⭐️በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ።
⭐️ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤
⭐️የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፤ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ።
⭐️ምኞታችሁ ልክ የለውም
⭐️አምሮታችሁ ብዙ ነው ።
⭐️የአማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል ።
⭐️ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ
⭐️የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ ⭐️ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱ በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ ።
⭐️ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ ፤ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም ⭐️ሁሉ አላችሁ ፤ግን ባዷችሁን ናችሁ
🙊ሃይማኖት 🙊እንጂ 🙊እምነት 🙏የላችሁም !"
👇ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤ እናም ወደ ኋላ ስለ ታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል ። ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትንና የተሸናፊነት ትርጉም በአንድ ላይ የያዙ ሃውልቶች ታቆማላችሁ
እመጓ
ገፅ 162