አዳም ረታ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ቀንዎትን ያሳምሩ
👉ግጥሞች
👉የአማርኛ መፅሀፍት በ pdf
👉ቀልዶች
👉አስተማሪ ና አዝናኝ ፅሁፎች
👉የአዳም ረታ እና ሌሎችም እውቅ ደራሲያን ስራዎች
👉ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የምትፈልጓቸውን አንድ ላይ በ አዳም ረታ ያግኙ።
@AdamuReta
@AdamuReta
@AdamuReta

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#አዳም_ረታ

#ፀጥታ_ነጋሲ......

ይኼ አብዛኛው የምንኖርበት አለም ፀጥታ ነው። ያልተነገረለት ነው። ሆሄ፣ቃል፣ አንቀጽ ፣ምዕራፎች ፣ቅዳሴና ዘፈን ፣እንጉርጉሮና ምንትስ አልተነዳበትም የሚባል ። ምድር ላይ ከተሰሩና ከተደረጉ ከታሰቡና ከታለሙ ነገሮች የተመዘገበው ስንቱ ነው? የአዳም የመጀመሪያው ሳቁ ተመዝግቧል? የመጀመሪያው የአዳም ወይ የሔዋን እንጉርጉሮ ይታወሳል? የሐጢያት መጀመሪያ የተባለችው በለስ የተበላችበትን ጊዜ ፣ ሰዐትና ደቂቃ የሚያውቅ አለ?......

ሙሴ ቀይ ባሕርን ሊሻገር ሲል ያን ያህል የውሐ ብዛት አይቶ ስለማያውቅ ሽንቱን ደጋግሞ በመሽናቱ የተበሳጨው ወንድሙ ኢያሱ ' ይኼ ተብታባ ምን ሆነ? መንገዱን ገና ሳናጋምስ ፊኛውን ታመመ እንዴ? ' ብሎ መናገሩን ማን መዘገበ? ሙሴ ይሄን ሰምቶ ያዙኝ ልቀቁኝ ' ይሄን ምላሳም ካልደበደብኩ' ማለቱስ?.......

... ናምሩድ አፉን የፈታበት ቋንቋ ምን ነበር? ሰለሞን ንግስት ሳባን ኦፊር ምድር እንሰት ኮባ ስር የደበቀቻትን ድንግልና እንደ ተራ የሊባኖስ በለስ አልጋው ላይ ስትጥልለት ድንቁርናዋና ልጅነቷ አስገርሞት እየሳማት ፡ " የእኔ ጅል ያን ሁሉ የተጓዝሽው ለዚህ ነው?" ማለቱን ክብረነገስት መዝግቦታል? ሳባስ እብራይስጥ ባለማወቋ እንደተተረበች ሳይገባት መሞቷን እናውቃለን?....

አዘጋጅ @isrik

@AdamuReta
@isrik

#እቴሜቴ_ሎሚሽታ


ዛሬ በትንንሽ ምሬት ይሞላና ጊዜ ይለወጣል።

ምንም የረባ ሳይደረግ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ይራራቃሉ፣

የተያያዙ ይፈታታሉ፣

ፍቅር የገመዳቸው ይበታተናሉ።

ሁሌም ሚስጥር ነው።

ለምን እንደወደድንም ለምን እንዳልወደድንም ሚስጥር ነው።

***
#እቴሜቴ_ሎሚ_ሽታ

@AdamuReta
@isrik
@isrik
@AdamuReta


📖 #አዳም_ረታ 📖

#የማያልቅ_ስጦታ

የካብኩት እየተናደ
የገመድኩትም ሲበጠስ
ያደመቅኩት እየፈዘዘ
ያነጽኩት ሁሉ ሲፈርስ
ደመናው ፀሐይ ሆኖብኝ
በመንገዴ እየተሰጣሁ
ከእንስራው ውሃ ጠፍቶ
ላቤን ከጉንጬ እየጠጣሁ
የበደሉኝን ይቅር ለማለት
ራሴን በራስ እየቀጣሁ
“ማነው?” ስባል “እኔ” የምል
የሰው ጥፋት የምሸከም
በኔ ይለፍ የምዘምር
እስክጠፋ የማልደክም
ሳይታሰብ እንደ መና
ከላይ ወርዶ የሚያወፍር
ስላለኝ ነው ታላቅ እውነት
ስላለኝ ነው አንዳች ክብር
ያንቺ ፍቅር...!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘

#ልክ_በዛሬው_ቀን...

