ዜና ETHIOPIA 🇪🇹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Telegram


ዜና ETHIOPIA 24 || ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ
ተአማኒ እና ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት የምታገኙበት ልዩ የኢትዮጵያውያን ቻናል ነው።
🇪🇹ወቅታዊ መረጃዎች
🇪🇹ልዩ ልዩ ዘገባዎች
🇪🇹መዝናኛ ዜናዎች
🇪🇹ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል
ጥቆማ ለመስጠት 👇
@ethiopian_zena_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


በማረሚያ ቤት ውስጥ ፎቶ ተነስተዋል በተባሉት ታራሚዎች ዘንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ በፍተሻ መገኘቱን የፌደራል ማረሚያ ቤት አስታወቀ

ከሰሞኑ በማረሚያ ቤት የአየር መንገድ ደህንነትን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው የሚከታተሉ እነ ጆን ዳንኤል ከማረሚያ ቤት ሆነው ለቀውታል በተባለ ፎቶ ዙሪያ ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳሬክተር አቶ ገረመው አያሌው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ስልኩ በፍተሻ ተገኝቷል።

ይህን ባደረጉ አካላት ላይ የማጥራት ስራ ተሰርቶ ጥፋተኛው ላይ በአሰራሩ መሠረት በህግ አግባብ ተመጣጣኝ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አቶ ገረመው ለብስራት ተናግረዋል።

Via:ዳጉ ጆርናል

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ራያ ቆቦ‼️

በራያ ቆቦ የሚገኘው ሮቢትንና ጎብየን የሚያገናኘው የአሚድ ድልድይ ተሰብሯል።

የሚመለከተው አካል አስቸኳይ ጥገና እንዲያደርግለት መልክታችን ነው።🙏

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


የኬንያ መንግስት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ 'ልዩ የፀጥታ ዘመቻ' መጀመሩን አስታወቀ።

የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በማርሳቢት እና ኢሲዮሎ ግዛቶች በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ 'ልዩ የፀጥታ ዘመቻ' መጀመሩን አስታውቋል።

አገልግሎቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚጠቀምባቸውን መሸሸጊያዎች ለቆ እንዲወጣ ለማድረግ “ኦንዶአ ጃንጊሊ ኦፖሬሽን” የተባለ ዘመቻ ከትናንት ጥር 26 ቀን ጀምሮ እንደሚያካሄድ ገልጿል።

በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄደው ዘመቻ ለኬንያ ብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሚጥሉ እንደ የጦር መሳሪያ፣ የአደንዛዥ ዕፅ እና የሰዎች ዝውውር፣ ህገወጥ የማዕድን ማውጣት ያሉ ህገወጥ ስራዎችን የሚያከናውኑ ወንጀለኞችን ዒላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ውል እንዲቋረጥ ሊደረግ ነው...
በCDC እና USAID የበጀት ድጋፍ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ውል እንዲቋረጥ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ‼️

ከአሜሪካ መንግሥት በCDC ወይም USAID አማካይነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከJanuary 24 ቀን 2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ ደርሶናል ሲል ጤና ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎች በበተነው ደብዳቤ ተመልክተናል።

በCDC እና USAID የበጀት ድጋፍ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ውል እንዲቋረጥ ተወስኗል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


በኦሮሚያ ክልል ጉጆ ዞን በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ 8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

አደጋው በትናንናው ዕለት 9 ሰዓት ላይ የደረሰ ሲሆን፤ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት ሥራ በተሰማሩ ዜጎች ላይ መድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን አስከሬን ከተደረመሰው አፈር ውስጥ የማውጣት ሥራ መከናወኑም ተገልጿል፡፡

