ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን ገለጸ
የስልክ ንጥቂያ ወንጀል ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት እየተስፋፋ ያለ ወንጀል ነው፡፡ የብሪታንያ መዲና በሆነችው ለንደን ይህ ወንጀል አሳሳቢ ሆኗል፡፡ የለንደን ከንቲባ ሳዲቅ ካሃን በከተማቸው የተስፋፋውን የስልቅ ነጥቆ መሮጥ ወንጀል ለመቀነስ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለዚህ እና መሰል ወንጀሎች ለመከላከል መፍትሔ እንዲፈልጉ ጥሪ አቅርበውም ነበር፡፡
ጎግል ለዚህ ወንጀል መልስ በሚል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ሰዎች ስልካቸውን በስርቆት ሲያጡ ለስልክ ቀፎ አምራች ድርጅት ወዲያውኑ ማመልከት የሚችሉበትን ስርዓት ዘርግቷል ተብሏል፡፡ ከዚህ በፊት ሰዎች ስልካቸውን ሲሰረቁ ቀፎው እንዳይሰራ ለማድረግ ማዘጋት የሚችሉት የይለፍ ቃላቸውን ካስታወሱ ብቻ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ግን ስልክ ቁጥራቸውን መናገር ከቻሉ የተሰረቀው ስልክ እንዳይሰራ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ቢቢሲ በቴክኖሎጂ አምዱ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩ እና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች የጠፋባቸውን መረጃዎች ወደ ሶስተኛ አካል ከመተላለፋቸው በፊት ያለምንም መቆራረጥ ዳም መልሰው እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
@Addis_Mereja