አበባ ባልሰጥሽ ለራት ባልቀጥርሽም
#የኔ_ወድሻለሁ
ባለሽበት ሆነሽ ባለሁበት ሆኜ
አብረን እንደሆንን ራሴን አሳምኜ
እራት እበላለሁ እራትሽን ብይ
ስጦታሽን እንቺ አበባሽን እይ

#የኔ_ወድሻለሁ...
ያለንበት ቦታ ለስላሳ ሙዚቃ
ሰማሽው አይደለ ላንቺ ይሁን በቃ
አውቃለሁ የኔ ሴት አውቃለሁ የኔ ዓለም
ቀይ መጸሀፍ እንጂ ቀይ ልብስ አትወጂም
ለራት የለበስሽው...
ሰማያዊ ቀሚስ ነጭ እስካርፍ ያለበት
ይሁን ደስ ብሎኛል ደምቀሽ እመሪበት

#የኔ_ወድሻለሁ...
ዘና በይ ፈገግ በይ
ባለሁበት ሆኜ ባለሽበት ሆነሽ
ብቸኝነት የለም የኔ ሆይ ልንገርሽ
ያሳቤን ስጦታ በይ አሁን ክፈቺው
አየሽው... ?
ወደድሽው... ?
የልቤ ትንፋሽ ነው በልብሽ ተንፍሺው

#የኔ_ወድሻለሁ!!!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik


ያንተ ተስፋ ማነው?!

እንደ አንተ ጭንቀትና ሀሳብ ቢሆን ዛሬን ማየት የማይታሰብ ነበር፤ ያንን ጊዜ ማለፍ ቅዠት ነበር፤ ግን አለፍከው፤ ያልገመትከው ሁሉ ሆነ አንተ ተስፋ ቆርጠህ ስትጨርስ ፈጣሪ ጀመረ። ያንተ ተስፋ የዚህ አለም ተለዋዋጭ ነገር አይደለም! ያንተ ተስፋ የማይለወጠው፣ በዘመናት የማያረጀውና የማያልፈው ፈጣሪህ ነው!

አስደሳች ጁምአ (አርብ) ተመኘንላችሁ🙏
@AdamuReta
@isrik
@Reta
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!


