የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኤርባስ A350-1000 በጥቅምት ወር ሊረከብ መሆኑ ተገለጸ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አኅጉር የመጀመሪያውንና ከ350 እስከ 410 መንገደኞች ማሳፈር የሚያስችለውን ግዙፍ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በጥቅምት ወር እንደሚረከብ ተሰምቷል።
አውሮፕላኑ ET-BAW በሚል የተመዘገበ ሲሆን፤ 46 የቢዝነስ ደረጃ እና 349 የኢኮኖሚ ደረጃ መቀመጫዎች በአጠቃላይ 395 መቀመጫዎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ ከሌሎች አውሮፕላኖች ጋር ሲወዳደርም ከፍተኛ የቢዝነስ ደረጃ መቀመጫዎችን ያሉት ነው።
ኤ350-1000 የመጀመሪያ በረራውን ከአዲስ አበባ ወደ ሄትሮው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ህዳር 3 ቀን 2024 በማድረግ ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚመጠበቅ ተነግሯል።
እነዚህ አውሮፕላኖች ከ777-300ER በመቀጠል ሁለተኛው ከፍተኛ ሰው የመጫን አቅም ያላቸው እንደሚሆኑም ተመላክቷል።
በሐምሌ ወር 2014 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚያደርገውን የኤርባስ A350-1000 ትዕዛዝ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር መፈራረሙ ይታወቃል፡፡
አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ከኩባንያው 22 ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን በማዘዝ 16ቱን ተረክቦ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፤ ከተቀሩት የኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ትዕዛዞች አራቱ ወደ ኤርባስ A350-1000 እንዲቀየሩ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000ን አገልግሎት ላይ ያዋለ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ያደርገዋል፡፡
[Ahadu]
@Addis_Mereja