በትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ አቅራቢያ ሁለት ሽጉጥና ሐሰተኛ ፓስፖርት ይዞ የተገኘው ግለሰብ ታሰረ!
ዶናልድ ትራምፕ በካሊፎርኒያ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ ባሉበት መድረክ አቅራቢያ ሁለት ያልተመዘገቡ ሽጉጦች ይዞ ተገኝቷል የተባለው ግሰለብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ።የ49 ዓመቱ ተጠርጣሪ ቬም ሚለር ጥቁር መኪና እየነዳ ሳለ ነው በፖሊስ እንዲቆም ታዞ ፍተሻ የተደረገበት። ፖሊስ ከመኪናው ውስጥ ሁለት ሽጉጥ እና “ብዙ ጥይቶች ያሉት ካርታ” ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።
በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ አሳውቀዋል።የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሲክሬት ሰርቪስ ግለሰቡ ለትራምፕ “አደጋ የሚሆን አይደለም” ብሎ ምንም ዓይነት ግርግር እንዳልተፈጠረ አስረድቷል።
የአካባቢው ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለውን ግለሰብ “ወፈፌ” ሲሉ የገለፁት ሲሆን የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ታዳሚዎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደገነም ብለዋል።
ነገር ግን አሁንም በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ አላገኙም።የሪቨርሳይድ ክፍለ ግዛት ፖሊስ ኃላፊ ተጠርጣሪው ምን ዕቅድ እንደነበረው ማወቅ ከባድ ቢሆንም ግለሰቡ ግን ፖሊስ ፕሬዘደንቱን ከሶስተኛ የግድያ ሙከራ እንደታደጋቸው ነው “የሚያምነው” ይላሉ።
ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር የዋለው በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት 11፡00 ሲሆን ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ አንድ ሰዓት ቀርቷቸው ነበር።የአሜሪካ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ሶስት ሳምንታት ይቀሩታል። በየቦታው እየዞሩ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ ከባድ የሚባል ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው።
[BBC]
@Addis_Mereja