📖 #አዳም_ረታ 📖

"ስማ.. .ስማ.. .!"
ዞር አልኩኝ። ለ ሰባት ዓመታት በግዳጅ የቆየ ወታደሩ የሰፈሬ ልጅ ነው ። አጎንብሶ ስለነበር አይቼው ልደበቅ አልቻልኩም ። ኩሪ ሰፈራችን መሀንዲስ ውስጥ ከገባበት ቀን ጀምሮ ትዕቢተኛ ውሪዎችን አደብ ስላሲያዘልን እወደዋለሁ። ገና መቀመጫቸውን በቅጡ ሳይጠርጉ ቺክ ለመጥበስ ተፍ ተፍ የሚሉ...ሞተር ሲነዱ ቆሌያችንን የሚገፉ ታደጊዎችን የእጃቸውን ይሰጥልናል።
እሱ እጅ የገባ ፍንዳታ ታዳጊ በጠረባ አየር ላይ ደንሶ ይመለሳል።
ይሁንና በዚህ ተግባሩ ብወደውም ብዙ ጊዜ ብር ስለሚለምነኝ ግን በሩቅ ሳየው ገና እደበቅበት ነበር። ለሶስት ጊዜ ያህል ገንዘብ ጠይቆኝ በአሉታ ስለመለስኩለት ቂም ቆርጭሞብኛል።
ሰሜን እዝ ውስጥ ዓመታትን አስቆጥሯል። ብልግና.. .ማነው ይቅርታ ብልፅግና መንግስት ኢትዮጵያንና ኤርትራን ሲያዋህድ የተፈጠረውን ነገር ያጫወተኝ ቅፅበት አትረሳኝም።
የደስ ደስ ተብሎ ወታደሩ በገፍ ቢራ ቀርቦለት ተፍታታ...የኢትዮ ወታደር ወደ ውሀው ጠንከር ይላልና የቢራ ጠርሙሶችን እንደ ቁልፍ አቅጨለጨላቸው።
የኤርትራ ወታደር ሁለት ቢራ ልፈው ፀጥ እረጭ ሆነ ነገሩ...
የወገን ጦር "እነዚህ ሰዎች ተታርቀንም ሌላ ጉድ ሊያመጡ ነው እንዴ?" ብለው ተጠራጠሩና "ጠጡ እንጅ " አሏቸው በግብዣ መልክ ...
የኤርትራ ወታደሮች ይሄን ጊዜ ነው ...
"ኢትዮጵያ ውስጥ ከሁለት በላይ መጠጣት ይቻላል ወይ ?🤔" ብለው የተገረሙት ።
ኤርትራ ሁለት መሎቲህን ልፈህ ሌላ ቢራ ሊጨምር ካልክ የኢሳያስ መንግስት ጉድጓድ ይጨምርሀል ።
ኤርትራ በመዓቀብ ብዛት ከዘመነኛ ስልጣኔ በትንሹም ቢሆን ተኳርፋለች።
እንደውም ሀሜት አይሁንብኝና የ ATM ማሽን ሲያዩ ብርቅ ሆኖባቸው ሰልፊ የተነሱም ጓዶች አሉ ተብሎ ይወራል 🙄
እዚህ ሸገር ቤተልና 22 የሚገኙ ኤርትራውያን ተዝናኖትን የማይጠግቡበት ምክንያት ይሄ ነው።
አንድ የኤርትራ ወጣት ጀማ ሺሻ ሲነፋ ካያችሁ ጎጆ ቤት የተቃጠለ ሊመስላችሁ ይችላል ።
ደግሞ ጨላ በሽ አላቸው... አሸን ዲያስፖራ በሚልክላቸው ብር ውስኪ ውስጥ ዋኝተን ዛሬውኑ ሻርክ ካልሆንን ይላሉ ። ሀያ ሁለት ሰፈር ኤርትራውያን ሲገቡ ቤት ኪራይ ደመና ልሶ ይመለሳል። የክብሪት ቀፎ የምታክል ክፍል ስድስት ሺህ ብር ለመከራየት እጃቸውን ወደ ኪሳቸው ቀለል አድርገው ነው የሚጨምሩት ።
"ወዬ"
"ወደየት እየሄድክ ነው?"
"ቢሮ "
ፈገግ አለ ...
