بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته
🍃🥀🍃🥀🍃🥀🍃
لله تعالى
🌱🌱ترك الغضب
🍒ቁጣን መተው(ንዴትን መቆጣጠር🌺
➡️ቁጣን መተው እጅግ በጣም አስፈላጊ እና አንገብጋቢ የሆነ ጉዳይ ነው።
قال رجل للنبي صلى الله عليه وسلم "يا رسول الله ما ينجيني من غضب الله؟" قال عليه الصلاة والسلام" لا تغضب."
አንድ ሰው ወደ ረሡል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም በመምጣት "ከአሏህ ቁጣ ነጻ የሚያወጣኝን ነገር ንገሩኝ" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም "አትቆጣ"በማለት መለሡለት። ይህ ብሎ ማለት ከአሏህ ቁጣ ሰላም መውጣት የፈለገ ሰው ቁጣን መተው አለበት።ምክንያቱም ቁጣውን የሚቆጣጠር ሠው ዲኑም ዱንያውም ሠላም ይሆንለታል። እጅግ በጣም አያሌ ሠዎች ቁጣቸውን ባለ መቆጣጠራቸው ምክንያት ከዲን ሲያፈነግጡ እና ዲናቸው ብሎም የዱንያ ሀያታቸው ሲበላሽ ይስተዋላል።
ቁጣን አለመቆጣጠር ወይም ቁጣን ማብዛት ከሚወዳት ሚስቱ፤ ከልጆቹ፤ከቤተሰቦቹ እና ከጓደኞቹ ያቆራረጠዋል።
☘ "አድ" ከሚባሉ የቀድሞ አረቦች መካከል አንድ በእስልምና ላይ ለ40 ዓመት ያህል የጸና ሰው ነበር።ስሙም ሂማር ኢብኑ ማሊክ ሲሆን በሠዓቱ የአከባቢው መሪ ነበር። አሏሁ ተዓላ ይህን ሰው ልጆቹን በሙሉ አደን በወጡበት ሰዓት መብረቅ አውርዶ አጠፋቸው።ይህ ለ 40 አመታት ያህል አሏህን ሲገዛ የነበረው ሠው እንዴት እየተገዛሁት ልጆቼን ያጠፋል በማለት በንዴት ምክንያት ጌታው ላይ በማመጽ ከፈረ። ለአርባ አመት የነበረበትን እምነት በመልቀቅ አፈነገጠ። ይህ ሰው በንዴት ምክንያት ዱንያውንም አኼራውን አበላሸ። አህባቢ ፊልላህ እጅግ በጣም ጥንቃቄ ልናደርግ እና በንዴት ሰበብ ራሳችን አደጋ ውስጥ ላለመጣል ቁጣችንን መቆጣጠር የግድ ነው። አሊያ በንዴታችን ሰበብ ሀያታችን ሊበላሽ ይችላል።
فعن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال "ليس الشديد من غلب بالصرعة إنما الشديد الذي يملك نفسه عند الغضب."رواه البخاري
🌴አቡ ሁረይህ ረድየሏሁ አንሁ እንዳስተላለፉት የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል:-"ጀግና ብሎ ማለት ሠዎችን ታግሎ የጣለ ሳይሆን በንዴት ግዜ ራሱን የተቆጣጠረ ሰው ነው።" ቡኻርይ ዘግበውታል።
🌿ቁጣን ለመተው ከሚያግዙ ነገራቶች መካከል አሏህ የሁሉነገራቶች ፈጣሪ መሆኑን እና ነገራቶችን ካለለመኖር ወደ መኖር የሚያስገባ መሆኑን ማስተንተን፤ በእያንዳንዱ ንግግሩ እና ተግባሩ አሏህ ዘንድ አንደሚጠየቅበት ማስተንተን እንዲሁም "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" የሚለውን ዚክር ማብዛት እና እነዚህን የመሳሰሉ ነገራቶችን መከወን ቁጣን ለመተው ሠውየውን ይረዱታል።
🥀አንድ ሠው ቁጣ ሲመጣበት የነበረበትን ሁኔታ ይቀይር። ማለትም ቆሞ ከነበር ቁጭ ይበል ቁጭ ብሎ ከነበርም ጋደም ይበል እንዲሁም ውዱእ ያድርግ።ይህን ማድረጉ ንዴቱን ወይም ቁጣውን ለማብረድ ሁነኛ ሚናን ይጫወታል
https://t.me/anallmuslim