#ለደካማ_ምዕመናን_የተጻፈ_ደብዳቤ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ "በታዋቂ" ሰዎች የሚደረግ ካሉበት ቤተ እምነት ወደ ሌላው ቤተ እምነት የሚደረግ ዝውውር እየተለመደ መጥቷል።
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት የቆየ ወደ ፕሮቴስታንት ማሕበር ሲቀላቀል፤ ኦርቶዶክሱ በሐዘን፤ ፕሮቴስታንቱ ደግሞ በደስታ ይንሳፈፋል።(በተመሳሳዩ ኦርቶዶክሱም እንዲሁ)
የአንድን ቤተ እምነት ሐሰተኝነትን ታዋቂ ሰው በመውጣቱ የምንመዝን ከሆንን ጴጥሮስ ኢየሱስን በመካዱ የኢየሱስን እውነት መሆንን እንጠራጠር ነበር፣ ዴማስም ዓለምን ወድዶ በመጥፋቱ የሐዋርያ ጳውሎስን አስተምህሮ በተጠራጠርን ነበር። ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም። እንዲሁም ደግሞ
የአንድን ቤተ እምነት ትክክለኛነትን ታዋቂ ሰው ወደዛ በመቀላቀሉ የምንመዝን ከሆነ ለወንጌል ብዙ ዋጋ የከፈለው ቱርቱሊያን የተቀላቀለበትን "የሞንታኒስ እንቅስቃሴን" እውነት ነው ብለን በተቀላቀልን ነበር።
የአንድን ቤተ እምነት ትክክለኝነት ሆነ ሐሰተኛነት እንደ pendulum በሚዘዋወሩ(በልጅነታቸው ዥዋዥዌ ባልተጫወቱ) ሰዎች አንመዝን።
ታዋቂ ሰው ከኦርቶዶክስ ወደ ፕሮቴስታንት ስለተቀላቀለ ብቻ ኦርቶዶክስን አናውግዝ፤ እንዲሁም ደግሞ ኦርቶዶክሶችም ታዋቂ ሰው ከፕሮቴስታንት ወደ ኦርቶዶክስ ስለሄድ አታውግዙን/ልክነታችሁንም አታረጋግጡልን።
መለኪያችን ግለሰቦች ሳይሆኑ፤ የቤተ እምነቱ አስተምህሮ ነው። አስተምሮ ላይ መነጋገር የአዋቂ ነው።
ዛሬ መጣ ያሉት ነገ ሊወጣ ይችላል፤ ፕሮቴስታንቱም ዛሬ መጣ ያሉት ነገ ሊወጣ ይችላል። በመውጣት እና መግባታቸው ደማችሁ ዝቅ እና ከፍ የሚል ከሆነ በሽተኛ ናችሁ እና ታከሙ።
የወጣው ምን አጥቶ ነው የወጣው የሚለው እና ምን አግኝቶ ነው የተመለሰው የሚለው የሁለቱም ጎራዎች የቤት ሥራ ነው።
ደግሞ ወደ እኛ ከመጣ በኌላ በገንዘብ አልደገፍነውም ብር ስላጣ ነው የተመለሰው እያላችሁ ምክንያት የምትደረድሩ ሆይ፤ ለእናንተም ፈራሁ፤(ነገ ምዕመን አልደገፈኝም ብለህ ልትክድ ያለኸው አንተ ነህና) የገባን ነገር እውነት ነው ብለን ካመንን እንኳን ማጣትን እንኳን መራብን ለጌታ መሞትን መምረጥ የለብንም እንዴ? ወይስ አሁን ምናገለግል በጣም ደልቶን እያገለገልን ነው። (ሰዎቹ ከኦርቶዳክስ ሲወጡ ብር ፈልገው ነው ይባላል፤ ወደ ኦርቶዶክስ ሲመለሱ ግን እኛ ጋር ብር ስላጡ ነው ይባላሉ።) ብቻ እኛ ያለንን ጥለን የምንከተለውን አምላክ እንጂ የሌለን እንዲሰጠን የምንከተለው አምላክ የለንም።
[ልብ አድርጉልኝ ስለ ዲያቆን ሐዋዝ እየተናገርኩኝ አይደለም። ምክንያቱም እሱ ፕሮቴስታንት እንደሆነ አላውቅምና]
ብቻ እንደ እኔ አንድ ሰው ኤቲስት ከሚሆን ሙስሊም፤ ሙስሊም ከሚሆን ደግሞ ጆቫ ዊትነስ/ሐዋርያት ቢሆን፤ ጆቫ ዊትነስ/ ሐዋርያት ከሚሆን ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ/ ካቶሊክ ቢሆ፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ/ ካቶሊክ ከሚሆን ኦርቶዶክ ተሐድሶ ቢሆን፤ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ከሚሆን ፕሮቴስታንት ቢሆን የተሻለ ነው እላለሁ።
[በሳል ምዕመን አይሳደብም፤ አይነጫነጭም፤ ጸጋና ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን]
Prist kibru ገፅ የተወሰደ!