"ይሄ ኮብልስቶን እንዲህ ፈራርሶ ስታይ ምንም አይሰማህም ? ካሁን በኅላ መኪና በዚህ እንዳያልፍ ድንጋይ እንደርድር "
ትዕዛዙ እንደ ሞዴሊስት ወገብ ቀጠን ያለች ነች። ታናሼ ነው... ታናሼ ነው ብዬ ትዕዛዙን አልንቅ ነገር በዚህ የጅብ ግራ እግር በሚያህል ክንዱ ያደባየኛል 😑
ሸሚዜን ሰብስቤ ድንጋይ መደርደር ጀመርኩ ... ከደቂቃዎች በኋላ ሰዓት እንደረፈደብኝ በምልክት ሳሳየው የፊቱን ሌላ መልክ ገልብጦ አሳየኝ።
እግዚኦ ማስፈራቱ !
ድንጋይ ማጋዜን ቀጠልኩ ። ከሰዓታት በኋላ ቢሮ የደረስኩት ወፍጮ ቤት የተቀጠረ ፈጪታ መስዬ ነበር ።
እንደውም ፊትለፊት የምትቀመጠው ፀሀፊያችን አቧራዬን አይታ "ሳላስብ ፀልዬ የሚለው የያሬድ ነጉ ቀረፃ ላይ ነበርክ እንዴ? የዱባይ አሸዋ መስለካል" ብላ ተላላጠችብኝ።😐
ኩሪ ሰፈር ውስጥ ስለሚውል እንከን ማውጣት አይታክተውም...እኔ ወራትን የተመላለስኩበት መንገድ ኮብልስቶን መንገድ እንደሆነ እንኳ ልብ ያልኩት "የኮብልስቶኑ መፍረስ አይታይህም ወይ?" ብሎ ሲያንባርቅብኝ ነው።
በዛ ላይ ሰፈር ውስጥ ያለ ለቅሶና ሰርግ ላይ በማገልገል ማንም አይደርስበትም...ድንኳኑን ብቻዬን ካልተከልኩት ነው የሚለው !
በየቀኑ ሰፈር በመጣሁ ቁጥር አዳዲስ ነገሮች ይገጥሙኛል ።
ችጋር ያራቆታቸው ደራቃ ተክሎች ሁሉ ውሀ ጠገቡ... ጭራሽ የሰፈራችን ውሪዎች ጋሽ አበራ ሞላ ሆኑብን...መንደሩ እንደመስታወት ያንፀባርቃል።
...
ዛድያ እኔም አመሻሽ ላይ ድንጋይ ሸከማውና የቢሮው ስራ የመጠጠው ጉልበቴን ለማሳረፍ ወደ ቤቴ ከነፍኩ ።
ሆኖም ቀዬ ስደርስ እነዛ ነገረኛ ሽማግሌ ሌባ ጣታቸውን ጠቆሙብኝ። ሰፈሩ በፖሊስና ደንቦች ተወሯል። CCTV ካሜራ ሆነው ወሬ የማያመልጣቸው ባልቴቶች ወገባቸውን ይዘው "ቀ" ፊደልን መስለዋል።
አንድ ብጉራም ፖሊስ ዱላውን አንጠልጥሎ ወደኔ ተንደረደረ ...
"ምንድነው?"
አንዴ ወገቤን ነርቶ አንቆራጠጠኝ ።
"እንዴ በህግ አምላክ !"
"እናንተም ህግ ታውቃላችሁ እንዴ? እስክንድር ነጋ መንገድ እንድዘጉ ያሰማራህ ፋኖ እንደሆንክ ደርሼበታለሁ "
በድንጋጤ አይኖቼ ፈጠጡ ...
ኩሪ ደረቱን ነፍቶ ከፖሊሶቹ ጋር ተጠጋኝ ።
" ስማ መንግስት በአንካሴ የሚሄድ አካል ጉዳተኛ መሰለህ እንዴ? መንገድ በድንጋይ በመዝጋት የሚወርድ መንግስት የለም እሺ?"
ይሄን የሚያወራው ጠዋት ድንጋይ እንደርድር ብሎ ያዘዘኝ ኩሪ መሆኑን በመጠራጠር አይኖቼ ደጋግሜ አሻሸኋቸው 🙂

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik

#Mikael aschenaki


የካቲት ወር በኢትዮጵያ
━━━━✦❁✦━━━━
አገራችን ኢትዮጵያ ካስተናገደቻቸው እና የወደፊት እጣ ፈንታዋን ከወሰኑ የታሪክ ክስተቶች ውስጥ የካቲት ወር ትልቅ ድርሻ አለው።
👇
በ1888 ዓ.ም. አገራችንን ቅኝ ለመግዛት ቋምጦ የመጣውን ወራሪውን የጣሊያን ጦር አያት ቅድመ አያቶቻችን አድዋ ላይ የደመሰሱት በዚህ በያዝነው የየካቲት ወር፤ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም.ነበር። እነሆ ዛሬ አባቶቻችን በደምና በአጥንት በከፈሉት መስዋዕትነት እና ባስመዘገቡት አኩሪ ድል እኛ አንገታችንን ቀና አድርገን የነጻነት ሳይሆን የድል በዓልን እናከብራለን።
👇
በ1969 ዓ.ም. የዚያድ ባሬ ሶማሊያ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ 700 ኪ.ሜ. ያህል ወደ ውስጥ ዘልቆ ነበር ። ታዲያ በጊዜው በመንግሥት ለውጥ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ ይህን ወራሪ ኃይል ለመመከት በቂና የተዘጋጀ ሰራዊትና የጦር መሳሪያ ባይኖራትም ነጻነቷን ግን አሳልፋ አልሰጠችም። በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ 300,000 ወታደር አሰልጥና ሶማሊያን ድል ስታደርግ ወርቃማው ድል የተመዘገበው የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም. ካራማራ ላይ ነበር።
👇
ፋሺስት ኢጣሊያ ከ1927 እስከ 1933 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት ኢትዮጵያን በወረራ ይዞ ቆይቷል። በተለያዩ መንገዶች በጣሊያን ጦር ላይ ጉዳት ለማድረስ ከተደረጉ ሙከራዎች አንዱ የፋሺስቱ እንደራሴ ሮዶልፎ ግራዚያኒን በቦምብ ለመግደል የተደረገው ነው። የግድያ ሙከራው ሲከሽፍ በግራዚያኒ ትዕዛዝ በአዲስ አበባ ላይ መዓት ዘነበባት። ቤቶች ከነነዋሪዎቻቸው እየተዘጉ ተቃጠሉ። በየመንገዱ የተገኘ ሰው እንደ በግ እየተጎተተ ታረደ። በሦስት ቀናት ጭፍጨፋ በአዲስ አበባ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በግፍ የተጨፈጨፉት በዚሁ ወር የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ነበር።
👇
የመጨረሻውን የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት ንጉሠ ነገሥት የአጼ ኃይለ ሥላሴን መንበር የነቀነቀውና ከስልጣን ያወረደው አብዮትም የተቀጣጠለው በዚሁ በየካቲት ወር ነበር። የካቲት 1966 ዓ.ም.።
👇
አጼ ሰርጸ ድንግል፣ አጼ ቴዎድሮስና ንግሥት ዘውዲቱን የመሳሰሉ ነገሥታት የነገሱት በየካቲት ወር ውስጥ ነበር። ከታላላቅ ጦረኞች እና ስመ ጥር የፖለቲካ ሰዎች መካከል ግራኝ አህመድ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው እና ራስ አሉላ እንግዳን የመሳሰሉት በሥጋ ከዚህ ዓለም ያረፉበት ወርም ነው። የካቲት!
👇
የካቲት ወር ብዙ የስነ-ፅሁፍ ኮከቦቻችንን ያጣንበት ወርም ነው። አቤ ጉበኛ የካቲት 2፣ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር የካቲት 12፣ ጸጋዬ ገብረመድኅን የካቲት 18፣ ማሞ ውድነህ የካቲት 23፣ እንዲሁም ተወዳጁ ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ እንደወጣ የቀረው የካቲት 24 ነበር።
📖 📖 📖 📖 📖

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik
@isrik


እንኳን ለ 126ኛው የአድዋ ድል በዐል በሰላም አደረሳችሁ

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik


"ስለ አብርሆት ቤተ-መፅሐፍ አንዳንድ እውነታዎች!"

