‹‹ ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው፡፡ ፆታ የሚያበላልጥና የሚያተናንስ ነገር የለውም፡፡ ›› አውራምባ
አውራምባ በዙምራ ኑሩ በ1964 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን የራሱ የሆነ ስርዓትና ባሕሎች ያሉት ማህበረሰብ ነው፡፡ ነዋሪዎቹ አውራምባን ሲገልጹት የእኩልነት፣ የመከባበር፣ የመደማመጥና የመቻቻል አካባቢ ነው ይሉታል።
አውራምባን ከሌሎች የማህበረሰብ ስርዓቶች ምን ልዩ ያደርገዋል?
• 'የሴቶች ሥራ' እንዲሁም 'የወንዶች ሥራ' ብሎ ነገር አለመኖሩ፡፡ አንዱን ፆታ አሳንሶ ሌላውን የሚያስበልጥ የሥራ ክፍፍልን የማይደግፍ ፤ ችሎታን መሰረት ያደረገ የስራ ባሕል ያለው ማህበረሰብ መሆኑ፡፡
• ጋብቻን በተመለከተ የተጋቢዎች ፈቃድ ላይ መሰረት ያደረገ እንዲሆን ያስተምራል፡፡
• ‹‹ የሀሳብ ልውውጥ ሲኖር አንድ የተሻለ ሀሳብ ይወለዳል ›› ብለው ስለሚያምኑ አውራምባዎች ለውይይት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡
• አውራምባ ስርቆትን ፤ ውሸት መናገርን ፤ ልመናንና ስንፍናን እንደ ነውር ይመለከታል፡፡
• ፆታ ያልገደበው የሀሳብና የውይይት መድረክ እንዲኖር ይፈቅዳል፡፡
• ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በፅኑ ይቃወማል፡፡
• ሁሉም ቤተሰብ በየ15 ቀን ውይይት ያደረጋል። ይህም የውይይት ባህል የእድሜ ልዩነት የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው ውስጥ አንዳች ጠቃሚ ሀሳብ አለ ‹‹ ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ተወያይተው ችግር የመፍታትና አዲስ ሀሳብ የማፍለቅ መብት አላቸው ›› ብሎ ያምናል፡፡
• እኔን አይመለከተኝም የሚባል ነገር የለም፤ ሁሉም ይሠራል። አንድ ሰው የሚያገኘውን እውቀት 'የኔ ብቻ' አይልም፤ ለሁሉም ያካፍላል።
• የመጨረሻውና ዋነኛው የአውራምባ ማህበረሰብ የሚታወቅበት እሴት ፡- ገንዘብና ጊዜ የሚባክንባቸውን የተንዛዙና አላስፈላጊ ወጪ የሚወጣባቸው የሰርግና የሀዘን ድግሶችን በልክ እንዲሆኑ የሚያስተምሩበት መርሃቸው ነው፡፡