"....ዛሬ ዛሬ ሙሉ በሙሉ የተረዳሁት የሐበሾች ስር ነቀልነት መሰረቱ ስሜት መሆኑን ነው።
ከዐሥረኛ ፎቅ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሆሆሆ ብለው እርስ በእርስ ተነዳድተው እየተንበለበሉ ይወድቃሉ።
ለእነሱ ዋናው ጉዳይ መውደቁ ሳይሆን ከፋም ለማም እጅ ለእጅ መያያዙ ነው። በሰው የደረሰበት ቢደርስባቸው ስህተት አይደለም።
ማሰብ የሚጀምሩት በመዋግደ ሕሊና ግፊት በመውደቅ ጎዳና ላይ ስምንተኛው ፎቅ ሲደርሱ ነው።
ወደ የት እየሄድን ነው? ይላሉ
ፓራሹቱን ይዘሃል ወይ? ይባባላሉ።
አምስተኛ ፎቅ ጀምሮ ወሬአቸው ጭቅጭቅና ፀፀት ነው። እስከ ዜሮ ፎቅ የሚቀጥለው ጉዞ በጸሎት የታጠረ ምሬት ነው። በየደጀሠላሙ መንበርከክ ነው። ነጫጭ ለብሶ በክራላይሶ መንደድ ነው። ለ'ተለመነኝ' በሚያጤሱት ዕጣን መታፈን ነው። እግዜር በምሬት ይገጠምበታል፣ የሚረገም ይረገማል፣ ስለት ይገባል፣ ጥንቆላ ይጠነቆላል።የሚታማ ማሰስ ነው። እጃቸውን የያዘው ደባል ዘላያቸውን ሰው መርገም ነው። ወደ ኋላ እየተመለሱ በአጀማመራቸው ማሳበብ ነው።
መሬት ወድቀው በትዕንግርት ከመሰባበርና ከመሞት ቢድኑ፣ የአወዳደቃቸው ዚቅ ሊያርሙ እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ተያይዘው ወደ ፎቁ ይወጣሉ።
ስህተቱ መውደቁ ሳይሆን አወዳደቃቸው ይመስላቸዋል። ይሄ የማያቋርጥ ክብ የእኛ ነው።
#የስንብት_ቀለማት
#አዳም_ረታ