Ethio University News


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


📚 Your premier source for daily educational news.
Buy ads: https://telega.io/c/EthioUniversity_News

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


#Announcement | #Raya_University

ራያ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ የተመደቡ (freshman) ተማሪዎቹ እና በ2018 ሪሚድያል ፕሮግራም ተከታትሎ ማለፊያ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ጊቢ የሚገቡበት ቀናት ከጥቅምት 16 እስከ 18 /2019 መሆኑን አሳዉቀዋል።

▸ ሙሉ መረጃው ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዘዋል።

@EthioUniversity_News
@EthioUniversity_News


#Announcement | #JU

ጅማ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቹ ጥቅምት 4 እና 5 ጥሪ አድርጓል።

@EthioUniversity_News
@EthioUniversity_News


#Woldia_University

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

@EthioUniversity_News
@EthioUniversity_News


📢 ማስታወቂያ

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተወዳድራችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ

ትምህርት ሚኒስቴር ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ የሆናችሁ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በተመዘገባችሁበት የምዝገባ ሊንክ በመግባት፣ ስማችሁን እና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን።

📅 የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት
🔗 የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply

@EthioUniversity_News
@EthioUniversity_News


#ማስታወቂያ | #DMU

በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዚዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት በሚከተሉት የአመራርነት ስራ መደቦች ላይ ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ መሰየም ይፈልጋል።

ይህ ማስታወቂያ #በአዲስ_ዘመን ጋዜጣም ታትሞ የወጣ ሲሆን ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 22 የስራ ቀናት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንጻ የብቃት እና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 106 ወይም በአዲስ አበባ በሚገኘው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ ወይም በኢሜል አድራሻ hr@dmu.edu.et መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። #DMU

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


#ጥቆማ

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የስልጠና ዘርፎችን በማካተት ለ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን የስልጠና መስኮች የሚያስተዋውቅበት የመረጃ ሳምንት ከመስከረም 14/2019 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት ሆኗል።

ተቋሙ የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች፦
➛ በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች
➛ በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች
➛ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) (ደረጃ 8) በሁለት ፕሮግራሞች

በኢንስቲትዩቱ የሚሰጠው ስልጠና 50 በመቶ የንድፈ-ሃሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ እንደሆነ ተገልጿል።

ተቋሙ በ16 የሳተላይት ካምፓሶች እና በሁለት ማዕከላት አማካኝነት ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


📢 ማስታወቂያ
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
 
1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
 
የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።
 
2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  
3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።
#ትምህርት_ሚኒስቴር

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


#ጥቆማ | #EPSU

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን አጠናቀው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራም (Extension) መመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


#ማስታወቂያ | #MoE

ለወሊሶ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ


በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት የምትገቡበትን  የመግቢያ ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እስኪገለጽ ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

#ማሳሰቢያ፦ በሌሎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተገኝታችሁ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ወደ ትምህርት ቤቶቹ በምትገቡበት ጊዜ መረጃ በሚከተሉት ስልኮች እየደወላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን።

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


#ማስታወቂያ

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በማለፍ በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፤

 
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና በመውሰድ ያለፋችሁ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ የመግቢያ ቀን መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።
ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው፤

1.  ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤ ለምሳሌ፡- ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ ወዘተ፣

2.  ለመኝታ አገልግሎት የሚያስፈልጉ አንሶላና ብርድ ልብስ፣

3.  እስካሁን ሲማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት የተሰጣቸውን መሸኛና የትምህርት ውጤታቸውን የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ይዘው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፤

4.  ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ከደረሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን ዩኒፎርም በራሳቸው ወጪ የሚያስዘጋጁ በመሆኑ፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
#ትምህርት_ሚኒስቴር

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


#ጥቆማ

‎የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ2026/2027 የትምህርት ዘመን የድኅረ-ምረቃ አመልካቾች መቀበል ጀምሯል፡፡

አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትነው ያለፋ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አመልካቾቹን የሚቀበለው የትምህርት ክፍል የፅሑፍ እና የቃል ፈተናዎች ይሰጣል፡፡

የሕክምና ትምህርት ቤት (በመደበኛ መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በአራት የMSc ትምህርት መስኮች

የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት (በመደበኛ እና በዕረፍት ቀናት መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በስድስት የMPH ትምህርት መስኮች

የነርሲንግ ትምህርት ቤት (በመደበኛ መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በስምንት የMSc ትምህርት መስኮች

የምዝገባ ጊዜ 👇
ከመስከረም
11-27/2019 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃ፦
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


ዘጠኙ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለራስ-ገዝነት መነሻ የሚሆኑ ሥራዎች ተሰናድተው መጠናቀቃቸውን ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል።

ላለፉት ጊዜያት አስፈላጊው የሰነድ ማደራጀትና ሌሎች ሥራዎች ሲከናወኑ እንደነበር የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ቀርቧል፣ አሁን የሚጠበቀው የተቋሙ ምላሽ ነው ብለዋል።

