🚨Alert🚨
“ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል ሰሞኑን ነጻ ሜጋ ባይት ለማግኘት “ ሊንክ ጠቅ ያድርጉ ” የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ወደተለያዩ ግለሰቦች እየተላከና እየተዘዋወረ ነው፡፡
ይሄው ከሥሩ ሊንክ የተቀመጠበት የሚዘዋወረው መልዕክት ፡-
➡️ 6 ወር ለቆየ ሲም፣ 10GB
➡️ 1 ዓመትና ከዚያ በላይ፣ 20GB
➡️ ከ5 አመት በላይ ለቆየ ሲም፣ 50GB ነጻ ሽልማት ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡
አንዳንድ ሊንኩን የከፈቱ ሰዎችም፣ “ ስንከፍተው መረጃዎት እየተበረበረ ነው ይላል፡፡ ጉድ ተሰርተናል ” ሲሉ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ብዙዎች ደግሞ ይህን ጉዳይ ኢትዮ ቴሌኮም ያውቀዋል ? በማለት እየጠየቁ ነው፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሚዘዋወረውን መልዕክት ተቋሙ ያውቀዋል? ትክክለኛስ ነው? ሲል ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቋል፡፡
የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኢፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ምን ምላሽ ሰጡ ?
“ የኛ ቲምም ቼክ አድርጎታል፡፡ Phishing የሚሉት የማጭበርበር መልዕክቶችን የሚልኩ ናቸው፡፡
ታማኝ ከሆኑ ካምፓኒዎች የሚላኩ መልዕክቶችን በማስመስልና የሰዎችን መረጃ የሚወስዱ Phishing ብለን የምንጠራቸው የሳይበር ጥቃት መንገዶች ናቸው፡፡
እኛ ያስቀመጥነውም እንሰጣለን ያልነው ሽልማትም የለም፡፡ የላክነውም መልዕክት የለም፡፡ የኛ የሴኩሪቲ ቲምም እየተከታተለ ነው፡፡
ሊንክ ልከው እርሱን ንኩ ነው ‘ንኩ’ የሚሉት የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን፡፡ ግን ፐርሰናል መረጃዎችን የመውሰድና ላልተገባ ነገር ሰዎችን ለመዳረግ የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡
ዌብሳይቶቹን የኛ ቲሞች ሞኒተር እያደረጉ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ቁጥጥር እያደረጉ ነው፡፡
ሳይቶቹን የመዝጋት ሥራዎች እየተሰሩ ነው በቅንጅት፡፡ ስህተት እንደሆነ፣ የኛ እንዳልሆነ ሰው እንዲያውቅ እናደርጋለን፡፡
ይኛው መልኩን ቀይሮ የሰውን መረጃ ለመውሰድ ሆነ እንጂ ብዙ ጊዜ በተለይ ቴሌግራም አካባቢ ላይ ተከታይ ለማግኘት በኢትዮ ቴሌኮም፣ በቴሌ ብር እየተከፈቱ ደንበኛ ለማብዛት የሚደረጉ ጥረቶች አሉ፡፡
ይሄም ኢንቴንሽኑ ሌላ ቢሆንም ያው ነው፡፡ ከእኛም ብቻ አይደለም ምንጩን ስናጣራው ከሌላ አገር ውስጥ የሚመጣ፣ ወደ ሌላ አገር ሪፈር የሚያደርግ ነው ሊንኩ፡፡
የትልልቅ ተቋማት መልዕክት በማስመስል ሊንኮችን አስቀምጠው አጓጊ ሽልማቶችን እየሰጡ የሰዎችን መረጃ የማጭበበርበር ነገር ነው የሚፈጠረውና Phishing በተለያዬ በኢሜይል፣ በቴክስት፣ በጥሪ መልክም ሊመጣ ይችላል፡፡
ሰዎች ሊንኩን ባለመንካት ከእንደዚህ አይነት አሳሳች መልዕክቶች ራሳቸውን ይጠብቁ፡፡ እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲገጥማቸውም በ9090 በነጻ ደውለው በዚያ እንዲያሳውቁንም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ” ብለዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በበኩሉ፣ “ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ስልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል መልዕክቶች ወደ ተለያዩ ግለሰቦች እየተላኩ መሆኑን እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡
አስተዳደሩ፣ “ መልዕክቱ የግለሰቦችን ሚስጥራዊ መረጃዎችን የማጥመድ ጥቃት (Phishing Attack) መሆኑን ማረግገጥ ችያለሁ ” ብሎ፣ ግለሰቦች ሊንኩን ባለመክፈት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
Credit: #TikvahEthiopiaFamilyAA