ሀድራ ብቻ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


✡✿በአላህ መንገድ ላይ አትለያዪ✿✡
ፍላጎታችን ጀነት ነው፡፡♥♥♥♥
👉 ኢሽቅ/መንዙማዎች ✔
👉 የሱሃቦች ታሪክ✔
👉 አዳዲሰ መረጃዎች✔
👉 የረሱል [ሰ.አ.ወ ]ምርጥ ስራዎችና ባህሪያቸው.....፡፡
፡፡፡፡ ፡፡፡ኢንሻአላህ ♥ ምርጡን ነገር እናቀርባለን፡፡✡
✔ጥያቄ ወይም አስተያየት ካላቹ ✔
@yabedretemama_bot
@Temu_Na

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




ለወሬ ቦታ አንስጥ


جاء رجل لخالد بن الوليد رضي الله عنه فقال له إن فلانا شتمك .. فقال: تلك صحيفته فليملأها بماشاء
አንድ ሰው ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ጋር መጣና እከሌ ሰድቦሀል አለው...
ይህቺ የስራ ሰሌዳው ነች በፈለገው ይሙላት አለው።
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
قال رجل لوهب بن منبه رحمه الله: إن فلانا شتمك .. قال: أما وجد الشيطان رسولا غيرك.

አንድ ሰው ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ዘንድ መጣና፦
እከሌ ሰድቦሀል አለው… ሸይጧን ካንተ ውጭ ሌላ የሚልከው መልእክተኛ አጣዴ አለው።
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
قال أحدهم لرجل .. فلان شتمك فقال: هو رماني بسهم ، ولم يصبني فلماذا حملت السهم وغرسته في قلبي.

አንድ ሰው መጣና ለአንዱ እከሌ ሰድቦሀል ሲል ነገረው…
እሱ ቀስቱን ወደኔ ወረወረው ነገር ግን ቀስቱ አላገኘኝም ነበር ለምን አንተ ቀስቱን አምጥተህ ልቤ ላይ ትተክለዋለህ ትወጋኛለህ? አለው።
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
جاء رجل إلى الشافعي رحمه الله: فقال له فلان يذكرك بسوء .. فأجابه: إذا صدقت فأنت نمام ، وإذا كذبت فأنت فاسق.
فخجل وانصرف.

አንድ ሰው ኢማም አሻፊኢ ዘንድ መጣና እከሌ በመጥፎ ያነሳሀል አላቸው…እውነትህን ከሆነ አንተ ወሬ አመላላሽ(አቃጣሪ)ነህ ዋሽተህ ከሆነ ፋሲቅ ነህ አሉት።
ሰውዬውም አፍሮ ሄደ።
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
أقول
لا تخبرني عمن يكرهني أو يتكلم عني .. اتركني أضحك وأضحك مع الجميع وأشعر أن الجميع يحبني، ولنترك القيل والقال .. فرسول الأمة يقول لا تنقلوا لي شئ عن أصحابي ، فإنني أحب أن أخرج إليهم وأنا سليم الصدر

እኔን በመጥፎ ስለሚያነሳኝ ሰው አትንገረኝ ከሁሉም ጋር በፈገግታ እኖር ዘንድ ተወኝ ሁሉም እኔን እንደሚወደኝ እያወኩ ልኑር።

➡አለ ....ተባለን ...ከማውራት እንቆጠብ።

ነብዩ ﷺ ስለባልደረቦቼ ነገሮችን እያመጣችሁ አትንገሩኝ እኔ ከነሱ ጋር ጥሩ ልብ ይዤ መውጣት መቀላቀል እፈልጋለሁ ብለዋል
https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM










አንድ ትልቅ ዐሊም ነበሩ ከደረሶቻቸው ጋር መንገድ ላይ ሳሉ አንድ ኸምር የያዘ ሰካራም መንገድ ላይ ያገኛሉ ።
#ሰካራሙ " አላህ ቻይ አይደለምን"اليس الله قادر አላቸው
#ዐሊሙ "አዎ አላህ ቻይ ነው "نعم الله قدر
#ሰካራሙ 2ኛ ጊዜ" አላህ ቻይ አይደለምን"اليس الله قادر አላቸው
#ዐሊሙ "አዎ አላህ ቻይ ነው "نعم الله قدر አሉት
#ሰካራሙ 3ኛ ጊዜ" አላህ ቻይ አይደለምን"اليس الله قادر አላቸው
#ዐሊሙ "አዎ አላህ ቻይ ነው "نعم الله قدر አሉት እና እያለቀሱ ወደቁ በዛው ራሳቸውን ሳቱ።

