TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
የመጽሐፍ መረጃ | Book Mereja

28 Sep, 07:02

Open in Telegram Share Report

ፈውስ የራቀው ሰው... 📖✨

​አለን ኤስ በአንድ ትልቅ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ድርጅት ውስጥ የመስክ ተወካይ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ ሰው ባለቤትና አራት ልጆች ያሉት ቢሆንም ከሌላ ሴት ጋር ድብቅ የፍቅር ግንኙነት መስርቷል።

​ወደ እኔ ሲመጣ ፊቱ ላይ ፍርሃት ይነበብበት ነበር፤ ቁጣ ቁጣም ይለዋል።
የእንቅልፍ እንክብል ካልወሰደ እንቅልፍ በዓይኑ አይዞርም።
ከፍተኛ የደም ግፊት እና ሐኪሙ ያላወቀለት ሌሎች የውስጥ ሕመሞች ነበሩበት።
በዚያ ላይ ከልክ በላይ ይጠጣል።

​ብዙም ሳይቆይ ለመረዳት እንደቻልኩት፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤው በውስጡ ያለ ስር የሰደደ የኃጢያተኝነት ስሜት ነው።

ያደገበትን ሃይማኖቱን እጅግ በጣም ያከብራል፣ ይፈራል።
በዚህ የተነሳ የጋብቻ ቃል-ኪዳኑን በማፍረሱ ውስጡ በወንጀለኛነት ስሜት እየተለበለበ ነበር።

​ይህንን የአዕምሮ ቁስል እንዲጠግግ እና ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ብሎ አዘውትሮ የሚወስደው መጠጥ ችግሩን ከማባባስ በቀር የፌደለት ነገር አልነበረም።
ነገሩ እሳትን በቤንዚን ለማጥፋት እንደመሞከር ነው።

​ይህ ሰው ለምን ፈውስ ራቀው⚡️
​አለን ስለ አዕምሮአችን ገለፃ ሳደርግለት በሚገባ አዳመጠኝ።

ችግሩንም ረጋ ብሎ አሰበው።
በመጨረሻ ድብቅ ግንኙነቱን ለማቆም ውሳኔ ላይ ደረሰ።
የመጠጥ ሱሱም ቢሆን ሳይረዳ ከራሱ ለመሸሽ ያደረገው ሙከራ እንደሆነ ተረዳ።

ድብቅ አዕምሮው ውስጥ የተሰነቀረው ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ተመንግሎ እስካልወጣ ድረስ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያገኝ ሲገነዘብ፣ በውስጡ የመተማመን መንፈስ ፈጠረለት።
​በመጨረሻም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ለመላቀቅ ቻለ።

​💡 ከጽሑፉ የምንወስደው ትምህርት፦
​ከተጠናወተን ጎጂ ልማድ ለመላቀቅ ጥልቅ ፍላጎት ካለን፣ 51% ፈውስ እንዳገኘን ይቆጠራል።
ይህን ጎጂ ልማድ ለማቆም ያለን ፍላጎት ለመቀጠል ካለን ፍላጎት የበለጠ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ መላቀቅ አይከብደንም።

​በአዕምሯችን መላልሰን የምናስበው ነገር የመጉላት ባህርይ አለው፤ በመሆኑም፦
• ከጎጂ ልማድ የመላቀቅን ነፃነትና የአዕምሮ ሰላምን መላልሰን እናስብ።
• አትኩሮታችንን ሁልጊዜ በዚህ አዲስ አቅጣጫ እናድርግ።
• ይህን ስናደርግ ቀስ በቀስ የነፃነትና የሰላም ስሜት በመላ አካላችን እየተሰማን ይመጣል።

​✍️ ጆሴፍ ማርፊ (Joseph Murphy)

📖"አእምሮን በብቃት በመጠቀም መልካም ሕይወትን የመምራት ቁልፍ ምስጢራት" (ትርጉም፦ እስክንድር ስዩም)

​ብሩህና የአእምሮ ሰላም የሞላበት አዲስ ቀን ይሁንላችሁ❕ 🌸

​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me

8.4k 0 13 69
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot