“ለምን መጣህ? ምን ቀረህ?” ዐይኖቿ የጥላቻ ጦራቸውን ሰብቀዋል። ሰውነቷ ይንዘፈዘፋል፣የሃዘን ካፊያ ጠግቦ።
“እንደሱ አይደልም እኮ….” እንዲሆናለች፣ከሰው ተራ ወጥታለች ካሉት ሴት ጋር አልገናኝ አለችበት። እነሱ አጋነው ነግረውት ነው ወይስ የራሱ የተጣመመ ልብ አጋኖ ተረድቶት ነው? እንኳንስ ከሰውነት ተራ ለትውጣ ከመቼውም የበለጠ አምሮባታል፣ ወዝ የጠጡት ጉንጮቿ በእልህ የጎመራ ቲማቲም መስለዋል፣ ዐይኖቿ በንዴት የንቦገቦጋሉ፣ ሉጫ ጸጉሯን እንደተላጨችው ቢያውቅም፣ በትንሽ ወር ውስጥ የበቀሉት ዘለላዎች ከሻሿ አልፈው እንደ ኑግ ያበራሉ፣ መውለዷ ሰውነቷን ሞልቶታል…. ቀጫጭነቷ በስጋ ትሸፍኗል፣ ያልተንቦራጨቀ፣ ያልተንዘላዘለ…. ሲሞቀው ተሰማው፣ ራሱን ወንድነቱን ጠላው። ይሄ አውሬ ልቡን ረገመው።
“በቁስሌ ላይ ጨው ለመንስነስ ነው?”
“ቁስል ቁስል ፣ ማንን ጥፋተኛ ለማድረግ ነው? ትሰሚያልሽ እኔ የመጣሁትኝ ሃዘንሽ ሃዘኔ ስለሆነ ነው። የውነት ባለቤትሽን በማጣትሽ በጣም ይቅርታ።”
“በጣም ቀልደኛ ነህ። 'ሃዘንሽ ሃዘኔ’? ለምን የሰጠሁሽ ትንሽዬ ገሃነም እንዴት ስትለበልብሽ እንደነበር ለማየት ነው አትለኝም?”
“እባክሽ እንደሱ አትበይ፤ ለኔ ምን ማለት እንድሆንሽ ታውቂያለሽ። አይደለም ያንቺን ሃዘን፣ በክፉ ሚያንሳሽን እንኳ እንደምጠላ….” መቀጠል አልቻለም። የዛኔ ለሀገር ፍቅራቸው ጉድ ሲባል፣ የልቡ በርታት የሆነችው ድክመቱን ፀፀቱን እንዳታይበት ፊቱን ገሸሽ አደረገ።
ከት ብላ ሳቀች፣ ከልቧ፣ አንጀቷ ተቃጥሎ ሆዷ እስኪፈርስ፣ ተንተከተች። ከ7 አመታት በኋላ የእውነት ሳቀች። ለሱ ግን ሳቋ መርዝ ሆነበት። በያንዳንዱ ቂ ቂ ቂ ውስጥ ለሱ ያላትን ቂም ጥላቻ በቀል በተዘዋዋሪ የምትነግረው መሰለው። ማንንም ፈጣሪን እንኳ ፈርቶ የማያውቀው ዛሬ የሷ ሳቅ በርክ ለቀቀበት። ያልተንቦራጨቀ፣ መደበቂያ ቢያጣ ፊቱን ደበቀ።
ጠራችው፣በስሙ፣ሊያውም አቆላምጣ፣ እንደማምር ከከንፈሮቿ የሚንጠባጠብ 'ዬ’ ስሙ ላይ እንደ ሀረግ የተጠመጠመ 'ዬ'። እንባውን ለመጥረግ ፋታም አላገኘም። መቼ ያነባው ነው? ከመቼ ወዲህ ነው እሱ ሚያለቅሰው? ግራ መጋባት ውስጥ ውስጡን ይቦጠቡጠዋል….
“የእውነት እንደዚህ ስቄ አላውቅም።” ከዐይኖቿ የፈለቁትን የእንባ ዘለላዎች በጣቷ እያንሳች፣ ተጠርገው እንዳይፈርሱ በጥንቃቄ። የሳቅ እንባ? ከመቼ ወዲህ ነው? እንቁ እንዳገኘች ሁሉ በአግራሞት አየቻቸው። ልትነግረው ቀና ስትል..... የእሱም እንባዎች በጉንጮቹ… የማይታመን ነው።
የመጀምሪያ ፍቅሯ እንባን አነባ።
ስሙን ደገመችው። የአሁኑ 'የኔ ጌታ'ን አስከትሎ ነው። እጆቿን ዘርግታ ፊቱን ወደሷ እያዞረች። ደጋሜ እንዚ ከሃዲ እንባዎቹ እንዳይወርዱ ግብግብ ገጥሟል። ዐይኖቹ እንባን ቀድተው የመልሳሉ፣ ካቅም በላይ ሞልተው ሳያፈሱ። ያመለጡትን በአውራ ጣቶቿ አበሰችለት፣ በከናፍርቷ አደርቀችለት።
“ዓለሜ ይቅርታ አድርጊልኝ…” ሳግ እንዳያወራ እየተናነቀው “ለዚህ ሁሉ የዳረኩሽ እኔ ነኝ፣ እድሜ ዘመኔ ሁሉ አንቺን ለመካስ አይበቃኝም። እኔ…” አቋረጠችው
“አይ አይ፣ የሕይወት አጋጣሚና እጣ ፋንታችን እንጂ በፍጹም ያንተ ጥፋት አይደልም እሺ?” ከመላው ሰውነቷ ፍቅር የተናል፣ ስታቅፈው የፍቅር ዝናብ እንደወረደብት ሁሉ ልቡ ረሰረሰ። በእቅፏ በደሉ ሁሉ ተሻረ። መቼም ላይተዋት፣ ፍቅሩን ላይቀንስባት ላሷ ሳይሆን ለራሱ በልቡ ቃል ገባ።
"ሰዓቱ ደርሷል እኮ አብሬህ ልሂድ እንዴ?" ጓደኛው ተፈራ ቢሮውን ሳያንኳኳ ዘው ብሎ እየገባ
"አይ፣ብቻዬን ይሻላል በጣም በዙ ማወራት አለኝ ከልቤ ይቅርታ ጠይቃታለው፣ እክሳታለው። አንተም ስራ የርፍድብሃል።" በሃሳብ ሰመመን ገንት ደርሶ የመጣው የምጀመሪያ ፍቅሯ።
ይቀጥላል
✍🏾✍🏾ምንትዋብ
14/06/2017✍🏾✍🏾