🏢 አዲሱ ላይብረሪ(አብርሆት) ህንፃው የተገነባው 38,687sqm ስፍራ ላይ ነው።

🏢 15 terabytes የሚሆን የተለያዩ መረጃዎች ይዟል። በሌላ አነጋገር 240,000 eBooks ይዟል።

🏢 በዚህ ላይብረሪ ውስጥ የተገነባው መፅሐፍ መደርደሪያ(bookshelf) ወደ ጎን 1.5 km ርዝመት ያለው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ መፅሐፍትን ይይዛል።

🏢 ላይብረሪው በአንድ ግዜ እስከ 3500 ሰዎችን ማስተናገድ ይችላል።

🏢 ላይብረሪው ለህፃናት ተብለው የተሰሩ የማንበብያ ክፍሎች አሉት። በተጨማሪም በላይብረሪው ውስጥ መሰብሰብያ አዳራሽ፣ የትያትር አደራሽ፣ የመፅሐፍ መደብር እና ካፌ ይገኛሉ።

🏢 115 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የፓርኪንግ ስፍራ አለው።

አብርሆት ማለት ምን ማለት ነው?

ጀርመናዊው የፍልስፍና ሊቅ ኢማኑኤል ካንት "አብርሆት ማለት ምን ማለት ነው ተብሎ ሲጠየቅ "እራሳችንን ከገባንበት ድቀት እና ባዶነት ነጻ ማውጣት ነው" ይለናል

🚀ራስን ነጻ ማውጣት

🚀ራስን መገምገም|መተቸት

🚀ራስን መጠየቅ እና መልሱን መፈለግ ነጻ ለመውጣት መተኪያ የሌላቸው መፍትሄዎች ናቸው ብሎም ያክላል!

የሥነ ልቦና ሳይንስ አጥኝዎች ደግሞ አብርሆትን self actualization (ራስን ከዘመን ጋር ማራመድ) ሲሉት፤ ከካንት አተረጓጎም በተለየ መልኩ "Enlightenment" የሚለውን ደግሞ "ንቃት" ብለው ይተረጉሙታል።

ወደፊት ስለ አብርሆት ቤተመፅሐፍት ብዙ የምንላችው ነገር አለን!አብራችሁን ሁኑ

@AdamuReta
@isrik


"ሀገር የምትራመደው በአንድ ሳንቲ ሜትር ዕውቀት፣ በመቶ ሳንቲ ሜትር ስነ-ስርዓት ነው"

#ሕማማትና_በገና

@AdamuReta

Comment👇
( @isrik )


"ገና የሕይወት አቡጊዳን እንደቆረስኩ፣ የታላላቅ አባቶቼን ድርሳን የሰደብኩት እዚህ ነው። ተደነቅሁም። ማነህ ያደነቅኸኝ? ይኼም ባይሆን ልክፍታችንን ይዘን ቅዱስ በቅዠት ጎሣው፣ እኔም በቅዠት ጎሣዬ ወደ ማጥ በድፍረት በቁጣ ገባን። 'ኢንተርናሲዮናል' በጉርምስናዬ ዘምሬ፣ ስለዓለም አንድ መሆን ሰብኬ ብዙ ሳልቆይ የተመረረ መንደረኛ የሆንኩት እዚህ ነው......"

ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik
@isrik


Forward from: የድሮ መፅሀፎች በPDF
አፍ - አዳም ረታ.pdf
23.4Mb
አፍ

ደራሲ - አዳም ረታ

ዘውግ - ልብወለድ

የህትመት ዘመን - 2010

የገፅ ብዛት - 250

አዘጋጅታ ያቀረበችው እህት ፍቅር ነበረች 🥰

ይ🀄️ላ🀄️ሉ @OLDBOOKSPDF


"ገብቶት የታዘበው ነገር ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ከሚመስሉትና ከሚያወሩት አለመጣጣሙ ነው። ብዙ ጊዜ ይሄ ዝም ያሰኘዋል። ደሞም ሰዎች በትንሽ ጉዳይ ሌላውን ሰው ይገምታሉ። ገምተው ትክክል እንደሆኑ ሁሉ ከልባቸው ይረካሉ። ማወቂያ መንገድ ባይኖራቸው አይጠራጠሩም?"

