Forward from: Thoughts
ለራሴ አዝዤ አላውቅም።
እሷ ስትበላ ራሱ ማየት ሀሴት ይሰጠኛል። እነገናኛለን ብዙ ምግብ አዝላታለሁ
መጀመሪያ ፀጥ ብላ እየተሻማች ቀጥሎ የምግቡን እያንዳንዱን ቅመም ለማዳመጥ በሚመስል አኳኋን አይኗን ጨፍና ስትመሰጥ ትቆይና
መጥገብ ስትጀምር ስለ ምግብ አስደሳች ተፈጥሮ lecture እያረገቺኝ በልታ ስትጨርስ ትንሽ አውርተን እንለያያለን።
ሁሉም ነገር በምግብ ካልተመሰለ ግር ይላታል።
አንድ ቀን እኮ ነው እንዲሁ ተገናኝተን እየበላች "ስሚማ" አልኳት "እ" አለቺኝ ቀና ሳትል
"ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?" አልኳት እንደአንተ አይነት እንድትል ነበር
"እንደ ፈንዲሻ..." አላስጨረስኳትም ቱግ አልኩ
"የጠየኩሽ እኮ ስለ እኔ..." አመለጠኝ
"ማለቴ ስለ ወንድ ምርጫሽ ነው እንጂ ስለ ምግብ ምርጫሽ አይደለም።
"አስኪ አስጨርሰኝ ስለ ወንድ ምርጫዬ በምግብ አድርጌ እያስረዳውህ እኮ ነው" አለቺኝ"
የሆዳም ነገር እያልኩ"በሆዴ "ይሁን ቀጥዪ የሚል ፊት አሳየኋት
" እንደ ፈንዲሻ በደስታዬ ጊዜ ብቻ የሚኖር እንደ ንፍሮም በሀዘኔ ጊዜ ብቻ የማገኘው ሳይሆን
እንደ እንጀራ ሁሌ የሚያስፈልገኝ ስፈልገው የማላጣው እንዲሆን ነው" ብላኝ መብላቷን ቀጠለች።
"ወይ አንቺ ጉደኛ እንጀራ የሆነ ባል ይሰጠኝ እያልሽ ነው" እያልኳት እሷ ስተስቅ እኔ ስገረም አበቃን።
©nani
https://t.me/justhoughtsss