የሱዳን መንግስት ሰራዊት በደቡብ ሱዳናውያን ላይ የፈፀመው ጅምላ ግድያ ቁጣ ቀሰቀሰ
ደቡብ ሱዳን በሱዳን የሚገኙትን አምባሳደሯን ጠርታለች የሱዳን መንግስት ሰራዊት ከሰሞኑ በተቆጣጠረው የጀዚራ ግዛት በስደት የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያንን ሲገሉ እና ሲያሰቃዩ የሚያሳዩ በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፉ ሪፓርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
በጀነራል አብዱልፈታ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን መንግስት ሰራዊት ለወራት በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ቁጥጥር ስር የነበረውን የጀዚራ ግዛት ከቀናት በፊት በእጁ ካስገባ በኋላ ፥ በግዛቱ በስደት የሚኖሩ የደቡብ ሰዱን ዜጎች ላይ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል ተብሏል።
የደቡብ ሱዳን ኘሬዝደንት ፅ/ቤት ዛሬ ምሽቱን ባወጣው መግለጫ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ተፈፅሟል የሚል ክስ አቅርቧል።
በዚህም ደቡብ ሱዳን በፓርት ሱዳን የሚገኙትን አምባሳደሯን ወደ ጁባ እንደጠራች አስታውቃለች።
የሱዳን ሰራዊት ግድያውን የፈፀመው የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ አባል ናቸው በሚል እንደሆነ ከግድያው ያመለጡ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ።
የሱዳን ሰራዊት ፈፅሟል በተባለው ጅምላ ግድያ በርካቶች ቁጣቸውን የገለፁ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት በመሪው አብዱልፈታ አልቡርሃን ላይ ማዕቀብ ሊጥል መሆኑም እየተገለፀ ነው።
#እውን_መረጃ