"አፍ"

አዳም ረታ

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik


"ሕይወት በየቀኑ ያለውና የምትኖረው እንጂ፤ ፖለቲከኞች በአጀንዳቸው ውስጥ የሚዘረዝሩት የተስፋ ማስታወቂያ አይደለም።

አንዲት የምትወዳትን ልጅ ማቀፍ ከአንቀፅ አስራ ሶስት ይበልጣል"

#የስንብት_ቀለማት


@AdamuReta
@isrik


"አባቴ ወላጄ ብቻ ሳይሆን የቤታችን የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ የባህል ሚኒስትርና ያው
የማይቀረው የስድብና የጥፊ ሚኒስትር ነው። ሹመት በደራረቡ በአገሩ መሪዎች ሲያላግጥ ሳቄ ይመጣል።"


@AdamuReta
@isrik
@AdamuReta


"ቦታና ጊዜው ቢለዋወጥም አንዳንድ ጊዜ የሚያስገምትም ይሁን የማያስገምት 'አለመለወጥ' ስር ነቀል ለውጥ የሚመስልበት ጊዜ አለ"

#ሕማማትና_በገና

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik


''ሕይወት እኮ መለወጥ እንደምትችል በየጊዜው አንድ የተለየ ነገር እያደረክ ማረጋገጥ ነው።

ማፍቀር እንደምትችል አረጋግጠሃል፤
መርሳት እንደምትችል አረጋግጥ።''

***
#መረቅ (አዳም ረታ)


@AdamuReta
@isrik


"የፖለቲካ ትግል ብላችሁ ብራና ትሸጣላችሁ።

ልዩ ናችሁ።

ልዩ በመሆናችሁ ባያገባኝም ያገባኛል።

አየህ ወንድሜ ገንዘብ ይመለሳል፤

ባህል አይመለስም።

ከጀርባዬ ያለው የያኒስ ሪስቶን Moonlight Sonata የተባለ ግጥም ፎቶ ነው። ሰውየው ኖቤል ፕራይዝ አሸንፎ የሽልማቱን ገንዘብ መቀበል አልፈለገም። ይሄ ግጥም ምን ይላል መሰለህ

[... I know that each one of us travels to love alone, alone to faith and to death.I know it. I’ve tried it. It doesn’t help.Let me come with you...] ግጥም መተርጎም እንደሚከብድ ታውቃለህ? መተርጎም ልሞክር?

ይገባኛል
ለየብቻችን ወደ ፍቅር ወደ እምነትና ወደ ሞትእየተጓዝን ነው
ሞክሬዋለሁ።
ምንም አይፈይድም።
ከአንቺ፡ ከአንተ፡ ከእናንተ ጋር ልምጣ. . .

አየህ ሪስቶስ ሃይለኛ ነበር።

ከተከፋፈልክ የትም አትደርስም ማለቱ ነው። መከፋፈል ደግሞ በራስ ውስጥም ሊሆን ይችላል።

ፍትሕ ትወዳለህ፤ ፍትሕ እንደጎደለ እያወቅህ ግን ዝም ትላለህ። አየህ፤ ይሄ አንድ ሰው ሲከፋፈል ነው።

***

የስንብት ቀለማት

@AdamuReta
@isrik


የፍቅር ቀን ወይም የአደይ ቀን

'እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የፍቅር ጀግና ለማድረግ በአገራችን ቫለንታይንስ ደይ እየተባለ የሚከበረውን የፈረንጆች በዓል ተውሰን እንደ አገራችን ፀባይ ለማክበር እቅድ አውጥተን ነበር፡፡

