እንደ ዓለም ባንክ ትንበያ በ2030 እ.አ.አ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ከ230 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ሥራዎች ይፈጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ የሥራ ዕድሎች በፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የዲጂታል ኢኮኖሚ አማካኝነት የሚፈጠሩ ናቸው።
እነዚህን እድሎች በአግባቡ ለመጠቀም መካከለኛ እንዲሁም የላቀ የዲጂታል ክህሎት መኖር ግድ ይላል። በተጨማሪም መሰረታዊ የፋይናንስ እና የዲጂታል እውቀት በእጅጉ ያስፈልጋል።
አሁን ላይ በአህጉሪቱ ከፍተኛ የዲጂታል ክህሎት ክፍተት ከመኖሩም በተጨማሪ በጾታ መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ ነው። የቴክኖሎጂ ልምምድ አናሳ መሆን በተለይ ደግሞ በፐብሊክ ሴክተሩ ያለው ደካማ የዲጂታል ክህሎት በፍጥነት ከሚጓዘው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር የማይጣጣም ነው።
የአሁን ላይ ባለው የዲጂታል እድገት የሥራው ዓለም በፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል። በዚህም በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ10 ስራዎች 9ኙ የሚሆኑት የዲጂታል ክህሎቶችን እንደሚፈልጉ ይገመታል።
ለዚህ ደግሞ የትምህርት ሥርዓቱን ማሻሻል፤ በምን፣ እንዴት፣ እና በማን የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስ ግልጽ የፖሊሲ ሥርዓት ያስፈልጋል። በተጨማሪም ህጻናት በትምህርት ቤታቸው እንዲህ አይነቱን ክህሎት እንዲያገኙ ማስቻልና ልዩ ልዩ ንቅናቄዎችን መፍጠር አስፈላጊ ነው።
#ጥያቄ: ባሉበት ዘርፍ ሥራው የሚጠይቀውን የዲጂታል ክህሎት አለኝ ብለው ያስባሉ? ለማሳደግና ለመማር እየሞከሩ ነው ? ምን ፈተናዎች አሉት? 👉
https://t.me/IbrahimibnuDelilZ