የዘጠናዎቹን ቀለም ያጎላችው ሀይማኖት ግርማ!
የዘጠናዎቹን ተወዳጅ ሙዚቀኞችን እና አልበሞችን አንስተን የማንዘነጋት አንዲት እንስት አለች እሷም ሀይማኖት ግርማ ነች በዛሬ የአልበም ትውስታችን የምንቃኘው ደግሞ "ጃለሌ" የተሰኘው አልበሟን ይሆናል።
ይህ 12 በተለያዩ ስልቶች የተሰሩ ሙዚቃዎች የተካተቱበት የሀይማኖት ግርማ ጃለሌ አልበም በዘጠናዎቹ ወጥተው ተወዳጅነትን ካተረፉ አልበሞች መካከል ነው።
በወቅቱ እጅግ ታዋቂ በነበሩ እና አንጋፋ እና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን በሚያቀርቡባቸው የምሽት መዝናኛ ቤቶች መድረክ ላይ "የሀረሯን ቆንጆ" ሀይማኖት ግርማን ማየት ብቻውን ያዝናና ነበር በዚህ መልኩ የሙዚቃን ሀሁ የቆጠረችው ሀይማኖት ግርማ ቦኋላም የራሷን ስራዎች መስራት ስትጀምር ተቀባይነት ለማግኘት አልተቸገረችም።
አልበሙ መጠሪያውን ያገኘው "ጃለሌ" ከተሰኘው በአልበሙ ውስጥ ቁጥር አንድ ትራክ ላይ ከሚገኘው የአፋን ኦሮሞን ከአማርኛ ጋር አዋህዳ በሰራችው ሙዚቃ ሲሆን ትርጉሙም "ፍቅሬ" ማለት ነው። የሩቅ ፍቅር ጎትቶ ያመጣባትን ናፍቆት በዚህ ሙዚቃ ውስጥ በሚገኙ ግጥሞች ለማከም የሞከረች ይመስላል።
በዚህ ተወዳጅ አልበም ላይ መገራ ወገር፣ አዲስ አባ፣ የማልቀይረው የተሰኙ ነጥረው መውጣት የቻሉ ድንቅ ሙዚቃዎችን ጨምሮ በድምሩ 12 ተወዳጅ ሙዚቃዎችን በውስጡ አካቶ ይዟል።
በግጥም ድርሰት ኃ/የሱስ ፈይሳ (4)፣ ሀብታሙ ቦጋለ(3)፣ ጌታሁን ምትኩ( ጌቱ ኦማሂሬ)(3)፣ ሀይሰም አባሂስ እና ሙሉቀን ዳግርማ ተሳትፈዋል በዜማ ድርሰት ደግሞ ተወዳጁ አርቲስት ታምራት ደስታ ሁለት ዜማዎችን ያዋጣ ሲሆን ኃ/የሱስ ፈይሳ(5)፣ ጌታሁን ምትኩ(ጌቱ ኦማሂሬ) (3)፣ ሀብታሙ ቦጋለ እና ሀይሰም አባስ ለግጥሙ እና ከሀይማኖት ግርማ የድምፅ ቃና ጋር የሚመጣጠኑ ዜማዎችን አቅርበዋል።
ተወዳጁ የሙዚቃ ሰው ጊታሪስት እና አቀናባሪው ዳግማዊ አሊ ጃለሌ አልበምን ይህ ቀረሽ እንዳይባል አድርጎ ቅንብሩን የሰራው ሲሆን ከቅንብር ውጪም በዚህ አልበም ስኬት ላይ የነበረው ድርሻ የጎላ ነበር።
ሀይማኖት ግርማ በተለይ ከጌታሁን ምትኩ ጋር በሰራችው ኦማሂሬ ሙዚቃ ይበልጥ የምትታወቅ ሲሆን አስማሉህ፣ላባብልህ እና ከዚራ የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ በርካታ ተወዳጅ ስራዎችን ያደረሰችን ድንቅ አርቲስት ነች።
@Birabiromusic