❣ ሒጃብ እና ፋሽን
ክፍል አንድ ታሪክ→ → ①
#ፃፊ→ ራህመት ሙሃመድ
ስንቶች ሴቶች አሉ የጊዜዉ ማዕበል ወደሚነዳቸዉ ሁሉ የሚነጉዱ በተቀደደላቸዉ ቦይ ሁሉ የሚነፍሱ ወደ ነፈሰበት አቅጣጫ ሁሉ እብስ የሚሉ ምን እያደረጉ እንደሆኑ እንኳን ቆም ብለዉ ለማስተንተን ጊዜ ያጡ ይመስላሉ ሳያስተዉሉ ቀስ እያሉ ከዲኑ ራቁ በሒጃብና አባያ ጉዳይ ችላ አሉ በሂደት ብዙ ነገሮች ዘነጉ በደመነፍስ የመጥፎ ሰሪዎችን መንገድ ይከተላሉ በገቡበት ጎዳናም ይገባሉ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች አሊያም ሙናፊቆች በፋሽን ስም አንዳች ነገር ያመጡላቸዉ እንደሆነ ያለ አንዳች ጥርጣሬ ይቀበላሉ ::
የቀደዱላቸዉን ሒጃብ ይለብሳሉ የሰፉላቸዉን አባያ ያጠልቃል አባያዉ ወይም ሒጃቡ ለስም ብቻ ነዉ ያለዉ መስፈርቱን ያሟላና የተፈለገበትን ዓላማ የሚያሳካ አይደለም ሒጃብ በመሠረቱ የሚስብና ሰዉን የሚያስከትል መሆን አልነበረበትም እነርሱ ግን ብቻዉን ዉበት አርገዉ ሰሩት እንዲስብ እንዲያስከትልም አደረጉት ዉበትን ደብቁ ሲባል አወጡት አንዳንዱ ሒጃብ የሚባለዉ ሰዉነትን መሸፈን ሲገባዉ በግላጭ የሚያሳይ ነዉ እይታን ከማራቅ ይልቅ ይሰርቃል።
ሰለሆነም እህቶች ሆይ! በዚህ መልኩ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል የሻቸዉን እንደሚለብሱት ሴቶች አትሁኑ በዲኑ የተወገዙ ነገሮች አትስሩ ፀጉርም ሆነ ሰዉነትን የሚሸፍነዉ ሒጃብ ለትልቅ ዓላማ የተደነገገ ቢሆንም ቅሉ ዛሬ ላይ መስመር ስቶ መልዕክት ያጣ ሆኖ እናገኛለን ከፊሎቹ ያጠሩ አንዳንዶቹ ሆን ብለዉ የተቆረጡ ሌሎች የተከፈቱ የጠበቡ ሰዉነትን የሚያሳዩ የሳሱ እና የመሳሰሉት ናቸዉ ለተመለከቷቸዉ አባያዎቹ ሌላ አባያ ሒጃቦቹ ሌላ ሒጃብ የሚያስፈልጋቸዉ አይነት ናቸዉ ሒጃብ ማለት መጋረድ መሸፈን ማለት ነዉ መሸፈን የተፈለገዉ ከወንዶች ዓይን ነዉ አላህ (ሱ.ወ) የእንስቶች ገላ ለወንዶች ሳቢና ፈታኝ እንዲሆን አድርጎ ፈጥሯል ሒጃብ ወንዶች የሴት ልጅን ገላ እንዳያዩ መከላከያ ነዉ ታዲያ ሒጃብ በራሱ ዉበት ጌጥና ብልጭልጭ ነገር ከተሞላ በእርግጥም ምኑን ሒጃብ ሆነ የአላህ መልክተኛ(ሰ.ዐ.ወ.) ሁለት ዓይነት ሰዎች የእሳት ናቸዉ ካሉትና የጀነት ሽታ ከሩቅ የሚያዉድ ሆኖ ሳለ የጀነት ሽታ አያገኙም ካሏቸዎች ሴቶች መካከል ለብሰዉ ነገርግን እርቃን የሆኑ ሴቶች ናቸዉ። አዎን ልክ ነዉ ለብሰዋል እንዳይባሉ፣ አልለበሱም አለበሱም እንዳይባሉ ደግሞ ለብሰዋል የሚባሉ አይነት ታዲያ ዉዷ እህቴ ጀነት መግባት የማይፈልግ ማን አለ ጀነት መግባት አትፈልጊም የአላህን ዉዴታ ማግኘት አትፈልጊም እህቴ ሆይ! ተኳኩለሽና ተጋጊጠሽ በመዉጣትሽ የሸይጧን መሳሪያ እየሆንሽ መሆኑን አስቢ አንድ ሙስሊም ወንድምሽ ባንች ምክኒያት ሀራም ነገር ላይ እንዲወድቅ ከባድ ወንጀል ዉስጥ እንዲዘፈቅ ትወጃለሽ በፍፁም እህቴ እንደዚህ መሆን የለብሽም በፋሽን በስልጣኔ ስም ኢስላምዊ ስርዓት የጎደለዉ የጨዋነት ወጉን ያልጠበቀ አለባበስ ለብሰሽ ወጥተሽ ሌላም ሴት ያንችን ጎዳና የተከተለች እንደሆነ እስከ ዕለተ ትንሳሄ ድረስ አንችን የሚከተሉ ሴቶች ሁሉ ወንጀል እንዳለብሽ አትዘንጊ ይህ በእርግጥም ትልቅ ጥፋት ነዉ አደራሽን እህት…የመልካም ነገር እንጂ የወንጀል ተከታይ ከማፍራት ተቆጠቢ።
ይቀጥላል →→ → ክፍል ②
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
`·. https://t.me/joinchat/AAAAAE6HtHNiEljTsdd57w
•════•••🍃🌺🍃•••════•