💥💥ዲቦራ💥💥
ባልኮኒውን እየወለወልኩ አያታለሁ። ፈገግታ ሳይለያት ነው የምትውለው። አንድ ለመጠጣት የመጣውን ሁለት ሶስት ስታስደግም አይቻለሁ። አለቃችን ከሁሉም ሰራተኛ በላይ ለእሷ ስሜት ይጠነቀቃል። ዋነኛ የቤቱ የገቢ ምንጭ መሆኗ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ገና ከተቀጠረች በሳምንቱ አለቃችን ሰዓት እንድታከብር ሲቆጣት "የምሰራው አምኜበት እስከሆነ ድረስ ያንተ አስታዋሽነት አያስፈልገኝም ህሊና አለኝ እኮ! ግን ገና ሳትቀጥረኝ ነግሬህ ነበረ እኔ አስተናጋጅ የመሆን እቅድ አልነበረኝም፥ ቀን ጥሎኝ ነው አሁንም ትምህርት ስለምማር ነው እንጂ ያለምክንያት ስራ የምበድል ሰነፍ አይደለሁም" ብላ ሽርጧን ወርውራ ስትወጣ
አለቃችን ራሱ ደንግጦ "እባክህ ንጉስ አንተ አነጋግራት እስኪ" ብሎ ላከኝ። ስሄድ ልብስ መቀየሪያ ውስጥ ተቀምጣ ስታለቅስ አየኋት ቀያይ ጉንጮቿ በርበሬ መስለዋል ልቤን እፍን አደረገኝ ከፊቷ ሄጄ በርከክ አልኩና ፊቷን ቀና አድርጌ "አሁን በሶል ንግግር ተናደሽ ማልቀስሸን ባወራ ማን ያምነኛል?!" አልኳት ፈገግ አለች
"ፀብ አልችልም ለዛ ነው እንጂ እሱም የተናገረው ትክክል ነው ስራዬ አይደል?!" ፊቷን ለመጥረግ የለበሰችው ሸሚዝ አጥሮ አልደርስ አላት። "ይኸው ሶፍት በቃ ይበቃሻል" ብዬ ሰጠኋት "ሳለቅስ ደበርኩህ እንዴ?!" አለቺኝ ፈገግ ብላ አሁንም አይኗ እንደደፈረሰ ነው። "እንደውም ደስ ነው ያለኝ ሶል እንደዛ የሚናገረው ሰው ያስፈልገው ነበረ በይ አሁን ነይ እንውጣ" ብያት ወጣን
ተያይዘን ከክፍሉ ስንወጣ ሶል በር ላይ ቆሞ ነበረ "ውጡ ውጡ መሽቷል እንደውም" አለ የባጥ የቆጡን እያወራን ቤቷ አድርሻት ተመለስኩ። ከዛ ምሽት በኋላ ጓደኝነታችን በይፋ ታወጀ። ረጅም ሰዓት ከስራ በኋላ እናወራለን ቤቷ ወይ ክላሷ አድርሻት እመለሳለሁ።
ፈጣሪ ራሴን በሴት መልክ ቢሰራኝ እሷን የምሆን ይመስለኛል። በፊት የምጫወተውን ጨዋታ ራሴ ላይ ትጫወትብኛለች። የምሳሳለትን ፈገግታዋን ለማንም ጠጪ ታባክነዋለች። ውስጤ ሲጨስ ሌላ ሰው የሚሰማው እስኪመስለኝ እናደዳለሁ "ተረጋጋ ምን እየሆንክ ነው" ብለውም ራሴን ምንም ማድረግ ያቅተኛል።
ሆን ብላ እንደምትጫወት የገባኝ ፈገግ ብላ ስትስለመለም ወንዱ ሲፍረከረክ ሰረቅ አድርጋ ስታየኝ ነው። ራሴን ስራዬ ላይ የጠመድኩ ልመስል ስሞክር ሁለት ግዜ በሀይል ጨብጬ ብርጭቆ ሰብሬያለሁ። ይሄኔ ያንን የተረገመ ፈገግታዋን ብልጭ አድርጋልኝ ታልፋለች።
የተወለወለ ባልኮኒዬን እየወለወልኩ ትመጣና ተንጠራርታ ፀጉሬን እየነካካች "ፀጉርህን እንዳትቆረጠው እንደዚህ ሲሆን ነው የምወደው" ብላኝ ትሄዳለች። ልቤ የሚሞቀውን ሙቀት ላስቆመው ይከብደኛል።
ለሁሉም ፈገግ ስትል እንዲህ እያልኩ ራሴን አፅናናለሁ "ለሁሉም ፈገግ ብትል ለሁሉም በነፃነት ከእኔ ጋር የምታወራውን ታወራለች?! ለሁሉም ፈገግ ብትል ከእኔ ውጪ ማን እንዲሸኛት ፈቅዳለች?! ፈገግታዋን ቢያዩ የህይወት ፍልስፍናዋን ያውቃሉ?! ሶል ዝጉ ብሎ ሲሄድ ወይን ይዘን ቀን ባስተናገድንበት ማታ ራሳችንን እያስተናገድን ስለቤተሰቧ ስታወራ አይተዋት ያውቃሉ?! አያውቁም" እያልኩ ንዴቴን አበርደዋለሁ ኧረ እንደውም አጉል የልብ ልብ ይሰማኛል
ቀኑን እንደዚህ ስታበግነኝ ስትውል ማታውን እኔን ብለው የሚመጡ ሴቶች ባልኮኒው ጋር ይደረደራሉ። በየተራ ይመጣሉ። ትኩረቴን አንዷ ላይ ካቆየሁት አትችልም ትመጣለች። "የኔ ንጉስ" ትለኛለች "ወዬ ልዕልቴ" ብላት ደስስ ባለኝ ኮስተር ብዬ "ምን ልቅዳ?!" እላታለሁ ያኔ ቁጣ ቁጣ ይላታል የጀመርኩትን ወሬ በደንብ ትረብሸዋለች።ፊት አልሰጣትም ትኩረቴ እነሱ ላይ ይሆናል። እንደማትችል አውቃለሁ ፊቷ ሲቀላ አያለሁ ደስስ ይለኛል የቀኑ ፈገግታዋ ይጠፋል። ቀስ በቀስ ሴቶቹ ይሄዳሉ።
እንደዚህ ያለንግግር ስንናቆር ውለን ስራችንን ጨርሰን ስንወጣ ምንም እንዳልተፈጠረ የባጥ የቆጡን እየቀባጠርን እሸኛታለሁ። አንዳንድ ቀን አስተቃቀፏ ይለያል። ደረቴ ላይ ተጣብቃ ትቆያለች። ፀጉሯን እያሻሸሁ "የኔ ቀበጥ ደግሞ ምን ፈለግሽ?!" እላታለሁ "ምንም የኔ ንጉስ ደህና እደር" ብላኝ ጉንጬን ሳም አድርጋኝ ሳትዞር ትሄዳለች። በእያንዳንዷ እርምጃዋ ልቤ ይከብዳል ምን እየሆንኩ ነው?! እያልኩ ወደቤቴ አዘግማለሁ
አንዷ በቅርብ ትዳሯን የፈታች ሴት በብዛት መምጣት አበዛች። ደግሞ ብቻዋን የምትመጣው እንደተመቸኋት ግልፅ ነው ለማውራት የምትከብድ አይደለችም። አንድ ቀን እንደተለመደው ስራዬን እያሳለጥኩ ሳወራት አምሽቼ እሷም ሄዳ ዘጋግቼ ልወጣ ስል ዲቦራን አጣኋት የታለች ስላቸው ተረባብሻ ነው የወጣችው አሉኝ ብደውል አላነሳ አለች። ነብሴ ተጨንቃ አደርኩ። "ምን እየሆነች ነው?! ቢያንስ የሆነ ነገር ብላኝ አትሄድም?!" እያልኩ ስብሰለሰል አደርኩ
ጠዋት ስገባ አልገባችም አርፍዳ መጣች ፊቷ ልክ አይደለም አይኔን ትሸሻለች ላወራት ስሞክር አለባብሳ ታልፈዋለች። ልንወጣ ስንል ቀድሜ ወጥቼ ጠበኳት "ብቻዬን መሄድ እችል ነበር" አለች እና ራመድ ራመድ ማለት ጀመረች "እሺ ምንም አናወራም አብሬሽ እንድሄድ ፍቀጂልኝ" አልኳት ሳትመልስልኝ መራመድ ቀጠለች
ቤቷ በር ላይ ስንደርስ "ደህና እደር" አለቺኝ ራቅ ብላ እንደቆመች "እንዳቅፍሽ አትፈቅጂልኝም?!" አልኳት ውስጤ ተሰብሮ አየቺኝ ያጣመርኩትን እጄን ዘረጋሁላት እቅፌ ውስጥ ገባች "ንገሪኝ በምንድነው ያስቀየምኩሽ" አልኳት ፀጉሯን እየደባበስኩ
"ሴትዮህ በጣም ቆንጆ ናት ፈት አትመስልም" አለቺኝ
ቀና አድርጌያት "ፈት መልክ አለው እንዴ?!" "እኔንጃ" ብላ ድጋሜ ፊቷን በደረቴ ደበቀችው "የኔ ልዕልት ቀናሽ እንዴ?!" አልኳት "ትንሽ" አለች ቀና ሳትል "እንድትቀኚ ብዬ እኮ ነው ሳወራት የነበረው" አልኳት
ወገቤ ዙርያ ያለውን እጇን አጥብቃ "ይሄ ጨዋታ እያደከመኝ ነው ከዚህ በላይ የምችል አይመስለኝም" አለች ፊቷን ቀና አድርጌ እያየኋት "እኔንም አቅም ካሳጣሺኝ ቆይቷል" አልኳት እጇን ከወገቤ ላይ አንስታ አንገቴ ዙርያ አደረገችውና ተንጠራርታ
"ምኖቹ ሞኞች ነን?! ምን እየጠበቅን ነው ታድያ?!" አለቺኝ በሹክሹክታ "አንቺን እየጠበኩሽ ነበር" አልኳን እኔም በጆሮዋ አንሾካሹኬ
"መጠባበቁ የሚበቃ አይመስልህም" ብላ ሸሚዜን ከደረቴ ላይ ይዛ ተንጠራርታ ሳመቺኝ።
ሰማችሁ ያልኩትን?! ሳመቺች!!!
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss