ዝክረ ስበሀት
ከቅብጠታት አንድ ቀን ፣አቶ አልአዛር ሲያቀብጣቸው ውሻቸውን " ሁለት መለኪያ አረቄ የተቀላቀለበት ክትፎ አኮሞኮሙት ፡፡
… ‹‹እናንተ የሰው ልጆች ኮተታችሁ ሲበዛ !›› አላቸው
‹‹አረቄዋ ከመቼው ስራዋን ሰራች !›› እያሉ ውስጥ ውስጡን ‹‹እንዴት እባክህ?!›› ሲሉት
‹‹የልብሳችሁ ብዛት ! ሙታንታ-ከናቴራ-ሸሚዝ-ሹራብ-ኮት-ካፖርት-ባርኔጣ-ካልሲ-ጫማ-ቀበቶ-ጡት መያዣ! አንሶላ-ብርድልብስ-አልጋልብስ-ፎጣ! ኧረ ወድያ !ኮተታም ዘር!››
‹‹ ኧረ ባክህ እናንተስ?››
‹‹እኛማ ፀጉራችን በቃን ፡፡ ፀጉራችን ፣በቃይ ከውስጣችን !››
‹‹እሺ!!!››
‹‹ማበጠሪያ፣ፀጉር መያዣ፣ፀጉር መጠቅለያ፣የፀጉር ቅባት፣ የ…››
‹‹በቃህ አታንዛዛብኝ!››
‹‹ደሞ የቤታችሁ ጣጣስ ? ማድቤት -ምግብ ቤት-እንግዳ ቤት-ሽንትቤት-እቃቤት-ወንበር-ጠረቤዛ-ሶፋ-ምንጣፍ-አልጋ-ቁምሳጥን-አግድም ሳጥን! ሌላ ኮተት ዝባዝንኪ ግሳንግስ !››
‹‹ሸይጣን ይንገስብህና! እናንተሳ ባክህን ?››
‹‹እኛማ ምድር ወለላችን ሰማይ ጣሪያችን ፡፡ በቃ ፡፡››
‹‹ወይ ጉድ !››
‹‹ሳህን -ማንኪያ -ሹካ-ኩባያ-ብርጭቆ-ጠርሙስ››
‹‹በቃህ ! በቃንግዲህ!››
‹‹ድስት-ጋን-ገንቦ››
‹‹ኧረ ባክህ ይበቃል››
‹‹የግሳንግሱ የኮተቱ ብዛት ! ሰፌድ-መሶብ-አገልግል››
‹‹በቃ!››ብለው ጮሁበት
‹‹ኮተታም ዘር! ቅራቅንቦ!››
‹‹ቅራቅንቦ?››
‹‹ቅራቅንቦ-ሞፈር-ቀንበር-ኮርቻ-ወስፈንጥር-ወስፌ››
‹‹እሰይ የኛ አዋቂ››
‹‹ግሳንግስ ቅራቅንቦ ! ጋሪ-ቢስኪሌት-ዶቅዶቄ-መኪና-ባቡር-መርከብ-ኤሮፕላን-በሮኬት ጨረቃ ላይ መውጣት››
‹‹ዝም በል አልኩህ! ሰካራም የውሻ ልጅ!››
‹‹ጠላ-ጠጅ-አረቄ-ወይን-››ሲል አቶ አልአዛር ጆሮአቸውን ደፈኑ
‹‹አለዝያ ያላሰብኩትን ሌላ ኮተት ያረዳኛል ››ብለው እያሰቡ ፡፡ ትንሽ ቆየት ብለው እጃቸውን ከጆሮአቸው ሲየወርዱ
‹‹ክርስትና-እስልምና-ፍጥምጥም-ሠርግ-ተዝካር-ሰደቃ…››
‹‹ኧረ ስለማርያም ተወኝ !›› አሉት
‹‹ማርያም-ሚካኤል-አቦ-ራጉኤል-ጅብሪል…›
‹‹ዝም በልኮ ነው የምልህ! የውሻ ልጅ››
‹‹አለቻ ስድብኤል!››
ስቀው ሲጨርሱ ቀጠለ‹‹ገበሬ-ነጋዴ-ቄስ-ጠበቃ-ዳኛ-አናጢ››
‹‹ኧረ በህግ አምላክ ተወኝ!››
‹‹ደሞ የህጋቹ ብዛት ! ወንጀለኛ መቅጫ-ፍትኃ ብሄር-የባህር ንግድ-የስነስርአት-አቤት ግሳንግስ ኮተት !››
‹‹ልብ አርግ፣ዋ!››
‹‹ደግሞ የክሳችሁ አይነት ፣ሰካራም-ተሳዳቢ-አጭበርባሪ-ነብሰገዳይ-እጅ እላፊ-አፍ እላፊ…››
‹‹አሁንስ በቃ !›› አሉና ተነስተው አንስተዉት በሩን ከፍተው ውጭ አስቀምጠዉት ተመልሰው በሩን ዘጉት ፡፡
‹‹ሰካራም የውሻ ልጅ ! ›› እያሉ ግማሽ እየሳቁ ፣ለራሳቸው ሲመርቁላቸው አንድ መለኪያ አረቄ ቀዱ፡፡
ምንጭ፡ አምስት ስድስት ሰባት ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
Joni Tsegaye