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


በሱዳን አማፂ ቡድን በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 44 ሰዎች ተገደሉ
በሱዳን የደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ካዱግሊ በአብዴላዚዝ አል ሂሉ የሚመራው የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ ወይም የኤስ ኤልኤም-ኤን አንጃ በፈጸመዉ ጥቃት ቢያንስ 44 ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ 28 ቆስለዋል ሲሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ኤስ ኤልኤም-ኤን በደቡብ ኮርዶፋን እና ብሉ ናይል ከ2011 ጀምሮ የሱዳን ጦርን እየተዋጋ ሲሆን ለሁለቱም ክልሎች ልዩ ቦታ እንዲሰጠው ጠይቋል።
የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ እንዳለው የኤስ.ኤል.ኤል.ኤን ሃይሎች ሰኞ ማለዳ መድፍ በመተኮስ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ከሟቾቹ መካከል ኢማም ኒዛር መሀመድ ቶም የሚገኙበበት ሲሆን በታሪካዊው የካዱግሊ አሮጌ መስጊድ ኃይማኖታዊ አባት ነበሩ።የደቡብ ኮርዶፋን አስተዳዳሪ መሀመድ ኢብራሂም አብደልከሪም ጥቃቱን “በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመ አረመኔያዊ ጥቃት” ሲሉ አውግዘዋል።
የሱዳን ጦር ውጤታማ የአጸፋ ምላሽ በመስጠጽ በአማፂያኑ ላይ በሰው ሃይል፣በተሽከርካሪ እና በመሳሪያ ረገድ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረስ መሳሪያና ጥይቶችን መያዙንም ተናግረዋል። ታጣቂ ቡድኑ በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።
በሱዳን ያለዉ ጦርነቱ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችን ለሞት መዳረጉን እና ወደ 14 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን መፈናቀቻን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የሱዳን ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ሆኖም የሟቾች ቁጥር እስከ 130 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል አንድ የዩናይትድ ስቴተስ ዩኒቨርሲቲ ያደረገዉ ጥናት ያሳያል።
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ኬንያ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ 'ልዩ የፀጥታ ዘመቻ' ጀመረች

የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በማርሳቢት እና ኢሲዮሎ ግዛቶች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚጠቀምባቸውን መሸሸጊያዎች ለቆ እንዲወጣ ለማድረግ “ኦንዶአ ጃንጊሊ ኦፖሬሽን” የተባለ ዘመቻ ከትናንት ጥር 26 ቀን ጀምሮ እያካሄደ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄደው ዘመቻ ለኬንያ ብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሚጥሉ እንደ የጦር መሳሪያ፣ የአደንዛዥ ዕፅ እና የሰዎች ዝውውር፣ ህገወጥ የማዕድን ማውጣት ያሉ ህገወጥ ስራዎችን የሚያከናውኑ ወንጀለኞችን ዒላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


የዕለቱ አንኳር ዜናዎች

1. የትግራይ ልሂቃን ልዩነታቸውን በመግባባትና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲፈቱ ጥሪ ቀረበ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ልሂቃን በውስጣቸው ያለውን ልዩነት በመግባባት፣ በሰላም እና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ ሉፈቱ ይገባል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለክልሉ ልሂቃን እና ለትግራይ ሕዝብ መግለጫ አውጥተዋል። ይሁን እንጅ በተለያዩ አጋጣሚዎችና በተለያዩ ምክንያቶች፣ በተለይ ደግሞ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ባጋጠመ አለመግባባት የትግራይ መሬት የጦርነት አውድ፤ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የጦርነት ሰለባ መሆኑን ገልፀዋል። የትግራይ ህዝብ የትላንት ቁስሉ ሳይሻር፣ ገና አሁንም ሰላምና እፎይታ አግኝቶ ሰርቶ እንዳይገባ በፍራቻና ጭንቅ የጦርነት ወሬ እየኖረ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ከፌዴራል መንግስት ይሁን ሌሎች ሃይሎች ጋር ያሉትን ልዩነቶች በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመግባባት ለመፍታት ዝግጁ እንዲሆኑ መክረዋል። በፌዴራል መንግስት በኩል፥ በሁሉም ጉዳዮች ለመነጋገር እና የሐሳብ ልዩነት እንደ ልዩነት በመውሰድ በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰላም መስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

