Enatye
ያኔ ሕፃን ሆኜ ነበረ የማዉቃት
ትዝ ይለኛል እኔ ስሞላቀቅባት
አስታዉሠዋለሁ የዛን ጊዜ ሕይወት
በጀርባዋ አዝላኝ አቅፋኝም በደረት ስታደርገኝ ቀበጥ
ደሞ ስበጠብጥ ሳጠፋ ያለ ቅጥ
በጣም ተበሣጭታ ትቆጣኝ ነበረ እናቴ በስስት
ከዛ አለቅሳለሁ ክፉኛ አምርሬ.... እንድታባብለኝ አይን አይኗን እያየዉ
እስዋም ትመጣለች አላስችልሽ ብሏት.... ቀኔን ልታስዉበዉ
አሁን አድግያለሁ ትልቅ ልጅ ሆኛለሁ
እንደ ድሮነቴ የልጅነት ወዜን ዛሬ አጥቻለሁ
ግን እናቴ አሁንም ያ እንቡጥነቴን ታየዋለች ባይኗ
አሁንም ትንሽ ነኝ ገና ልጅ ነኝ ለሷ
እናትዩ ፍቅሬ ወልደሽ ያሳደግሽኝ
መንገዴን አቃንተሽ ከችግሮቼ ፊት ከለላ ሆነሽኝ
እናትዬ አለሜ ጥብና ብልሕ ሁሉን አስተማሪ
ደስተኛ ያድርግሽ ከረጅም እድሜ ጋር ዘመንሽን ፈጣሪ
በ Kumi 🍁
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@audio_poems
@audio_poems
@Audio_poem_discussion
╔════════════╗
👉JOIN: @BegitimEnawga
👉JOIN: @BegitimEnawga
╚═════════════╝
ያኔ ሕፃን ሆኜ ነበረ የማዉቃት
ትዝ ይለኛል እኔ ስሞላቀቅባት
አስታዉሠዋለሁ የዛን ጊዜ ሕይወት
በጀርባዋ አዝላኝ አቅፋኝም በደረት ስታደርገኝ ቀበጥ
ደሞ ስበጠብጥ ሳጠፋ ያለ ቅጥ
በጣም ተበሣጭታ ትቆጣኝ ነበረ እናቴ በስስት
ከዛ አለቅሳለሁ ክፉኛ አምርሬ.... እንድታባብለኝ አይን አይኗን እያየዉ
እስዋም ትመጣለች አላስችልሽ ብሏት.... ቀኔን ልታስዉበዉ
አሁን አድግያለሁ ትልቅ ልጅ ሆኛለሁ
እንደ ድሮነቴ የልጅነት ወዜን ዛሬ አጥቻለሁ
ግን እናቴ አሁንም ያ እንቡጥነቴን ታየዋለች ባይኗ
አሁንም ትንሽ ነኝ ገና ልጅ ነኝ ለሷ
እናትዩ ፍቅሬ ወልደሽ ያሳደግሽኝ
መንገዴን አቃንተሽ ከችግሮቼ ፊት ከለላ ሆነሽኝ
እናትዬ አለሜ ጥብና ብልሕ ሁሉን አስተማሪ
ደስተኛ ያድርግሽ ከረጅም እድሜ ጋር ዘመንሽን ፈጣሪ
በ Kumi 🍁
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
@audio_poems
@audio_poems
@Audio_poem_discussion
╔════════════╗
👉JOIN: @BegitimEnawga
👉JOIN: @BegitimEnawga
╚═════════════╝