Forward from: ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ
አላማውቄን የት ሄጄ ልክሠሣት ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፍረዱኝ ጠቁሙኝ ቦታ ካወቃችሁ፣
ጅህልናን ሣልከሣት አልቀርም ባካችሁ።
ብዙ በድላለች ካሣ ትከፍላለች ፣
አለቃትም ነበር ውስጤን አቃጥላለች።
አለማወቄ እንጂ ኃላ የጎተተኝ፣
እውቀት ብርሀኑ የት ነበር ሚያደርሠኝ፣
በወንጀል ከማመፅ ብዙ በቆጠበኝ፣
አላህን በእጅጉ በደንብ ባስታወቀኝ።
የጌታችን ፍቅር ሁሉንም ይስባል ፣
በታወቀ ቁጥር ሁኔታው ያስፈራል፣
የእዝነቱ ነገር ልብን ያሸንፋል።
እንኳን ሊታመጽ ትዛዙ ተጥሶ፣
ምርኮኛ ያረጋል በውስጣችን ነገሶ።
ነብሴ ምቀኛዋ ሁሌም የምፈራት፣
ከሸይጣን ጉትጎታ እንዴትስ ላርቃት።
ቀን ማታ ስትወጥር በመጥፎ ጉንተላ ፣
በዚክር እስቲግፋር ለማለትም ችላ ።
ጥረቴን አደረኩ በጌታ እርዳታ፣
ሁሌ ትመኛለች የማይሆን ዛዛታ፣
ዝቅ ልታረገኝ ከአማኞች ተርታ፣
ስኬቴን ልቀማኝ ማግኛዬን እርካታ።
ገፍላ ልሆንላት ጌታዬን የረሣሁ፣
እቅዷን ላከሽፍ ካሁኑ ተነሣሁ።
ከጠላቴ ሼይጣን ወዳጅነት ወዳ፣
ተነሳች እሷማ እኔኑ ልትጎዳ።
አላህ ካለጠበቀኝ ከመጥፎ ወጥመዷ፣
እኔ ወዳቂ ነኝ ሂያጅም መንገዷ።
ያረቢ ጠብቀኝ ከነብስያ ተንኮል፣
ባንተ የተመካ እኮ መቼ ያፍራል፣
ልቤ ባንተ ሁሌም ተመክቷል።
ከአሄራ እህቴ A.A
http://t.me/AbuTeqiyPomeChannel
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፍረዱኝ ጠቁሙኝ ቦታ ካወቃችሁ፣
ጅህልናን ሣልከሣት አልቀርም ባካችሁ።
ብዙ በድላለች ካሣ ትከፍላለች ፣
አለቃትም ነበር ውስጤን አቃጥላለች።
አለማወቄ እንጂ ኃላ የጎተተኝ፣
እውቀት ብርሀኑ የት ነበር ሚያደርሠኝ፣
በወንጀል ከማመፅ ብዙ በቆጠበኝ፣
አላህን በእጅጉ በደንብ ባስታወቀኝ።
የጌታችን ፍቅር ሁሉንም ይስባል ፣
በታወቀ ቁጥር ሁኔታው ያስፈራል፣
የእዝነቱ ነገር ልብን ያሸንፋል።
እንኳን ሊታመጽ ትዛዙ ተጥሶ፣
ምርኮኛ ያረጋል በውስጣችን ነገሶ።
ነብሴ ምቀኛዋ ሁሌም የምፈራት፣
ከሸይጣን ጉትጎታ እንዴትስ ላርቃት።
ቀን ማታ ስትወጥር በመጥፎ ጉንተላ ፣
በዚክር እስቲግፋር ለማለትም ችላ ።
ጥረቴን አደረኩ በጌታ እርዳታ፣
ሁሌ ትመኛለች የማይሆን ዛዛታ፣
ዝቅ ልታረገኝ ከአማኞች ተርታ፣
ስኬቴን ልቀማኝ ማግኛዬን እርካታ።
ገፍላ ልሆንላት ጌታዬን የረሣሁ፣
እቅዷን ላከሽፍ ካሁኑ ተነሣሁ።
ከጠላቴ ሼይጣን ወዳጅነት ወዳ፣
ተነሳች እሷማ እኔኑ ልትጎዳ።
አላህ ካለጠበቀኝ ከመጥፎ ወጥመዷ፣
እኔ ወዳቂ ነኝ ሂያጅም መንገዷ።
ያረቢ ጠብቀኝ ከነብስያ ተንኮል፣
ባንተ የተመካ እኮ መቼ ያፍራል፣
ልቤ ባንተ ሁሌም ተመክቷል።
ከአሄራ እህቴ A.A
http://t.me/AbuTeqiyPomeChannel