የዚህ ቀጣይ ?? እኔንጃ ብቻ ከዚህ ጋር የተያያዘ ነገር ልጽፍ አልኩኝና ሀሞቴ ፈሰሰ። መፍሰስ ብቻ አይደለም ለምንድነው የምጽፈው ግብግብ ከራሴ ጋር ጀመርኩኝ 🧐
ሰበብ ከምክንያት ደርድሬ ....
"አሁኑኑ ሳይጠፋብኝ ልፃፈው.."
"ገና ከጸሐይ መግባቴ አይደል እንዴ በዛ ላይ የጠዋቱ ፈተና ራሴን አሳምሞኛል ክላስም ጆሮኤን ከማስደንቆር ያለፈ ምንም አላተረፍኩም። አረፍ ልበል ከምሳ ቡና በኋላ እጽፋለው።"
ብዙ ጨመርኩበት ቀነስኩበት ፣ በሃሳብ ወረቀት ተሰረዘ ተደለዘ፣ ተቆርጦ ተሰፋ በልክ። ደርሶ ስልኬን ሳነሳ ... ልጽፍ ...
"ምንትዋብ ተነሽ እስቲ ልጄ የማርያምን ሽንኩርት እንላጥ በረከቱም ይደርስሻል "
ጉም😐 ከ10 ኪሎ ሽንኩርት ጋር መፋጠጥ
'በቃ ይሄንን ልጨርስ እራትም ልስራ በስርዓት ልረጋጋና እጽፋለው ....ቆይ ...ቆይ ... እራት መስራት ከየት መጣ??'
12 ሰዓት። ጨራረስኩ ሻዬን አፈላው ወይራዬን አጫጫስኩ 😌 ሰላም በሰላም። ገና "እሷና እኔ" እንዳልኩኝ .... ከየት ላምጣው?? የት ገባ ?? በሃሳቤ 30ና 40 ጊዜ እየጻፍኩት? የመርሳት ችግር አጋጠመኝ ?? አረጀው እንዴ?? ባስስ ባስስ አጣሁት። ደንግጬ ሳልጨርስ....
"አስር ድስት ጥደሽ አስሩም አረረብሽ እኮ! መቼ መፍጫውን መለሽና ነው የምትቀመጭው"
የቁጣ ናዳ 😂
ይሄው ጭው ብሎብኝ አሞቴም ፈሶ ቁጭ ብያለው።
እስቲ coming soon በምትለው እንያዛትና የመጻፍ ልክፍት እስኪያንዘፈዝፈን እንጠብቃለን ። እንዲህ ካልተደነጋገርን
መልካም ምሽት ይሁንላቹሁ !🦋