ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀረች
ኢትዮጵያ በሶማሊያ በሚሰማራዉ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ሳትካተት ቀረች
በጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ዉስጥ ለመካተት ያነሳችውን የተሳትፎ ጥያቄ ሶማልያ ሳትቀበለዉ ቀርታለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ለማቋቋም ትናንት አርብ ዕለት በውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።
15 አባላት ያሉት ምክር ቤት በእንግሊዝ መሪነት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ በ14 ድምጽ ሲያፀድቅ አሜሪካ የድምፅ ተአቅቦ አድርጋለች።
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ለመወጣት ዝግጁ ናት ሲሉ ቢገልጹም ፤ የሶማልያው ተወካይ በሰጡት ምላሽ ሶማልያ የወታደሮቹን አሰፋፈር ብሔራዊ ጥቅሟን ባስከበረ መልኩ እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል።
"አሁን ያለው የወታደሮች ድልድል በስምምነት እንደሚጠናቀቅ አበክረን እንገልፃለን" ያሉት የሶማሊያ ተወካይ በአሁኑ ወቅት የግብፅን ጦር ጨምሮ 11,000 ወታደሮች ማሰባሰብ ችለናል ሲሉም ተናግረዋል።
@Addis_Mereja