በፍትሐብሔር ክርክር የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች ማን መቼ ያነሳቸዋል?
በፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት እና በተከራካሪዎች
1. በተከራካሪዎች
ከሳሽ በተከሳሽ ላይ በቃል ክርክር ጭምር (በቅፅ 25 በሰ/መ/ቁ.222297)
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.358 መሰረት የመቃዎሚያ ከሳሽ የሆነ ተከራካሪ (በቅፅ 26 በሰ/መ/ቁ.196255)
ከሳሽ በጣልቃ-ገብ ላይ (ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.244 (1) (2) ማንኛውም ተከራካሪ)
ተከሳሽ በከሳሽ ላይ ፡-መርህ ነው 234 (1) (ሐ) እና ብዙ የሰበር ውኔዎቾ
ጣልቃ-ገብ በከሳሽ እና በተከሳሽ (በቅፅ 20 በሰ/መ/ቁ.108647)
አንዱ ተከሳሽ በሌላኛው ተከሳሽ ላይ (በቅፅ 12 በሰ/መ/ቁ.49295)
ባልተነጣጠለ ሃላፊነት በቀረበባቸው ክስ አንዱ ተከሳሽ ያነሳው የይረጋ መቃዎሚያ ሌሎች ተከሳሾች ባያነሱትም ክሱን ያቋርጣል (በቅፅ 4 በሰ/መ/ቁ.19081)
ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት የሚያነሳቸው መቃዎሚያዎች
ፍ/ቤቱ የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9 እና 231 (1) (ለ) )
የክስ ምክንያት የለውም (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9 እና 231 (1) (ለ))
ጉዳዩ በውሳኔ ያለቀ ነው (ቅፅ 13፣ ሰ/መ/ቁ.58119)
በፍሕብሔር የሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀመጡ ይርጋዎች (ቅፅ 1፣ ሰ/መ/ቁ.17361)