TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
𝐄𝐓 |ነፃ|CRYPTO+

24 Aug, 16:19

Open in Telegram Share Report

ከ100 በላይ የዓለም ቆንጃጅት በሩት ታሪክ አብረው እንባቸውን አፈሰሱ"

ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ሩት ይርጋለም በታላቁ የዓለም አቀፍ የውበት ውድድር ላይ የሀገሯን ስምና ባንዲራ በኩራት ከፍ አድርጋ በማስጠራት ላይ ትገኛለች።

ሩት ወደ ቬትናም ለሚስ ወርልድ ውድድር ለመጓዝ አንድ ሳምንት ብቻ ሲቀራት ነበር በህይወቷ ውስጥ እጅግ አሰቃቂና ልብ ሰባሪ ነገር የገጠማት። በጣም የምትወዳት ውድ እህቷ ቅዱሳን፣ በቅርብ ጓደኛዋ እና በጓደኛዋ ፍቅረኛ አማካኝነት እጅግ በሚዘግንን ሁኔታ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሞባት ህይወቷ አልፏል። ይህንን ሊታሰብ የማይችል ከባድ የሀዘን እዳና የልብ ስብርባሪ ተሸክማ ነው ሩት ሀገሯን ለመወከል መድረክ ላይ የቆመችው።

ይህን አሰቃቂ ታሪኳንና የደረሰባትን መራራ ሀዘን በመድረኩ ላይ ከ100 በላይ ለሚሆኑ የዓለም ቆንጃጅትና ታዳሚዎች ልብ በሚነካ ንግግሯ ስታጋራ፣ ታሪኳን ያደመጡት የዓለም ቆንጃጅት በሙሉ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው አብረዋት በእንባ ተራጭተዋል፤ መድረኩም በሙሉ በለቅሶና በሀዘን ተሞልቷል።

ሩት እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት ስታለቅስ፣ የየሀገራቱ ተወካዮችና ታዳሚዎቹ በሙሉ ከመቀመጫቸው ተነስተው በእንባ ታጥበው በታላቅ ጭብጨባ ብርታቷንና ጥንካሬዋን አደንቀውላታል።

"በቅርብ ሰው እንዲህ ያለ አሰቃቂና ከባድ የሀዘን ጭንቅ ደርሶባት፣ የልቧን ቁስል ችላ ሀገሯንና ህዝቧን ለማስጠራት በጽናት መቆሟ ከወዲሁ ትልቅ አሸናፊ ያደርጋታል!" ሲሉ በርካታ ታዳሚዎች በለቅሶ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ሩት ንግግሯን ስታጠናቅቅ ለሞተችው እህቷ የላከችው "ቅዱሳን እወድሻለሁ..." የሚለው ልብ የሚነካ ቃል የብዙዎችን እንባ አፍስሷል።
ይህንን የፅናትና የጥንካሬ ምሳሌ የሆነችውን እህታችንን ደግፈን እስከ መጨረሻው አሸናፊ ለማድረግ ሁላችንም ድምፅ እንስጣት!

449 0 0 3
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot