ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮር የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ ከታኅሳስ ወር መጨረሻ ወዲህ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ አምስት ሰዎች እንደሞቱና 270 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ አስታውቋል።
ባካባቢው ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት፣ የንጽህና አጠባበቅ ጉድለትና የሰዎች እንቅስቃሴ በሽታው በስፋት እንዲሠራጭ ሊያደርገው እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል ተብሏል። በዞኑ በሽታው ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ባንድ የጸበል ቦታ ውስጥ ከተከሰተ ወዲህ፣ በክልሉ በ16 ዞኖች በ60 ወረዳዎች የተሠራጨ ሲኾን፣ እስካሁን 4 ሺሕ 983 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል።
@Ewun_Mereja