ፑቲን አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነትን ውድቅ አደረጉ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በሃይል መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ብቻ በመስማማት በዩክሬን አፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ የተኩስ አቁም ስምምነትን ውድቅ አድርገዋል። የትራምፕ ቡድን በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ከዩክሬናውያን ጋር የሰራውን አጠቃላይ የአንድ ወር የተኩስ አቁም ስምምነት የሩሲያ መሪ ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም። አጠቃላይ የእርቅ ስምምነት ሊሰራ የሚችለው የውጭ ወታደራዊ ዕርዳታ እና ከዩክሬን ጋር ያለው የመረጃ ልውውጥ ካቆመ ብቻ ነው ብለዋል።
የዩክሬን አውሮፓውያን አጋሮች ቀደም ሲል እንደነዚህ ያሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ውድቅ አድርገዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ንግግር የፊታችን እሁድ በጅዳ ሳውዲ አረቢያ እንደሚቀጥል በመካከለኛው ምስራቅ የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። ለሦስት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ሩሲያ ከስድስት ወራት በፊት በዩክሬን ወረራ የተነጠቀችውን የኩርስክ ክልል ግዛት በቅርቡ ማስመለስ ችላለች። የማክሰኞው የትራምፕ-ፑቲን ውይይት ከአሜሪካ አቋም ከሳምንት በፊት ከቆመበት ማፈግፈጉን ያሳያል። ሆኖም ግን ሁለቱ መሪዎች በመካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ የሰላም ድርድር እንደሚደረጉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የልዑካን ቡድን ባለፈው ማክሰኞ ከዩክሬን አቻዎቻቸው ጋር በጄዳህ ሲገናኝ ኪየቭ በመሬት፣ በአየር እና በባህር ላይ ለ30 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲስማማ ባቀረቡት ሀሳብ ዩክሬንን አሳምነው ነበር።የትራምፕ እና የፑቲን የስልክ ዉይይት ካበቃ በኋላ ማክሰኞ እለት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ በፊንላንድ ሄልሲንኪ የገቡት ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ዩክሬን የኢነርጂ መሠረተ ልማትን የሚሸፍን የእርቅ ስምምነት ሀሳብ ክፍት እንደሆነች ገልፀው ነገር ግን በመጀመሪያ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ትፈልጋለች ብለዋል። የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጥቃት ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነትን አልቀበልም በማለታቸው ፑቲንን ከሰዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል