....እኔ ወድሻለሁ...
እኔ ወድሻለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት
እንደዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት፤
እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ፤
እኔ ወድሻለሁ
እንደመቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን።
በዉቀቱ ስዩም
@የፍቅር ቃል
እኔ ወድሻለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት
እንደዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት፤
እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ፤
እኔ ወድሻለሁ
እንደመቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን።
በዉቀቱ ስዩም
@የፍቅር ቃል