(ቀልቤን ባትሰርቀው)
ካፈቀርኩህማ ዘመናት አለፈ
ወተቱም እረግቶ ፣ ለቅቤ ተረፈ
እሳቱም ባነደው ፣ አመድን ወለደ
ደግሼም ሳልጠራህ፣ ኑሮተወደደ
ይኸው በትረካ፣ ስምህን እያወጋሁ
ስንቱን አቀበት ፣ በሀሳቤ ወጣሁ
የሆዴ ማጀትም ፣ ቅኔውን ቢሰፋ
ወርቁን አላገኘ፣ ሚዛንም አልደፋ።
ሰውነቴም ቢሆን አቅሙን ተነጠቀ
ፍቅርህን ተርቦ፣ በናፍቆት አለቀ።
ድሮም እኮ - - -
ያለቤቱ አይነድም እሣቱ
ማሩም ይቀርና ይበዛል እሬቱ
እህልም እኮ ካልዘሩት በወቅቱ
አረም ይከበዋል አያምርም ውጤቱ
ስለዚህ አለሜ - - -
በታሪክ ጀበና ፣ ስማችን ይቀዳ
ከራሳችን አልፎ፣ እንትረፍ ለባዳ
እንኳንስ የሰው ልጅ ፣ የተማረው ቀርቶ
እንስሳም ይኖራል ፣ በህብረት ተስማምቶ
እንደው ምን አለበት ፣ ቀልቤን ባትሰርቀው
አብረኸኝ ብትሆን ልቤን ባሳርፈው።
# ቤዚቾ
የጥበብ ልሳን!
@ArtGosa
@ArtGosa
@ArtGosa
ካፈቀርኩህማ ዘመናት አለፈ
ወተቱም እረግቶ ፣ ለቅቤ ተረፈ
እሳቱም ባነደው ፣ አመድን ወለደ
ደግሼም ሳልጠራህ፣ ኑሮተወደደ
ይኸው በትረካ፣ ስምህን እያወጋሁ
ስንቱን አቀበት ፣ በሀሳቤ ወጣሁ
የሆዴ ማጀትም ፣ ቅኔውን ቢሰፋ
ወርቁን አላገኘ፣ ሚዛንም አልደፋ።
ሰውነቴም ቢሆን አቅሙን ተነጠቀ
ፍቅርህን ተርቦ፣ በናፍቆት አለቀ።
ድሮም እኮ - - -
ያለቤቱ አይነድም እሣቱ
ማሩም ይቀርና ይበዛል እሬቱ
እህልም እኮ ካልዘሩት በወቅቱ
አረም ይከበዋል አያምርም ውጤቱ
ስለዚህ አለሜ - - -
በታሪክ ጀበና ፣ ስማችን ይቀዳ
ከራሳችን አልፎ፣ እንትረፍ ለባዳ
እንኳንስ የሰው ልጅ ፣ የተማረው ቀርቶ
እንስሳም ይኖራል ፣ በህብረት ተስማምቶ
እንደው ምን አለበት ፣ ቀልቤን ባትሰርቀው
አብረኸኝ ብትሆን ልቤን ባሳርፈው።
# ቤዚቾ
የጥበብ ልሳን!
@ArtGosa
@ArtGosa
@ArtGosa