ይቅር መባባል ያስፈልገናል!
በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ አብርሃም ሊንከን የጎላው ለምንድነው? በዘመኑ ያሳለፋቸው ጠንካራ አሻራዎቹ፤ በክፉና ደግ ቀን የወሰናቸው ጠንካራ ውሳኔዎች ይሄንን ገናናነት እንዲሰጡት እድርጓል፡፡
ሊንከን በአሜሪካ ታሪክ ስመ-ጥር ይሁን እንጂ አሜሪካንን አላገኛትም ወይም አላቋቋማትም፡፡ በዋናነት እነ ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ቶማስ ጀፈርሰን፣ ቤንጃሚን ፍራንክሊን እና የመሳሰሉት ናቸው ከእንግሊዝ እጅ መንጭቀው አሁን አሜሪካ ብለን የምንጠራው አገር ያቋቋሙት። ሊንከን ግን …አሜሪካ በእርስበርስ ጦርነቱ በፈራረሰች ጊዜ የነበረ ፕሬዚዳንት ነው፡፡
አገር የካዱ ጀነራሎች ተማርከው ለመጨረሻ ጊዜ በተገኙበት የካቢኔ ጉባኤ ላይ ሊንከን የተናገረው የሰለጠነ ሀሳብ ሁሉንም ያስደንቃል፣ ያረካል፣ ሁሌም ይታወሳል፡፡
“የገደለ ይገደል!” "ዐይን ያጠፋ ዐይኑ ይጥፋ!"… ብለው የምያምኑ ብዙ የዓለም መሪዎች ነበሩ፣ ሊንከን ልብ ግን እንደዚያ አልነበረም። ይቅርታ ማድረግ ይቻላል ብሎ የሚያምን መሪ ነው፡፡ ይህንን ያንፀባረቀው ደግሞ የመጨረሻው የካቢኔ ጉባኤ ላይ ነበር፡፡ “ሀገሪቱን አምሰዋል፣ ለመገንጠል መክረዋል፣ ጦር አንስተዋል ፣ ለብዙዎች ህይወት መጥፋት መንስዔ ሆነዋል" …የተባሉ “አሸባሪዎች” ቅጣት ምንድነው?” ተብሎ ሲጠየቅ፡- “እስከ ዛሬ ድረስ የፈሰሰው ደም በቂ ነው፣ ከእንግዲህ በኋላ የማንም ደም እንዲፈስ አልፋቅድም” ነበር ያለው፡፡ ታዲያ ይህ የይቅርታ ቃል በአሜሪካውያን የፈጠረው ስሜት ቀላል አልነበረም፡፡ በቁስል ላይ ቁስል፣ በቂም ላይ ቂም ከመፍጠር ይልቅ፣ በይቅርታ ዘይት ቁስልን ማድረቅ ይሻላል፡፡ ይሄንንም በማድረጉ በዓለም ካርታ ላይ በደማቅ የተሳለች አገር ለመምራት በቃ።
እኛስ በሊንከን ቦታ ብንሆን ምን እንዲወስን እናደርግ ነበር ወይም ምን እንወስን ነበር? ይሄ ለሁላችንም ጥያቄ ሊ