What is Trojan Horse Virus ?
🧩 የትሮጃን ፈረስ ማልዌር ምንድን ነው? እንዴስ ይሠራል?
🧩 የትሮጃን ፈረስ ወይም ባጭሩ ትሮጃን ማልዌ #Trojan malware የኮምፒውተር ስርዓትን ለማግኘት( ለማጥቃት) ራሱን እንደ ህጋዊ/ጤናማ ሶፍትዌር የሚያስመስል የማልዌር ዓይነት ነው። ትሮጃን አንዴ ከተጫነ ወሳኝ መረጃዎችን መስረቅ፣ የተጠቃሚ እንቅስቃሴን መከታተል እና ለሳይበር ወንጀለኞች ያልተፈቀደ የርቀት መዳረሻን ማመቻቸት እና የመሳሰሉ ተንኮል አዘል ተግባራትን ማከናወን ይችላል።
🧩 እንደ ሌሎች የኮምፒውተር ቫይረሶች ወይም ዎርሞች (worms) ትሮጃኖች እራሳቸውን አያባዙም። ይልቁንም ስርጭታቸው በማህበራዊ ምህንድስና ዘዴዎች እና በተጠቃሚዎች መስተጋብር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ምንም ጉዳት የሌላቸው በሚመስሉ የኢሜይል አባሪዎ(attachments) ውስጥ ተደብቀው ወይም በሀሰተኛ የሶፍትዌር ማሻሻያ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
🧩 ትሮጃን ማልዌር የተጎጂዎችን የኮምፒዩተር ስርዓት ለማግኘት እራሳቸውን ልክ እንደ ትክክለኛ መተግበሪያዎች ወይም ፋይሎች ማስመሰል ይችላሉ። አንዴ ከተጫኑ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ ለምሳሌ ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ መስረቅ፣ ስርዓቱን ማወክ/ ማስተጓጎል ወይም የሳይበር ወንጀለኞች ከርቀት ዲቫይሶቻችንን እንዲቆጣጠሩት መፍቀድን ያጠቃልላል።
🧩 የትሮጃን ማልዌሮች ሰርጎ ለመግባት የሚጠቀሙበት ዋና ዘዴ ማህበራዊ ምህንድስና (social engineering) ነው። የሳይበር ወንጀለኞች ተጠቃሚዎች ማልዌሩን እንዲያወርዱ እና እንዲጭኑ ለማታለል ብዙ ጊዜ እንደ ማስገር (phishing) ኢሜይሎች እና ሀሰተኛ የሶፍትዌር ማዘመኛ ያሉ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ።
🧩 በአንዳንድ አጋጣሚዎች ትሮጃኖች በተንኮል አዘል ድረ-ገጾች ሊሰራጩ ወይም ከሌሎች ምንም ጉዳት የሌላቸው ከሚመስሉ መተግበሪያዎች ጋር ሊጣመሩ ይችላሉ።
🧩 ትሮጃኖች ካቀዱት የጥቃት ዒላማ ስርዓት ውስጥ ከገቡ በኋላ በድብቅ ተንኮል አዘል ተግባራቸውን ይፈጽማሉ። ላልተፈቀደ መዳረሻ የጀርባ በር (Back door) ሊከፍቱ፣ በጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር እንዳይታወቁ የደህንነት ቅንብሮችን ሊቀይሩ ወይም የጎላ ጥርጣሬ ሳይፈጠር መረጃዎችን ሊመነትፉ ይችላሉ። በመሆኑም ግለሰቦች እና ተቋማት ሊደርሱ የሚችሉ ጉዳቶችን በመገንዘብ እና ጠንካራ የሳይበር ደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር ረገድ ንቁ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
📌 በቀጣይ ጽሁፋችን ስለ ትሮጃን ማልዌር ዓይነቶች የምንመለከት ይሆናል
CompuTech
DifferentVideos