ዩናይትድ ስቴትስና ኔቶ - ዩክሬናውያን የ #ATACMS ሚሳይሎችን ዒላማ በመምረጡ ረገድ ይበልጥ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በፅኑ አሳሰቡ።The NewYork Timesከአንድ ወር በላይ በፊት ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ውስጥ በሚገኙ የወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ምዕራባውያን ሰራሽ የረዥም ርቀት ሚሳይሎችን ማስወንጨፍ መቻሏ በመሣሪያው አቅራቢዎች ዘንድ ታላቅ አድናቆትን አሰጥቷት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
ይሁን እንጂ የዩክሬን ጦር በብርያንስክ ክልል ላይ የመጀመሪያውን ሁለት የሚሳይል ጥቃቶች ከፈጸመ በኋላ ከወደ ሩስያ በኩል ካሁን ቀደም በይፋ የማይታወቅ እና #ኦሪሽኒክ በተባለ መብረቅ መሠል የሚሳይል አዝናቢ በዴኒፕሮ በሚገኙ የወታደራዊ ኢንዱስሪ ዞኖች ላይ ምላሽ ከተፈጸመ በኋላ ዩክሬን ቀደም ሲል የነበረውን የረዥም ርቀት ሚሳይል አጠቃቀሟን በመቀነስ #ሂማርስ የተባለውን ሮኬት ብቻ በማስወንጨፍ ተገድባ ቆይታለች።
የዩናይትድ ስቴትስ እና የኔቶ ባለስልጣናት ዩክሬን የአሜሪካን ATACMS የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ከቁጥራቸው አናሳነት እና ከዒላማዎቻቸው አንጻር ይበልጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ መጠቀም እንዳለባት ያምናሉ - ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
ዩክሬን በምትጠቀማቸው ሚሳይሎች ቁጥር ላይ የበለጠ ጠንቃቃ መሆን እና ዒላማውም የበለጠ ተመራጭ ሊሆን እንደሚገባው ማጤን እንዳለባት ማስጠንቀቂያ እንደደረሳት ህትመቱ የዩናይትድ ስቴትስ እና የኔቶ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ሰራሽ የረዥም ርቀት ሚሳይሎችን ወደ ሩሲያ ግዛት ማስወንጨፍ አሜሪካ በታሪኳ ሰራቻቸው ስህተቶች ሁሉ ትልቅ ስህተት መሆኑን በተደጋጋሚ በይፋ ተናግረዋል።
https://t.me/EthioGlobal_News