⎡
ነፃ–ምርጫ | Freewill
«...Let those who call themselves philosophers bear the risk to their mental health that comes from thinking too much about free will.»₁
—
[— እሳቤ ዘ ነፃ ምርጫ... ]
አንዳንድ ነገሮች ከቁጥጥራችን ውጭ ናቸው— ከኑባሬያችን በስተፊት የተፈጠሩ ነገሮች፤ መወለዳችን፤ በዘረ-መል የተለገስነው ሁሉ።
ሌሎች ደግሞ በቁጥጥራችን ስር ይመስላሉ — ይሄን ፅሁፍ ማንበብ ወይም መተው፤ አንባቢው ምርጫ አለው!
እንደነገሩ ከላይ ከላይ ከታሰበ ⎡ሊብሪተሪያኒስት⎤ ነን— ነፃ ምርጫ ያለንና ሁሉ ቀድሞ ያልተወሰነ፤ ቀድሞ ከተወሰነ ደግሞ መወሰኑ ከነፃ ምርጫችን ጋር ላይጣጣም የተረገመ ይመስላል። መወሰኑ ነፃ-ምርጫችንን ስጋት ላይ የሚጥል ቢመስል፥ መምሰል ብቻ እንጅ፤ ቅድመ—ውሳኔ ድርጊቶቻችንን በዘፈቀደ ከመመራትና የጭፍን የእድል ውጤት ከመሆን ይጠብቃቸዋል። አእምሯችን ከተቀኘበት ትንሽ ወጣ ስንል ⎡ኮምባቴብሊስት⎤ ወይ ⎡'ስኬፕቲክስ⎤ ነን— ነፃ-ምርጫችንና ቅድመ-ውሳኔው የሚጣጣሙ፤ ወይ ደግሞ ቀድሞ ተወሰነም ቀረም ነፃ-ምርጫ የለንም እንደማለት! ሁሉም ነገሮች ቀድመው ከተወሰኑ ቶማስ ሊጎቲ እንደሚለው ከአሻንጉሊት ላንበልጥ፤ የዘረመልና የአካባቢያችን ባሪያ ልንሆን። ቅድመ-ውሳኔ ስሁት ቢሆን ድርጊቶቻችን ሁሉ ጭፍን እንቅስቃሴ እንጅ ድርጊት አይሆኑም— ድርጊት ከተራ ⎡ሪፍሌክስ⎤ የሚነጠለው የድርጊቱን አላማና ግብ መኖርን መሰረት አድረገን ነው። አላማ ያለው ድርጊት በፈፃሚው ቅድሚያ መፈለጉ፤ ቅድመ ውሳኔን እውነት አድርጎ የ⎡ሊበሪትሪያንን⎤ «ነፃ-ምርጫ አለን!» መፎክር ⎡ኢሉዥን⎤ ብቻ ያደርገዋል።
[— ነፃነት ለድርጊት ፤ ነፃነት ለውሳኔ... ]
[Will] ይላሉ — ወሳኔ የመስጠት ብቃት ነው። የድርጊት ነፃነት የዚሁ ውሳኔ የመስጠት ነፃነት ውጤት ነው። ሁለቱን ነጣጥሎ ማሰብ ከባድ ነው — አንዱን መቁጥጥር ስር ማድረጉ ሌለኛውንም እንደመቆጣጠር ይወሰዳል። [Will] ልቦናዊ ነውና ለሱ ያለንን ነፃ ምርጫ (Freedom of will) ድርጊቱ ላይ ያለንን ነፃ ምርጫ (Freedom of action) ብንገልፅበት— ድርጊቱን ልቦናዊ ፤ ውሳኔያችንን ደግሞ ድርጊት (Action proper) ማድረግ ነው። ስጋዊ የሆነውን ድርጊት ልቦናዊ ለሆነው [Will] ማሰገድ! ከዚ ውንጀላ ለማምለጥ ማለትም ቶማስ ፒንክ እንደሚለው' ⎡«ቮሊሽናስት»⎤ ላለመባል ድርጊቱ ኢ-ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ከውሳኔው የተቀዳ ብቻ ሳይሆን በፈፃሚው በቀጥታና ያዊታዊ በሆነ መንገድ የሚተገበር ነው' የሚል መከራከሪያ ይቀርባል።—
«voluntary action ( Action other than 'action of will) is more than just an effect of an earlier action that was performed entirely inside my head. It is also a further and direct involvement on my part in agency, something over which I am exercising direct control as I do it»₂
[— ሰብዕ «አመዛዛኝ እንሰሳ» ስለመሆኑና፤ በመሆኑ ስለደረሰበት የነፃ-ምርጫ አፈና... ]
«ይሄን» ለመስራት ጠንካራ ምክንያት ካለህ «ያን» ለመስራት ነፃ ምርጫ የለህም። ድርጊቱ ጠንካራ ምክንያት በመኖርህ ቀድሞ ተወስኗልና! ቅድመ-ውሳኔ እውነት ከሆነ ⎡Incompatibilism⎦ ይሻራል— እርሱ የድርጊቶቻችንን ቀድሞ አለመወሰን መሰረት ያደርጋልና። በአንድ ጊዜ ምክንያታዊና ነፃ ምርጫ ያለው አካል መሆን ደግሞ ለፈጣሪ የተተወ ምሉዕነት ነው። ችግሩ ሲወስክ ተመልከት! ምክንያታዊነት የሚነግሰው ድርጊቶች—|Action proper| ላይ ባለን ነፃ-ምርጫ ላይ ብቻ አይደለም። በኛ ቁጥጥር ውስጥ ባልሆኑት እምነትና ፍላጎቶቻችንም ውስጥ ነው!—እነሱ |Theoretical reason| ሊሉት እኛ «ምናባዊ ምክንየታ» ልንለው ይሄን ፅሁፍ ቁጭ ብየ ደሴ ላይ ስፅፍ አዲስ አበባ ላይ ሽ ሰወች እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አመንኩ! በተቃራኒው እንዳምን ግን ነፃ ምርጫ የለኝም— በምክንያታዊነቴ ተገድቦል!— [በምናባዊው ምክንያታዊነት]። ነፃ-ምርጫህን በስንዝር ስትቀርበው ወደ ኢ—ምክንያታዊነት በክንድ ትቀርባለህ። ምናልባት ግን ኢ-ምክንያታዊ መሆንም የነፃ ምርጫችንን ማሳያ ይሆን? አላውቅም!
[— ስለ ሆብስ ሁለንታ፣ ግድፈቱና፤ በተራ ፍላጎታችን ስለተቃኘው ነፃነታችን... ]
«አነባለሁ» ብሎ መወሰን —ለማንበብ ጠንካራ በሆነ ፍላጎት መካበብ ነው። ፍላጎት ሲጠነክር ወደ ውሳኔ ይቀየራል። እናማ [Will] አለ ሆብስ « ከተራ ፍላጎት አይለይም»። ይሄ ተራ ፍላጎት ደግሞ በሁሉም እንሰሳቶች ዘንድ ስላለ ተለይቶ ለሰብእ የተሰጠ አይደለም። [Will] ወደ ተራ ፍላጎት ከወረደ ከቁጥጥራችን ውጭ ሆኗል የሚለውን ያስይዛል— የሁለተኛው ከዚሁ ነውና። ስለዚህ በሆብስ ሁለንታ ውስጥ ያሉ ፍጡራን እነሱ «Action of will» ያሉት እኛ «ልባዊ-ድርጊት» ያልነው የላቸውም። ታድያ የሁሉ ፍጡር ነፃ ምርጫ ከዚሁ ከቁጥጥሩ ውጭ ከሆነው፤ ቀድሞ ከተወሰነለት ተራ ፍላጎቱ የተመዘዘ ከሆነ ነፃነቱ ምኑ ላይ ይሆን? «የሰው ልጅ ነፃነት የሚያርፈው በተራ-ፍላጎቱና— እሱን በመፈፀሙ መካከል ባለው ነፃነቱ (መሰነካል ባለመኖሩ) ነው! ነፃ-ምርጫ ያልተደናቀፈ ተራ ፍላጎት ነው።» [Hobbesian Freedom]–ን ከቅድመ ውሳኔ ይልቅ ካቴና ይገድበዋል!!
« A free man, is he, that ... is not hindred to doe what he has a will to ... from the use of the word Free-will, no Liberty can be inferred of the will, desire or inclination, but the Liberty of the man; which consisteth in this, that he finds no stop, in doing what he has the will, desire, or inclination to doe.»³
የሆብስ ሃሳብኮ ጥሩ ነበር «የሰው ልጆ 'ነፃነት' አለው የሚባለው የፈለገውን ሁሉ መስራት ሲችል ነው» ነፃነቱን የሚያጣው ደግሞ «በፍላጎቱና— ፍላጎቱን በመፈፀሙ መካከል እንቅፋት ሲገባበት ብቻ ነው።» ግን የሰው ልጅ ነፃ ምርጫ ለማጣቱ ምክንያቱ ራሱ ፍላጎቱ ሆኖ ሲገኝ—[ Hobbesian Freedom] ይብረከረካል። ለምሳሌ፥ የእፅ ተጠቃሚወችን ውሰድ — የአለመጠቀም ነፃ ምርጫቸው በዕፅ ፍላጎታቸው ተገድቧል።
[—ፀሃፊው በነፃ ምርጫው እዚጋ የተወው! ምናልባት የሚቀጥለው ...
(© Ā৳ì৳⎝ª৳ì৳—)
______
₁–Henrik Walter, Neurophilosophy of Free Will, Pp. 4
₂— Thomas Pink, Free will: short introduction, Pp. 38
³–Thomas Hobbes, Leviathan, Chapter– 21, Pp. 145