ክንዱ ትከሻዋን፥ ቀኝ እጁ ቀኝ እጇን፥ ትኩስ ትንፋሹ ጆሮዋን፥ አንገትዋን ሲነካት፥ ልዩ ሙቀት፥ የወንድነቱ ሙቀት፥ በዚህ ሁሉ በኩል፥ እንደ ኤሌክትሪክ ማዕበል በሰራካላትዋ ጎርፎ አጋላት። ያ ለምለም፥ ያ ውብ አካላትዋ ከማር ሰፈፍ እንደ ተሰራ ሁሉ፥ ሙቀት እንደሚፈራ ሁሉ፥ ትንሽ በትንሽ መቅለጥ፥ ትንሽ በትንሽ መፍሰስ ጀመረ። ሰውነቷን መግዛት፥ በሰውነቷ ማዘዝ ተሳናት። ወዲያው ሳታስበው፥ ሳታዝዘው፥ ራስዋ ቀና፥ ፊቷ ወደ ፊቱ ዘወር አለና፥ አፏ ተከፍቶ የሱን አፍ ፍለጋ ሲሄድ በመንገድ ተገናኙ። ከዚያ እጆቿ አንገቱን፥ የሱም እጆች የሷን ተጠምጥመው ይዘው፥ አፏ ባፉ፥ አፉ ባፏ ውስጥ ቀለጡ። እሱ በሷ፥ እሷ በሱ ውስጥ ጠፉ። [...] ወደ ሌላ ዓለም፥ ወዳንድ አዲስ ዓለም ገቡ።
ትንሽ ዝም ብለው፥ ዓይን ላይን ተያዩና፥ ደግሞ እንደገና ዓይናቸውን ከድነው፥ ደግሞ እንደገና አፍ ላፍ ተያይዘው፥ ደግሞ እንደገና አንድ ላይ ተዋህደው፥ ደግሞ እንደገና ወዳገኙት አዲስ ዓለም ሄዱ።
ፍቅር እስከ መቃብር | ከሐዲስ ዓለማየሁ | ገጽ 317-318
ትንሽ ዝም ብለው፥ ዓይን ላይን ተያዩና፥ ደግሞ እንደገና ዓይናቸውን ከድነው፥ ደግሞ እንደገና አፍ ላፍ ተያይዘው፥ ደግሞ እንደገና አንድ ላይ ተዋህደው፥ ደግሞ እንደገና ወዳገኙት አዲስ ዓለም ሄዱ።
ፍቅር እስከ መቃብር | ከሐዲስ ዓለማየሁ | ገጽ 317-318