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፍስሐ ጌታቸው (ዶ/ር) በበኩላቸው አስፈላጊው ሰነድ የማዘጋጀት ሥራ መጠናቀቁን አስረድተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በይፋ ጥያቄውን ተቀብሎ "የራስ-ገዝነት ሥራ ጀምሩ" ሲል እንጀምራለን ብለዋል።

የራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ሒደቱን እንዲጀምሩ የሚፈቀድላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን መንግሥት መግለፁ ይታወቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ ለሁለት ዓመት የሽግግር ሥራ በመሥራት ራሳቸውን ወደ ማስተዳደር ይገባሉ ተብሏል።

@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews


#ማስታወቂያ

ለ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

በ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች፣ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ስማችሁንና ሪፈረንስ ቁጥራችሁን በማስገባት እስከ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ እንገልጻለን።

#ማሳሰቢያ፦ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው በተጠባባቂነት ከተያዙ መካከል የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን እየገለጽን ምደባ የሚካሄደው ክፍት ቦታዎች ባሏቸው ት/ቤቶች እንደሚሆን እናሳውቃለን። #MoE

✦————————————✦ 
@Ethio_UniversityNews
@Ethio_UniversityNews
✦————————————✦


#Announcement | #EPSU

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አድርጓል።

➞ የመግቢያ እና የምዝገባ ቀናት – መስከረም 20 እና 21 / 2019 ዓ.ም (September 30 – October 01 / 2026)

➞ የኦሬንቴሽን ቀን – መስከረም 22 / 2019 ዓ.ም (October 02 / 2026)

➞ የ1ኛ ሴሚስተር ትምህርት የሚጀመርበት ቀን – መስከረም 25 / 2019 ዓ.ም (October 05, 2026)

|| @ethio_UniversityNews


#Announcement | #ASTU

ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የ 2019 መደበኛ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ አዲስ ገቢ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ

ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን መስከረም 20 እና 21/2019

ስሆን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ግቢው ስትሄዱ

➞ የ 12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፍኬት
➞ ከ 9-12 የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
➞ 4 ፓስፓርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ
➞ አንሶላና ብርድ ልብስ
➞ የስፖርት ትጥቅና ጫማ ይዛችሁ እንድትመጡ አስታውቋል።

#ማሳሰቢያ: ከመግቢያ ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም።

|| @ethiopian_universities


#Announcement | #AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ 2019 የመጀመሪያ አመት (Freshman) ተማሪዎች ወደ ግቢ የሚገቡበት ቀናት መስከረም 18 እና 19 /2019 መሆኑን ገልጸዋል።

|| @ethiopian_universities


#Update | #Mekelle_University

መቋለ ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ አድርጎ የነበረው የምዝገባ ጥሪ ወደ መስከረም 18 /2019 ዓ.ም መራዘሙን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን እና አንዳንድ ያልተጠበቁ ጉዳዮችን ለመፍታት ቀጣይነት ባለው ውይይት ላይ እንደምገኝ ገልጿል።

|| @ethiopian_universities


#ማስታወቂያ

በ2019 ወደ ፌዴራል አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ9ኛና 10ኛ ክፍል ለመማር ተመዝግባችሁ ላላፋችሁ እና እስካሁን ድረስ ላልተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣
ቀደም ሲል ለምዝገባ በተጠቀማችሁበት ሊንክ በመግባት እስከ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለንባለን። #MoE

|| @ethiopian_universities


#Debre_Tabor_University

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የተቋሙ ነባር የቅድመ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 28 እና 29/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት (Freshman) እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

|| @ethiopian_universities


#HUCMHS

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከስር የተዘረዘሩት ትምህርት መስክ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 14 እና 15/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

1. ፋርማሲ ➻ ከ2015-2018 ዓ.ም ባቾች
2. ሕክምና ➻ የ2018 ዓ.ም ባች
3. HO, Health Informatics, Nursing, Psychiatry Nursing, Environmental Health, Midwifery, Optometry, MLS,  Anesthesia, and MRT ➻ ከ2016-2018 ዓ.ም የገባችሁ ባቾች

በ2015 ዓ.ም የገባችሁና በተራ ቁ. 3 ላይ የተዘረዘሩት ፕሮግራም ተማሪዎች ትምህርት የምትቀጥሉበትን ቀን በቀጣይ የሚያሳውቅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

|| @ethiopian_universities

20 last posts shown.

6 096

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

#Update | #Mekelle_University መቋለ ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ አድርጎ የነበረው የምዝገባ ጥሪ ወደ መስከረም 18 /2019 ዓ.ም መራ...
#Announcement | #ASTU ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የ 2019 መደበኛ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ አዲስ ገቢ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ ...
#Call_Announcement #Mattu_University መቱ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች ወደ ጊቢ የሚመለሱባቸዉ ቀናት መስከረም 7 እና 8 /2018...
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 252 የጤና ባለሙያዎች አስመርቋል። ተመራቂዎቹ በሕክምና ዶክትሬት፣ በነር...
#ተጨማሪ ጳጉሜን 02 እና 03/2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (UAT) ለመውሰድ የመፈተኛ ...