2. በአማራ ክልል ያሉ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎቻቸው የተግባር ተኮር ስልጠና ለመስጠት የጸጥታ ችግር እንቅፋት ሆኖብናል አሉ። የጤና፣ ህግ፣ ታሪክና መሰል የትምህርት መስኮች የሚማሩ ተማሪዎችን ለተግባር ተኮር ስልጠና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለመውሰድ በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር ተግዳሮት እንደሆነባቸው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል። አሁን ላይ የህግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ራቅ ወዳለ ቦታ ሳይሄዱ በከተማው ለማሰልጠን የታቀደ ቢሆንም እንደ ታሪክ እና ጤና የመሳሰሉት የትምህርት መስክ ሰልጣኞች ወደ ሌላ ክልል እና ከተማ ተንቀሳቅሰው የሚማሩት እንደመሆኑ ሰልጣኞች ከሌሎች ጋር በሚኖራቸው ውድድር ተጽዕኖ ይፈጥርባቸዋል ተብሏል።

3. በትግራይ ክልል የጤና መድህን አገልግሎት ለማስጀመር በሚደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ በክልሉ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው። በክልሉ በነበረው ጦርነት የጤና መድህን አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል። ይሁን እንጅ በክልሉ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት፤ የበጀት እና የሰው ኃይል እጥረት ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑን በኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የመቀሌ ቅርንጫፍ ተናግሯል። 206 ሰራተኞች እንዲቀጠሩ የማድረግ እንዲሁም ማህበረሰቡ አሁን ባለበት የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት የአገልግሎቱን ክፍያ መፈጸም ስለማይችል 50 በመቶ የሚሆነውን በተቋሙ መሸፈን እንዲያስችል የሃብት ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። የምዝገባ ሂደቱን በታህሳስ ወር ለማስጀመር የታቀደ ቢሆንም በታቀደው የጊዜ ቀጠሮ ማስኬድ አልተቻለም።

4. በዳውሮ ዞን በትራፊክ አደጋ የ 2 ሰዎች ህይወት አለፈ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ከገሣ ከተማ ወደ ሎማ ባሌ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዚ ተገልብጦ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ በደረሰው አደጋ 10 መንገደኞች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሳባቸውም ተገልጿል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቅራቢያ ወደሚገኙ የጤና ተቋማት ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተጠቅሷል።

5. ደቡብ አፍሪካ ለዶናልድ ትራምፕ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ሰጠች። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለደቡብ አፍሪካ የሚሰጠው ድጋፍ ይቋረጣል ሲሉ በትናንትናው ዕለት ዝተው ነበር። ሀገሪቱ መሬት እየወረሰች ነው፤ አንዳንድ የማህበረሰብ ክፍሎችም በመጥፎ ሁኔታ እየታዩ ነው ሲሉ የተናገሩት ፕሬዝዳን ዶናልድ ትራምፕ ዝርዝር መረጃዎችን ግን ይፋ አላደረጉም። ይሁንና በሁኔታው ላይ አስፈላጊው ምርመራ እስኪካሄድ ድረስ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚላክ እርዳታ እንደሚቋረጥ አስታውቀዋል። በአውሮፓዊያኑ 2023 አሜሪካ የ440 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለደቡብ አፍሪካ ሰጥታ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ። ይህ በዚህ እንዳለ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ግን አሜሪካ ለኤችኤይቪ ኤድስ መከላከል ድጋፍ ካልሆነ በስተቀር የተለየ የገንዘብ ድጋፍ ከዋሸንግተን እንደማያገኝ አስታውቋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


የዕለቱ አንኳር ዜናዎች

1. ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በራሳቸው መገበያያ ገንዘብ ለመገበያየት መስማማታቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ ጋር በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ተስማምተዋል ተብሏል። የዩክሬኑን ጦርነት ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ከዶላር ውጭ የሆነ ግብይት ለመፈጸም ስምምነቶችን እያደረገች የምትገኝው ሞስኮ ተጨማሪ ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን አካታለች፡፡ ይህን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት ስምምነት ላይ የደረሱ ሀገራት 40 ደርሰዋል። በዚህም ሀገራቱ ከሩሲያ ጋር በሚፈጽሙት ግብይት የሚያጋጥማቸውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ እና የተሸለ የንግድ ትስስር ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል። ከዚህ ባለፈም የብሪክስ አባል ሀገራት ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም እና ነጻ የግብይት ሰንሰለት ለመፍጠር ባስቀመጠው ዕቅድ የራሱን የመገበያያ ገንዘብ ማስተዋወቁ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህን ገንዘብ ተግባራዊ ማድረግ እና ዶላርን ከዋና የመገበያያ ገንዘብነት ለማስወጣት የሚደረግ ጥረት በሀገራት ላይ ማዕቀብ እና የ100 በመቶ ታሪፍ ጭማሪን ተግባራዊ እንደሚያስደርግ ዝተዋል፡፡

2. በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት በይፋ ተቋቁሞ ስራ ጀመረ፡፡ የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሙና በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አቶ ሞገስ ታፈረን የምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ አድርጎ የመረጠ ሲሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ነጻነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑትነ ዶ/ር ደጀን መዝገቦን ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መምረጡ ተገልጿል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ከሲቪል ማህበራት፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ዲያስፖራ፣ የክልሉ ሙሁራን እና የጸጥታ አካላት ተወካዮችን ያካተተ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ ትላንት በተቋቋመው የአማካሪ ምክር ቤቱ ወስጥ ግን የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ ሳልሳይ ወያነ ፖለቲካ ፓርቲ፣ የክልሉ ዲያስፖራ አባላት ተወካዮች አልተሳተፉም ተብሏል። በቀጣይ እንዲሳተፋ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ተናግሯል፡፡

3. በፌደራል ፍርድ ቤቶች ዕልባት እንዲሰጥባቸው የሚመጡ ጉዳዮች ቁጥር በየወቅቱ እየጨመረ በመምጣቱ ለመዛግብት በጊዜ ውሳኔ ከመስጠት አንፃር ብዙ መስራት ያስፈልጋል ተባለ፡፡ በፍርድ ቤቶች ተገልጋይ የሚፈልገዉንና የሚጠብቀዉን የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ከፍጥነትና ከጥራት አንፃር መልስ መመለስ በሚያስችል መንገድ መፈፀም ካልተቻለ የሚፈልገዉን ውጤት ማምጣት አስቸጋሪ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናግሯል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ 2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱ በእቅድ ከተያዙት 64ሺህ 703 መዛግብት 84ሺህ 207 መዛግብት እልባት መስጠቱን ተናግሯል፡፡ ይህ አፈፃፀም ካለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ20,734 መዛግብት ከፍ ያለ መሆኑ ተጠቅሷል። በአጠቃላይ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ዕልባት እንዲሰጥባቸው በዕቅድ ከተያዙ መዛግብት አንፃር ከፍ ያሉ አፈጻጸሞች እየታዩ ቢሆንም በየወቅቱ እየጨመረ ከመጣው የመዛግብ ፍሰት ጋር ተያይዞ እየቀረቡ ላሉ ጉዳዮች ውሳኔ ለመስጠት ብዙ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

4. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ። ባንኩ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 58.3 በመቶ መሰብሰብ መቻሉንም ገልጿል። በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድሥት ወራት 245 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን ከ1 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችያለሁ ብሏል።

5. በሱዳን የገበያ ሥፍራ ላይ በተፈፀመ የመድፍ ጥቃት በጥቂቱ የ54 ሰዎች ሞቱ። በሱዳን የርዕሰ ከተማዋ ካርቱም አካል በሆነችው ኦምዱርማን በአንድ የገበያ ሥፍራ ላይ በተፈፀመ የመድፍ ጥቃት በጥቂቱ የ54 ሰዎች ተገደሉ ገበያውን ዒላማ በማድረግ በተፈፀመው የከባድ መሳሪያ ድብደባ ከተገደሉት ሌላ 158 ሰዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት ገጥሟቸዋል። ሰላማዊ ሰዎች ለተገደሉበት እና ለቆሰሉበት የገበያ ስፍራ ድብደባ የመንግስት ጦር RSF የተሰኘውን የፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት በተጠያቂነት ከሷል፡፡

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


በ4 ወር እስር እንዲቀጡ ተወስኗል !!

