የግብጹ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች ጋር የሶስትዮሽ ጉባዔ ለማድረግ አስመራ ገቡ
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ እና ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ ጋር የሶስትዮሽ ጉባኤ ለማድረግ አስመራ ገቡ።
በትላንትናው ዕለት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ ኢርትራ መግባታቸው እና ‘በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት’ ዙርያ ከኢሳያስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገ/መስቀል የግብጽ እና የኤርትራ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማሻሻል እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ፣ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ እና ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ የሶስቱን አገራት ግንኙነትን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጠናው ጸጥታ እና መረጋጋት ዙሪያ የሶስትዮች ጉባኤ ያደርጋሉ ተብሏል።
@Addis_Mereja