ከደቂቃዎች በኋላ ሲነቁ ደረሶቹ ምን እንደሆኑ ጠየቋቸው ከዛም ዐሊሙ እንዲህ አሉ:-
#በመጀመሪያ አላህ ቻይ አይደለም ወይ ያለኝ አላህ እኔን ኸምር ሊያስተወኝ አይችልም ወይ ነው ያለኝ አዎ አላህ ቻይ ነው አልኩት።
#በሁለኛው አላህ ቻይ አይደለም ያለኝ አላህ እኔን እንዳንተ ዐሊም ሊያደርገኝ አይችልም ሲለኝ አዎ አላህ ቻይ ነው አልኩት።
#በሶስተኛው አላህ ቻይ አይደለም ያለኝ አላህ አንተን እንደ እኔ ኸምር ጠጪ ማድረግ አይችልም ወይ ሲለኝ አዎ አላህ ቻይ ነው ብዬ ራሴን ሳትኩ አሏቸው።

ዛሬ አንተ ያለህበትን የኢማን ቦታ አይተህ ሌሎችን ዝቅ አታድርግ አትሳደብ መጨረሻ ላይ ማን በዲኑ ላይ እንደሚሞት አታውቅምና

ሰይዳችን ሶለሏሁ.ዐለይሂ.ወሰለም ስራ ሚለካው በመጨረሻ ነው ብለዋል። ሁሌም አላህ በሰጠህ ኒዕማ እያመሰገንክ ኑር እንዳይወሰድብህ ዚያዳ እንዲኖረው።

#አሏህ ኻቲማችንን ያሳምርልን

https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM










ሰረፈ ሰላም በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በሩቃ እና በማሸት ስም የተለያዩ አስነዋሪ ተግባራት ሲፈፅም እንደ ነበረ ዑለሞች በምስክሮች ያረጋገጡበት አቶ ሚስባህ ከማል ከዚህ በኋላ መሰል ተግባራት እንዳይፈፅም ፈፅሞ ከተገኘም በህግ እንደሚከሰስ ፌደራል መጅሊሱ የፃፈው ደብዳቤ ይገልፃል። ይህ ግለሰብ ፈፀማቸው የሚባሉ ተግባራት እጅግ የሚሰቀጥጡ ናቸው። ምንም እንኳ አጀማመሩ የተጎዱ ስፖርተኞችን ወጌሻ በመሆን ማከም የጀመረ ቢሆንም ቀስ እያለ መድሃኒት ወደ መስጠትና ወጣ ባለ መንገድ ሩቃ ወደ መስጠት ተሸጋግሮ በስተመጨረሻ ወደ ጥንቆላው ዓለም እንደተቀላቀለ ዑለማዎቹ ጉዳዩን ለማጣራት በሄዱበት መንገድ ማረጋገጥ ችለዋል።

ሰዎች ኸይር የሰሩ እየመሰላቸው ከጅኖች ጋር መነጋገርና ማድረግ ይጀምሩና የጂን ዓለም ደግሞ ካልገበርክለትና አምልኮ ካልፈፀምክለት ስለማይታዘዝ ቀስ በቀስ ወደ ሽርክ ወደ ጥንቆላ ዓለም ይዘውት ይዘልቃሉ። ለዚህም ነው ከጅን ጋር የሚያቀራርቡ ነገሮች ፈፅሞ እርም ተደርገው የሚታዩት። በቁርአን እንደ ተገለፀው ሸይጧን ጅን ነው። ሸይጧን ደግሞ እንዴት እራሱን ቀያይሮ የሰውን ልጅ ለማጥመም እንደሚሰራ የታወቀ ነው። ሙስሊም ጅን ጋር ነው የማወራው እያለ ሸይጧንን ጓደኛው አድርጎ ከእስልምና ሊያስወጣው ይችላል። ከጅን ጋር ማውራት ትልቅ እውቀት አይደለም። ብዙ ሰዎች ከጅን ጋር ማውራት ብርቅ ስለሚመስላቸው የተለየ ጀብድ የፈፀሙ ይመስላቸውና ሳያስቡት ወደ ሽርክ ዓለም ሰምጠው ይገባሉ።

#ሼር #ሼር  #ሼር
#sher #sher  #sher
ያድርጉ
https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM






قَالَ ﷺ: «البَخِيْلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ»

ታላቁ ነብዬ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው»

ምንም ያህል ብናወድሳቸው ምንም ያህል ብንወዳቸው ከሁሉ ነገር በላይ ከ ነፍሳችን በላይ ብንወዳቸውም ለሳቸው በጣም በጣም ያንሳቸዋል ወላሂ።

ያለፉት የአላህ ደጋጎች የ አላህ ወልዮች ሲናገሩ እኮ "ጀነትን የምንናፍቀው ሰይዳችን ሲላሉበት ነው" ይላሉ
አያቹ ጀነት እንኳን ማማረዋ እና መለምለሟ በ ሰዪዳችን ነው።

ረሱልን ማወደስ ላይ እንበርታ
https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM






ሀቢቢ ላሂ መህቡቢ ረቢ
አል ሺሚዩል አረቢ

ሸህ አብዱል ወሀብ

ከሚስ ሙባረክ💚
@yemuhabawzulal




Mawulid standared.pdf
1.7Mb
❤️መውለድ በኡስታዝ ሀሰን ታጁ
💚የረቢዕ ስጦታዬ ነው አንብቡት ለነ ፉላንም አሳዩልኝ
https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM
https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM

20 last posts shown.

141

subscribers
Channel statistics