📞#እስቲ_ፈልጉልኝ_ያን_ታማኝ_ጓደኛ🌄
ከመልካም ቤተሰብ ከሷሊህ የወጣ፣
በፍቅር በእዝነት የኖረ ባ በባ፣
አላህ በወደደው ማእረግ የገባ፣
በአግባብ ተኮትኩቶ ምግባሩ ያማረ፣
አላህን በመፍራት ለአላህ ያደረ፣
በተውሂድ ሰንሰለት ልቡ የታሰረ፣
የሰለፉን ሷሊህ መንገድን የያዘ፣
በሱናዋ መስመር ቆሞ የተጓዘ፣
ከሽርክያት ሰፈር ርቆ የኖረ፣
ከቢድኣ ወጥመድ እራሱን ያዳነ፣
ከጥመት አንጃዎች ነፍሱን ያገለለ፣
ሁሌዬ ለአሄራው ቀን ከሌት የቆመ፣
ዱኒያን ትወት አርጎ ነፍሱን ያሸነፈ፣
ስሜት ሳይከተል በደሊል ያመነ፣
ካለ ውድ ወንድሜ ለልቤ መፅናኛ፣
እስቲ ፈልጉልኝ ያን ታማኝ ጓደኛ??
ታማኟን እህቴን የእውነት ሰለፍዯን፣
አፋልጉኝ በእውነት ቀና ላርግ አንገቴን።
አወ
በሂጇቧ ደምቃ
በኒቃብ ተውባ
በሀያዕ ዋ ሰምራ
በሚስጥር ካባዋ
አላህን አድርጋ
ያለች እንቁ እንስት ታማኝ ባልንጀራ፣
አፋልጉኝ በአላህ ትኖራለችና።
የተውሂድ ካባዋን በእምነት ገንብታ
ሱናዋን በቲባእ በኢኽላስ አስውባ፣
አላህን በመፍራት እንባዋን አንብታ፣
ለወንድም አዛኟን አፋልጉኝ በአንድ አፍታ።
አወ
አላህን የፈራ፣
ታምኖ የማይከዳ፣
ለወንድም የሚያስብ በሸሪእ ጎዳና፣
አፋልጉኝ ይኖራል ገጠር ከከተማ።
ከጅሀነም እሳት የሚያስጠነቅቀኝ፣
ጀነትን በብስራት ተስፋ የሚሰጠኝ፣
ከወንጀል ታቅቦ እኔን የሚያድነኝ፣
በመልካም ስራ ላይ የሚያበረታታኝ፣
ወደ ተውሂድ መስመር ወስዶ የሚያደርሰኝ፣
በሱና ላይ ቆሞ እኔን የሚያፀናኝ፣
ፈልጉልኝ በጣም የጓደኛ ታማኝ።
✍ አቡ ተቅይ ቃዒድ
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel
ከመልካም ቤተሰብ ከሷሊህ የወጣ፣
በፍቅር በእዝነት የኖረ ባ በባ፣
አላህ በወደደው ማእረግ የገባ፣
በአግባብ ተኮትኩቶ ምግባሩ ያማረ፣
አላህን በመፍራት ለአላህ ያደረ፣
በተውሂድ ሰንሰለት ልቡ የታሰረ፣
የሰለፉን ሷሊህ መንገድን የያዘ፣
በሱናዋ መስመር ቆሞ የተጓዘ፣
ከሽርክያት ሰፈር ርቆ የኖረ፣
ከቢድኣ ወጥመድ እራሱን ያዳነ፣
ከጥመት አንጃዎች ነፍሱን ያገለለ፣
ሁሌዬ ለአሄራው ቀን ከሌት የቆመ፣
ዱኒያን ትወት አርጎ ነፍሱን ያሸነፈ፣
ስሜት ሳይከተል በደሊል ያመነ፣
ካለ ውድ ወንድሜ ለልቤ መፅናኛ፣
እስቲ ፈልጉልኝ ያን ታማኝ ጓደኛ??
ታማኟን እህቴን የእውነት ሰለፍዯን፣
አፋልጉኝ በእውነት ቀና ላርግ አንገቴን።
አወ
በሂጇቧ ደምቃ
በኒቃብ ተውባ
በሀያዕ ዋ ሰምራ
በሚስጥር ካባዋ
አላህን አድርጋ
ያለች እንቁ እንስት ታማኝ ባልንጀራ፣
አፋልጉኝ በአላህ ትኖራለችና።
የተውሂድ ካባዋን በእምነት ገንብታ
ሱናዋን በቲባእ በኢኽላስ አስውባ፣
አላህን በመፍራት እንባዋን አንብታ፣
ለወንድም አዛኟን አፋልጉኝ በአንድ አፍታ።
አወ
አላህን የፈራ፣
ታምኖ የማይከዳ፣
ለወንድም የሚያስብ በሸሪእ ጎዳና፣
አፋልጉኝ ይኖራል ገጠር ከከተማ።
ከጅሀነም እሳት የሚያስጠነቅቀኝ፣
ጀነትን በብስራት ተስፋ የሚሰጠኝ፣
ከወንጀል ታቅቦ እኔን የሚያድነኝ፣
በመልካም ስራ ላይ የሚያበረታታኝ፣
ወደ ተውሂድ መስመር ወስዶ የሚያደርሰኝ፣
በሱና ላይ ቆሞ እኔን የሚያፀናኝ፣
ፈልጉልኝ በጣም የጓደኛ ታማኝ።
✍ አቡ ተቅይ ቃዒድ
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel