና ከውጪ ሀገር አጋሮች ለሆስፒታሉ ልማት የሚውሉ ገንዘብ እና ቁሳቁስ በማሰባሰብ ያለምንም ክፍያ በታማኝነት በማገልገላቸው:-
በዚህም መሰረት ለመላው ኢትዮጵያዊያን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ለበጎ ምግባራቸው በክልሉ መንግስት እና በወላይታ ዞን አስተዳድር የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ።
#ዳጉ_ጆርናል