...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ።
ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ።
የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን።
"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል።
የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።"
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ
መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::''
ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው።
ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"
አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።
ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው።
አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::
"ፍቅር መተወን አይችልም
በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት።
አለመኖር 📚