በ3ቱ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተሰጠ ፍርድ በቅርቡ በቅዱስ ሚካኤል ታቦት እያሾፉ እና እይቀለዱ በቲክ ቶክ ቪዲዮ ለቀው የነበሩት ተማሪ ገመቹ ምትኩ፣  ተማሪ ካሳን አድቬንቸር፣ ተማሪ ጋዲሳ ኢቲና ዛሬ በአምቦ ዳዳቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን እያንዳንዳቸው በ4 ወር እስር እንዲቀጡ ተወስኗል::

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


#Update

ተፈታለች

ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈ ከ4 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ፣ ሰኞ ጥር 26 ቀን 2017ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ተፈትታለች።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ታዬ ደንዳ ❗️


#ዜና_ETHIOPIA


ጅቡቲ አመነች !!

  ከትናንት በስተያ በአፋር ክልል የተፈፀመውን የድሮን ጥቃት አስመልክቶ የጅቡቲ መከላከያ ሚኒስትር መግለጫ ያወጣ ሲሆን የድሮን ጥቃቱን  መፈፀሙን አምኖ 8 ሰው መግደሉን ገልጿል።

የድሮን ጥቃት የተፈፀመው በራሳችን ግዛት ውስጥ ነው ያለ ሲሆን አሸባሪዎችን ለመምታት ነው ብሏል። ለተጎጂዎች እገዛ እናደርጋለን ብሏል።

የጅቡቲ መንግሥት መከላከያ ሚኒስቴር ይሄን ማስተባበያ ቢሰጥም የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በአፋር ክልል ኢልዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ሲሆን የድሮን ጥቃት የተፈፀመው ሁለት ጊዜ ነው።

በዚህ ጥቃት በቀብር ስነስርዓት ላይ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ሰዎች መሞታቸውን እንዲሁም ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውን የአፋር የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ዙሪያ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


በጉደር ከተማ በእሳት አደጋ የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ህጻን ልጅን ጨምሮ ወላጅ አባቱ እና እናቱ ህይታቸው አለፈ

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጉደር  ከተማ  አስተዳደር ውስጥ ወላጆች ከአንድ ዓመት  ከስምንት ወር  ልጃቸው ጋር በእሳት  ቃጠሎ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን የጉደር  ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል ።

ጥር 24 ቀን 2017  ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በጉደር ከተማ አባገዳ  ቀበሌ ውስጥ አቶ ዮናስ ደጀኔ የተባሉ የባለ ሶስት እግር  ባጃጅ አሽከርካሪ  ቤንዚን በጄሪካን ቀንሰው እቤት ውስጥ  ሲያስቀምጡ በድንገት በመኖሪያ ቤቱ በተነሳው  እሳት አደጋ መፈጠሩን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ሰምቷል ።

ቃጠሎው ለአንድ ሰዓት የቆየ ሲሆን  በመኖሪያ ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰም ተገልጿል ። አቶ ዮናስ የተባለው የባጃጅ አሽከርካሪ እና ባለቤቱ ወይዘሮ ብርቱካን የተባለችው እናት ከእነ ልጃቸው ህይወታቸው  ወዲያዉኑ ማለፉ ተነግሯል።  አቶ ዮናስ ባለቤቱን እና ልጁን ከቃጠሎ ለማትረፍ ሲሞክር ህይወቱ አልፏል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ፖሊሶች  ግለሰቦቹን ከእሳት ለመማውጣት የሞከሩ ቢሆንም ሳይሳካለቸው መቅረቱን የሟች የወይዘሮ ብርቱካን ንጉሴ ወንድም አቶ ደበሬ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግሯል።
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ጥንቃቄ‼

ዛሬ 10:00 አካባቢ ወልድያ ከተማ መግቢያ ድልድይ ተደርምሷል።

ጥቆማ ሰጭ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከጅቡቲ /ከቆቦ/ ወደ ወልድያ  መግቢያ  በር  ላይ  ዳቦ ቤቱ አካባቢ ያጋጠመ ነው ብለዋል።

መንገድ ለጊዜው መዘጋቱንም ጠቁመዋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


የጉልበት ስራ ሰርቼ ይቺን ቀን ሳይርበኝ ባሳልፍ ብሎ በየመንገዱ የሚንከራተት የሀገሬ ወጣት እየታፈሰ የሚደርስበት የግፍ ፅዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው

Via:Elias Meseret

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


#Update
ሰመረ ባርያው ተፈቷል !!

