ስልክ ደውሎ ቀጠሮ እስከማስያዝ የደረሰው አዲሱ የጉግል ጄሚናይ አገልግሎት ይፋ ሆነ !
ጉግል ጄሚናይን ከጥያቄ መላሽነት ወደ ሥራ ፈጻሚነት የሚያሸጋግር “Tasks in Gemini” የተሰኘ አዲስ አገልግሎት አስተዋውቋል።
ቴክ ክራንች እንደዘገበው አገልግሎቱ በአሜሪካ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ህንድ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በነፃ መቅረብ ጀምሯል። የሚሠራውም በ “Gemini 4 Hydrogen” ሞዴል ላይ ነው ተብሏል።
ሀሳቡ ቀላል ነው፤ ብዙ ደረጃዎችን የሚጠይቅ ሥራ ለጄሚናይ ሰጥተው ወደ ሌላ ጉዳይዎ ይሄዳሉ፤ እሱ ደግሞ ከጀርባ ሆኖ ይጨርሳል።
ከኢሜይልዎና ከካሌንደርዎ መረጃ ተነስቶ የቀን ሥራዎችን ሊያደራጅ፣ የጉዞ ዕቅድ ሊያዘጋጅ፣ ተደጋጋሚ ምርምር ሊያከናውን ይችላል።
አገልግሎቱ ከዚህም ያልፋል። ስልክ ደውሎ ዋጋ ያወዳድራል፣ ምርት መኖሩን ያረጋግጣል፣ ቀጠሮም ያስይዛል።
ይህ እድገት የኤአይ ዘርፍ ወዴት እየሄደ እንደሆነ ያሳያል፤ መረጃ ከሚሰጥ ረዳት ወደ ሥራ ፈጻሚ ወኪልነት።
ተደጋጋሚ ሥራዎችን በመውሰድ ጊዜ የሚቆጥብ ከሆነ ዲጂታል አገልግሎቶችን የምንጠቀምበትን መንገድ በእጅጉ ሊቀይረው ይችላል።
@Addis_News