የጦር ጀግኖች ብቻ ሳይሆን የፍቅር ጀግኖች ያስፈልጉናል፡፡

ቫለንታይን ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ ክፋት የለበትም፡፡ ተቃቅፈው የሚሄዱ ፍቅረኞች ማየት ደስ ይላል፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘው በመንገድ የሚሄዱ ወጣቶች ትዕይንት የሚናፍቅ ነው፡፡ እኔ ወጣት በነበርኩበት ዘመን እንዲህ ማድረግ ያሳፍረን ነበር፡፡ ልጆቻችን በፍቅር እንዲያፍሩ አልፈልግም፡፡

ፍቅርን ከብልግና አምታተናል፡፡

ይሄን ቫለንታይን ቀን በዓል ኢትዮጵያዊ ለማድረግ ሦስት ነገሮች ማሟላት አስበን ነበር፡፡

አንደኛ፤ ከየትኛውም የአገራችን ክፍል አስገራሚ የፍቅር ታሪኮችን መሰብሰብና ለብሔራዊ በዓል የሚያገለግለንን ነቅሰን ማውጣት፤

ሁለተኛ፤ ምሳሌ የሚሆኑንን የአበባ አይነትና የአበባ ቀለም መምረጥ፤

ሦስተኛ፤ በታዋቂ ገጣሚ፤ ሙዚቀኛና ኮርዮግራፈር በአሉን የሚዘክር በቀላሉ አድማጭ ሊያንጎራጉረው የሚችል ዜማ መስራት ነበሩ፡፡

ከነዚህ ውስጥ ኮሚቴው ለብቻው የሚወስናቸው የበዓሉን ቀን፣ የአበባው ዓይነትና የአበባ ቀለም ሲሆኑ፣ የተቀሩት ዐላማዎች ግን በጥናትና በህብረት ውሳኔ ይፀድቃሉ፡፡

አገራችንን ከአደይ የበለጠ ምን አይነት አበባ ሊወክላት ይችላል? ከመስከረም ወር የበለጠ ምን የሚያምር ወር አለ? ቢጫ ቀለምስ ውብ አይደለም?

የአገራችን ስም ከተሰራባቸው ቀለማት አንዱ ዮጵ ትርጓሜው ቢጫ ወርቅ ማለት ነው፡፡ ቢጫ የፀሐይ ብርሃን ነው፡፡ ፀሐይ ከሌለ ሕይወት የለም፡፡ እንደ ፍቅረኞች ፊት የምታበራው ፀሐይ አይደለችም? የተፋቀሩ ሁሉ እየተንቦገቦጉ አይደለ የሚውሉትና የሚያድሩት?

#የስንብት_ቀለማት
አዳም ረታ

@AdamuReta
@isrik


"እውነት የሚባለው ነገር ከምናየው፣ ከማናየው፣ ከምናምንበትና ከማናምንበት የተቀመመ መሆኑን መረዳት የሚያስፈራራ፣ በትንሹም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አለው አይደል? በማንፈልገው 'ተበዳይነታችን' ውስጥ ባናወራውም የራሳችን ተሳትፎ ይኖርበታል። ምንም ብንክድ አወዳደቃችን ውስጥ የኛ ኃሳብ በማይታይ መልክ ተቀምጧል ('እዚህ ምን አደርጋለሁ?' እያለ)። ሌሎች ድርጊት ውስጥ ያለው ማጥፊያ ሴራ በእኛ የታበየ የቂሎች ሳቅና ድጋፍ የታጀበ መሆኑን እንስተዋለን።"

**
-አዳም ረታ

( እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ)

@AdamuReta
@isrik


"መጥፎነት በርግጥ መጥፎነት የሚሆነው የተደረገው ሲካድ ነው። የታለፈው አልታየም ሲባል ነው። ባለፈው ክረምት ቤት ባንሰራም ቢያንስ ዝናብ ዘንቦ እንደነበር መናገር ማንን ያቆስላል?"

***

የስንብት ቀለማት

#በአዳም_ረታ

🈴JOIN🈴

@AdamuReta

COMMENT

@isrik

20 last posts shown.

665

subscribers
Channel statistics