ሰመረ ካሳዬ (ሰመረ ባርያው) በዛሬው እለት መፈታቱን አረጋግጠናል ።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቀላል የመኪና አደጋ !!

የዛሬውን ተጠባቂ ሸገር ደርቢን ለመታደም ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ አዳማ ከተማ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን ይዞ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ አደጋ ገጥሞታል ።

ተሽከርካሪው በፈጣን መንገድ ላይ የፊት ጎማው ፈንድቶ ከብረት ጋር ተጋጭቶ አደጋ ድርሶበታል። በአደጋው ምንም ሰው እንዳልተጎዳ ተገልጿል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


የባንኮች ብድር ጉዳይ

ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ መስከረም ላይ ይነሳል

ካለፈው ነሀሴ 2015 ዓ.ም. አንስቶ ተጥሎ የነበረው ባንኮች መስጠት የሚችሉት አዲስ ብድር ገደብ ሙሉ ለሙሉ ሊነሳ መሆኑን ተሰምቷል።

የአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅትን (IMF) መረጃ እንደሚጠቁመው ባንኮች የሚችሉት የብድር መጠን ላይ ተጥሎ የቆየው ጣሪያ በቀጣይ መስከረም ይነሳል።

በነሀሴ 2015ዓም ወደ ስራ የገባው የብድር ጣሪያ ባንኮች አመታዊ የብድር እድገታቸው ከቀደመው የብድር ክምችት  መጠን በ14 በመቶ ብቻ እንዲያድግ የሚያደርግ ነው።

ባለፈው ወር መጨረሻ እድገቱ ወደ 18 በመቶ እንዲሆን በብሄራዊ ባንክ ተወስኖ ነበር። ሆኖም ውሳኔው በባንኮች በአወንታዊ የታየ አልነበረም።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ተገደሉ !!!

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት  ፣  ተመራማሪ እና መምህር  እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው ተገደሉ ።

ዶ/ር አንዷለም ስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል ። 

በ37 ዓመታቸው የተቀጠፍት ዶክተር አንዷለም ፤  በዩኒቨርሲቲው ፣ ብሎም በሀገሪቱ   አሉ  ከሚባሉ በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች አንዱ ነበሩ ።

በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ አውግዟል ።

በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው ብሏል ።

ዶ/ር አንዷለም በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን ሲል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24

20 last posts shown.

1 198

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

ባህር ዳር ከ4 አይሱዙ በላይ የተበላሸ በርበሬ ተያዘ በባህር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒልክ ክፍለ ከተማ ሰላም ቀበሌ በሚገኝ ገባያ ማዕከል ለምግብነት የ...
የትግራይ የሠራተኛ ማሕበራትና የክልሉ መንግስት ዉዝግብ የትግራይ መንግስት ሰራተኞች ማሕበር፣ የትግራይ ዓቃብያነ ሕግ ማሕበር፣ የክልሉ ጤና ባለሙያዎች እ...
በጣም ያማል።በ11 ቀበሌዎች የ770 አርሶ አደሮች ሰብል ወድሟል። ተጎጅ አርሶ አደሮች በዋድላ የደረሰው ጉዳት ከጉዳትም በላይ ነው። በሰሜን ወሎ ዞን...
➤ደሴ ➽226 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ህንፃ ተመርቆ አገልግሎት ጀመረ። @zena_ethiopia24 @zena_ethiopia24
በካሊፎርኒያ የተነሳዉ ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር አልተቻለም ፡፡ አሜሪካ ያላትን አቅም ለመጠቀም ብትሞክርም እስካሁን እሳቱን መቆጣጠር አልቻለችም ፡፡...