የጋዜጠኛ መአዛ ብሩ የንባብ ልምድ
‹‹ አባቴ ትጉህ አንባቢ ነበር፡፡ ዘወትር ወደ ቤት ፤ ብዙ መፅሐፍትና ጋዜጦች ገዝቶ ያመጣል፡፡ ይዞ የመጣቸው ጋዜጦች አንብቤ ስጨርስ በእጄ እንድገለብጥ ያደርጋል፡፡ ይህን የሚያደርገው … ማንበቤን ለአዕምሮዬ ፤ መጻፌን ለእጅ ጽሑፌ ማማር ከማሰብ ነበር፡፡
ዘጠኝ አመት ሲሆነኝ ከሂርና አዲስ አበባ መጥቼ ሴንት ሜሪ አዳሪ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ ለከተማውና ለተማሪዎቹ እንግዳ ስለሆንኩኝ ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር፡፡ ለዚህም ስል ጋዜጦችና መጻሕፍት በየቀኑ አነብብ ነበር፡፡ አነብባቸው ከነበሩት መሃል …የዛሬይቱ ና አዲስ ዘመን ጋዜጦች ይጠቀሳሉ ›› የምትለን መአዛ ብሩ ናት…
የሸገር ሬዲዮ ጣቢያ መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛ የሆነችው መአዛ ብሩ ቅዳሜን በጨዋታ ፤ እሁድን በሸገር ካፌ የምታስናፍቅ ድንቅ ጋዜጠኛ ናት፡፡ መአዛ ግሩም በሆኑ የጥያቄ ለዛዎቿና ስለእንግዳዎቿ የምታውቅበት ልክ በአድማጮቿ ዘንድ ከሚያስወድዷት ነገሮች መሃል ናቸው፡፡ ስለ እንግዶቿ መረጃ ልታገኝ ከምትችልባቸው መንገዶች እና ከእንግዶቿ ጋር የምታወራበትን የቋንቋ ውበት ለመፍጠር እንግዶቿ ከሆኑት ነገር በጥቂቱም ማወቅ ይጠበቅባት ነበር፡፡ ለዚህ ቀዳሚ መፍትሄው ደግሞ ማንበብ ነው፡፡ የግል የንባብ ልምዷ እንዳለ ሆኖ ከደራሲ ጋር ለማውራት የድርሰትን ውጤቶች በጥቂቱም ቢሆን ማንበብ ይፈልጋል …
ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ከማን ጋር ያደረገችው ቃለ መጠይቅ ይበልጥ ደስ ይላችኋል?… ኮሜንት አድርጉልን