📍አዲስ አበባ
የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ አዲስ ታሪፍ ይፋ አድርጓል።
በዚህም በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በተሰማሩ ሚኒ-ባሶች ፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።
አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
ጭማሪ በተደረገበት በአዲሱ ታሪፍ ዝቅተኛው 10 ብር ሲሆን ከፍተኛው 65 ብር ገብቷል።
" ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ ነበር ፤ ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነበር " ሲል ቢሮው ገልጿል። የአሁን አዲስ ታሪፍ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ እንደሆነ አመልክቷል። የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስቧል።
(የአዲሱ ታሪፍ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)
@Addis_Mereja