የመጨረሻ ልጅ ነኝ ቤተሰቦቼ ሲያዩኝ የኖሩት ቀዳዳዬን ሊሰፉ ፣ የጎደለኝን ሲሞሉልኝ ነው ። ዝምታዬ ቦታ አለው ይታይም ነበር ።
አደኩኝ እና ከአለም ተቀላቀልኩ!
የተወደድኩ ከመሰለኝ perfect man ለመምሰል መጣር አቆማለሁ ተራራ ጫፍ ቆሜ ጀርባዬን እሰጣለሁ ። እድሜልክ የሚያስፈርድብኝ ጉዳይ ለማንም አታውሩ ሳልል አጋራለሁ ...
እንደማምናቸው የሚያምኑኝ ይመስለኛል ስህተቴን በፋይል በፋይል የሚያደራጁት አይመስለኝም ።
አስቤ ያልጨረስኩትን ያላለቀ ሃሳቤን አጋራለው ። ተሳክቶልኝ እና ወድቄ የተሰሙኝ ስሜቶች እንደወረደ እተርካለሁ
የኔ ያልኳቸው መጉደሌ የሚያርቃቸው አይመስለኝም ። ለፍርድ የሚያቀርቡኝ የሚወስኑብኝ የሚያስፈርዱብኝ አይመስለኝም !
እነሱ ላይ መጨከን ስለማልችል የሚጨክኑብኝ አይመስለኝም ።
አለም አወቃቀሩ እንደ ቤተሰብ አይነት አለመሆኑን ለማወቅ ስንት የሃዘን ጅራፍ እላዬ ላይ እንዳረፈ !!
ጅራፉ የፈጠረብኝ ማንነት እንዴት ፈሪ እንዳደረገኝ... ማመኔ የወለደው ጥርጣሬ ብዛት መዓት ሆነ ። ውልቃቴ ንቅናቄ እንዳይኖረው እንዴት በጥንቃቄ እንደምራመድ ።
አረማመዴ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች እንዴት ጉዳዬ እንደማልላቸው ። አለምን እንዴት እንደማላምናት !
እንደ ዘበት የሰማሁት ተረተረት እንዴት አንደፍልስፍና መቁጠር እንደጀመርኩ
።ቃላቸውን ከበሉ ለቃላቸው እረጅም ርቀት የሚሄዱ ሲገጥሙኝ እንዴት እንደምደነግጥ !! በድያቸው አፀፋውን ከመለሱ እንዲሁ የተውኝ እንዴት እንዳሳመሙኝ!!
እኔ ብሆን ኖሮ ፣እኔ ማለት ፉከራ እና ሽለላ መኖር እንዴት እርግፍ አድርጎ እንዳስተወኝ ።
ቅዱስ ነኝ ከሚሉ ሌቦች ሌባነኝ የሚሉ ሌቦች እንዴት እንደማይጎረብጡኝ ። ለመወዳጀነትም አልፀየፋቸውም ።
በርግጥ ችግሩ የመጨረሻ ልጅ መሆን አይደለም ።🙌
© Adhanom Mitiku