Dashen Bank


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


Dashen Bank is one of the leading banks in Ethiopia with over 860 branches and banking outlets.
Visit our official facebook site @ https://www.facebook.com/DashenBankOfficial
Visit our Website:https://dashenbanksc.com

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


በቀን 20 ሺህ ብር ማውጣት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

የዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ ግሪን ካርድ ከዳሸን ባንክ በተጨማሪ በማንኛውም ባንክ ኤ.ቲ.ኤም ላይ በቀን እስከ 20,000 ሺህ (ሃያ ሺህ) ወጪ እንዲያደርጉ ያስችልዎታል፡፡

ለበለጠ መረጃ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://dashenbanksc.com/card-services/

#DashenBank #Dashen #Amex_Green_Card #Ethiopia #ኢትዮጵያ #card

6.5k 0 12 37 84

የኃዘን መግለጫ

9.7k 0 17 40 235

ሶስተኛው ምዕራፍ የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ሥልጠና ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ

ዳሸን ባንክ በስራ ፈጠራ ዘርፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየተገበረ ባለው ዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር 3ኛውን ምዕራፍ በ10 ከተሞች የሚያካሂድ ሲሆን የመጀመሪውን ቅድመ ውድድር ስልጠና በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል፡፡

የቅድመ ውድድር ስልጠናው የስራ ፈጠራ ፅንሰ-ሃሳብ ቀረጻ፤ የፈጠራ ንድፈ ሃሳብ አዘገጃጀት እና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ግንዛቤን የሚስጨብጥ የማነቃቂያ ስልጠና ነው፡፡

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎት እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለዉ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት ዳሸን ባንክ ከሌሎች ባንኮች በመቅደም በሀገር አቀፍ ደረጃ የስራ እድል ፈጠራ ውድድርና ስልጠና በማቅረቡ አመስግነዋል፡፡ 

የዳሸን ባንክ ማርኬቲንግና ብራንዲንግ ዳይሬክተር አቶ እንዳለ ገ/ስላሴ በበኩላቸው ሥልጠናው የስራ-ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ሃሳባቸውን በምን መልኩ ማቅረብና ወደ ሥራ መቀየር እንዳለባቸው የሚያግዝ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ሐዋሳ ቀጠና ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ጴጥሮስ ሞገስ እንደገለጹት፣ በሁለተኛ ምዕራፍ ውድድር ላይ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ አሸንፈው የተሸለሙት የሀዋሳ ከተማ ተወዳዳሪዎች መሆናቸውን አስታውሰው በዚህኛውም  ምዕራፍ ላይ የሚሳተፉ የከተማዋ ተወዳዳሪዎች የእነሱን ፈለግ በመከተል ጠንካራና ንቁ ተፎካካሪ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ዳሸን ባንክ በአንደኛውና በሁለተኛው ምዕራፍ የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድሮች በሺዎች የሚቆጠሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ወጣቶችን የስራ ፈጠራ ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና የሰጠ ሲሆን ለውድድሮቹ አሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት እና የፋይናንስ ድጋፍ አድርጓል


2 Jobs available

For the latest job opening, please follow our LinkedIn Page:
https://www.linkedin.com/company/dashen-bank-official-page


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

ሐምሌ 10 እና 11፣ 2016 ዓ.ም በተካሄደው ዓመታዊው የስራ አስኪያጆች ጉባኤ ላይ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቀጠና እና አካባቢ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ቅርንጫፎች እውቅና ተሰጥቷል። ዳሸን ባንክ ለአሸናፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ በቀጣይም መላው የባንኩ ማህበረሰብ ባንካችን አመርቂ ውጤት ያስመዘገብ ዘንድ ጥረት እንዲያረግ በአክብሮት እንጠይቃለን።

11.7k 0 19 25 140

ልዩ የተማሪዎች የቁጠባ ሒሳብ

የከፍተኛ ትምህርት ለሚከታተሉ ሁሉ የሚከፈት የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን ለሚቆጥቡት ገንዘብ ጠቀም ያለ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብለት እና የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የሚስችልዎ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:https://dashenbanksc.com/other-special-deposit/

#studentsaving #saving #ኢትዮጵያ #DashenBank #Dashen #Bank


ውድ ደንበኞቻችን

ስለ ሸሪክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎታችን ያልዎትን ገንቢ ሃሳብ እና አስተያየት ይግለጹልን፡፡

#Ethiopia #ኢትዮጵያ #DashenBank #Dashen #Bank #sharik #IFB


28ኛው የዳሸን ባንክ ስራ አስኪያጆች ጉባኤ እየተካሄደ ነው

28ኛው የዳሸን ባንክ ስራ አስኪያጆች ጉባኤ ዛሬ በሚሊንየም አዳራሽ ተጀምሯል።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ያለፈው በጀት አመት ባንኩ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበበት እንደነበር ገልጸዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የአዲሱ በጀት አመት ዕቅድ እና የባንኩ የተለያዩ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶች ውይይት ይደረግባቸዋል።

ዳሸን ባንክ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በከፈታቸው ከ870 በላይ ቅርንጫፎቹ ዘመናዊና ደንበኛ ተኮር አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

14.8k 0 30 61 313

10 Jobs available

For the latest job opening, please follow our LinkedIn Page:
https://www.linkedin.com/company/dashen-bank-official-page


ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!

አጭበርባሪዎች ከዳሸን ባንክ የተደወለ በማስመሰል ደንበኛውን ለጉዳት የሚያጋልጥ የግል መረጃዎችን እንዲያጋሯቸው በማድረግ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ስርቆት ለመፈፀም ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን በባንካችን አሠራር መሰረት፣ ከሞባይል ባንኪንግ(አሞሌ) አገልግሎት ጋር በተያያዘ እርስዎ በአካል ወደ ባንካችን ቅርንጫፎች ሳይመጡ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት የለም፡፡

መሰል ጥሪዎች ሲደርስዎት የተደወለበትን ስልክ ቁጥር በነጻ የስልክ መስመር 6333 ወይም አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ያመልክቱ፡

#Ethiopia #ኢትዮጵያ #DashenBank #Dashen #Bank #amole #secure #cybersecurity #security #informationtechnology #Compliance #Risk


በዳሸን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት አመታዊ የድንገተኛ አደጋ መከላከል ልምምድ ተካሄደ

በዳሸን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት አመታዊ የድንገተኛ አደጋ መከላከል ልምምድ (Annual Fire Safety and Drill Exercise) ዛሬ ተካሂዷል፡፡

ይህ ልምምድ የድንገተኛ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት አቅምን ለመገንባት እንዲቻል የሚከናወን መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና በአደጋ ጊዜ ቺፍ ኢቫኩዌሽን ኦፊሰር አቶ አስፋው አለሙ አመልክተዋል፡፡

የዳሸን ባንክ የደህንነትና ሰኪውሪቲ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ሃብታሙ ኤባ ልምምዱ በባንኩ አደጋ ቢከሰት የመከላከል አቅምን የሚያሳድግ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ ልምምድ ቀደም ብሎ በድንገተኛ አደጋ መከላከልና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለባንኩ ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያ መሳሪያዎች የተገጠሙለት ሲሆን ከአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል፡፡

14.9k 0 24 40 213

ሐላል የሆነ ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይፈልጋሉ?

የሙዳረባህ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ(የኢንቨስትመንት ሒሳብ) ይህ የሒሳብ አይነት በግለሰቦች፣በዕድሮች፣በተለያዩ ማህበራቶች፣ ከሃገር ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊከፈት ይችላል፡፡የሙዳረባህ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሒሳብ ደንበኞች ትርፍና ኪሳራን ለመካፈል በተወሰነ የጊዜ ገደብ የሚከፍቱት ሒሳብ ነው።

#DashenBank #Dashen #Bank #Ethiopia #ኢትዮጵያ #IFB #sharik #InterestFreeBanking #finance #banking #halal #halalbusiness #finance


የዳሸን ከፍታ 3ተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር ምዝገባ ሊያልቅ 3 ቀን ብቻ ቀረው

ለበለጠ መረጃ የዳሸን የጥሪ ማዕከል (6333) ይደውሉ ወይንም ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይጎብኙ!

Facebook
| Instagram | X | Linkedin | @dashenbankofficial' rel='nofollow'>Tiktok | @dashenbank' rel='nofollow'>Youtube

#DashenBank #Dashen #Bank #Ethiopia #ኢትዮጵያ #dashenkefta #entrepreneur #registration


በፓሪስ በሚደረገው የ2024 ኦሎምፒክ ለሚሳተፉት የአገራችን ዕንቁ አትሌቶች የመሸኛ ሙዚቃ ኮንሰርት ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ተዘጋጅቷል። የኮንስርቱን ትኬት በአቅራቢያዎ በሚገኙ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች፣ በአሞሌ ዋሌትና በአሞሌ ቴሌግራም ቦት መግዛት እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በታላቅ ደስታ ነው።

#parisolympics2024 #ethiopia #olympics #athletics #amole #DashenBank


ይጠንቀቁ!

በዳሸን ባንክ ስም በተከፈቱ ሃሰተኛ የሊንክዲን ገጾች እንዳይታለሉ ይጠንቀቁ!

ትክክለኛውን የዳሸን ባንክ ሊንክዲን ገፃችንን ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:-

https://www.linkedin.com/company/dashen-bank-official-page


#DashenBank #Dashen #Bank #Ethiopia #ኢትዮጵያ #Fake #scam #scamalert #fakepage


ውድ የ12ኛ ክፍል የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ፤ ፈተናውን በስኬት በማለፍ የልፋታችሁን ፍሬ የምታገኙበት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኛለን።

Facebook | Instagram | X | Linkedin | @dashenbankofficial' rel='nofollow'>Tiktok | @dashenbank' rel='nofollow'>Youtube

#ethiopiaexam #ethiopiannationalexam #exitexam #DashenBank #Dashen #Bank #Ethiopia #ኢትዮጵያ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኦንላይን ሲኒማ መተግበርያ Tele Tv፤ ዳሽን ባንክ የአለም አቀፍ ክፍያ አጋር መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።

#DashenBank #Bank #OnlineTV #Movies #Ethiopia #ኢትዮጵያ


አጭበርባሪዎች ከዳሸን ባንክ የተደወለ በማስመሰል ደንበኞችን ለጉዳት የሚያጋልጥ የግል መረጃዎችን እንዲያጋሯቸው በማድረግ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ስርቆት ለመፈፀም ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን በባንካችን አሠራር መሰረት፣ ከሞባይል ባንኪንግ(አሞሌ) አገልግሎት ጋር በተያያዘ እርስዎ በአካል ወደ ባንካችን ቅርንጫፎች ሳይመጡ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት የለም፡፡ መሰል ጥሪዎች ሲደርስዎት የተደወለበትን ስልክ ቁጥር በነጻ የስልክ መስመር 6333 ወይም አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ያመልክቱ፡፡

#DashenBank #Dashen #Bank #Ethiopia #ኢትዮጵያ #amole #secure #cybersecurity #security #informationtechnology

18 last posts shown.