አቅጣጫ የሳተ ቁጣ (Misdirected Anger)
አቅጣጫ የሳተ ቁጣ ማለት፣ ቁጣችን በአንድ ሰው ወይም በአንድ ሁኔታ ምክንያት ቢነሳም፣ ያንን ቁጣ ከችግሩ ጋር ያልተያያዘ ሌላ ሰው ላይ ማውጣት ነው።
በሌላ አገላለጽ፣ ቁጣው እውነተኛ ነው፤ ነገር ግን የቁጣው አቅጣጫ የተሳሳተ ነው።
እንዴት ይከሰታል?
አንዳንድ ጊዜ የቁጣችንን እውነተኛ ምንጭ መጋፈጥ አስቸጋሪ ስለሚሆንብን፣ ቁጣችንን በቀላሉ ልንጋፈጠው በምንችለው ሰው ላይ እናወጣዋለን።
ለምሳሌ፦
• በሥራ ቦታ አለቃችሁ አስቸግሯችሁ፣ ወደ ቤት መጥታችሁ በትዳር አጋራችሁ ላይ ትቆጣላችሁ።
• በራሳችሁ ላይ ተስፋ ቆርጣችሁ፣ ልጆቻችሁን ከመጠን በላይ ልትወቅሱ ትችላላችሁ።
• አንድ ሰው አዋርዷችሁ፣ ቁጣችሁን ግን በሌላ ንጹሕ ሰው ላይ ታወጡታላችሁ።
• የገንዘብ ችግራችሁ አበሳጭቷችሁ፣ ስሜታችሁን ግን በአካባቢህ ባሉ ሰዎች ላይ ትገልጻላችሁ።
• ቀደም ሲል የተከማቸ የውስጥ ቁስል ኖሮባችሁ፣ ዛሬ በአንዲት ትንሽ ክስተት ምክንያት ትልቅ የቁጣ ስሜት ትገልጻላችሁ።
አቅጣጫውን የሳተ ቁጣ አደገኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ለእኛ ቅርብ እና ጥሩ የሆኑ ሰዎችን ስለምንጎና በሂደቱም ስለምናጣቸው ነው፡፡
ለሌላው ጊዜ ከመቆጣታችሁ በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችሁን ጠይቁ፡-
1. የዚህ ቁጣ እውነተኛ ምንጭ ማን ወይም ምንድነው?
2. የእኔ የቁጣ ምላሽ ከተፈጠረው ነገር ጋር የሚመጣጠን ነው?
3. ከዚህ በፊት የተፈጠረ ነገር የዛሬን ስሜቴን እየጎዳው ይሆን?
4. በእርግጥ ያስቆጣኝ ሰው ላይ ነው የተቆጣሁት፣ ወይስ ከሌላ ቦታ የመጣ ቁጣ ተሸክሜ ነው የመጣሁት?
ትክክለኛውን ስሜት፣ በትክክለኛው መጠን፣ ጊዜ፣ ቦታ እና በትክክለኛው ሰው ላይ መግለጥን እንማር!
https://m.youtube.com/user/naeleyob623