🌿 ሆሣዕና 🌿
“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ልጅ ሆይ እልል በይ፤ እነሆ ንጉሥሽ አዳኝ ነው፤ ትሑትም ኾኖ በአህያም፣ በአህያዪቱም ግልገል በውርንጫዪቱ ላዩ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡ ሠረገላውንም ከኤፍሬም፣ ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል፡፡›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ንጉሠ ነቢያት ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም በሄደበት ዕለት ማለትም መጋቢት 22 ቀን በ33 ዓ.ም ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
‹‹ሆሣዕና›› ማለት አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ‹‹ማዳን የባሕርይህ የሆነ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መጥተህ እድነን›› እያሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የጸለዩበትን ጸሎት የያዙትን ሱባኤ ያመለክታል፡፡ በቀድሞ ዘመን በሰረገላ እና በፈረስ የሚቀመጥና ገስግሶ የሚሄድ ጦረኛ ነው፡፡ ጌታ ግን በአህያ ላይ ተቀምጦ መጓዙ የሰላም አምላክ፣ ሰላምን ለዓለም የሚሰጥ፣ ይቅርታውን ለአዳም የሚያደርግ መኾኑን ለማብሰር ነው፡፡
በዕለተ ሆሣዕና የእናታቸውን ጡት የሚጠቡ ሕፃናት ሳይቀሩ በትህትና ዝቅ ብሎ በአህያ ጀርባ ወደ ኢየሩሳሌም የገባውን የባሕርይ ንጉሥ አመስግነውታል፡፡ ይኸውም ይህ ከመሆኑ ከአንድ ሺ ዓመታት በፊት ቅዱስ ዳዊት “ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ›› በማለት በተናገረው ትንቢት መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ እንኳን ሕፃናት ይቅርና ግእዛን የሌላቸው የቢታንያ ድንጋዮችም ጭምር ‹‹በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ቡሩክ አምላክ ነው›› እያሉ አመስግነዋል፡፡ (መዝ. 8፥2-3)
|| @AHATI_BETKERSTYAN